ወስላትነት በኢትዮጵያ ሕግ ምን ማለት ነው

በአንድ ወቅት በፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በታየ የስርቆት ወንጀል ጉዳይ ተከሳሹ ድርጊቱን መፈፀሙ ተረጋግጦ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ፣ የቅጣት አስተያየቱን እንዲሰጥ የተጠየቀው ዐቃቤ ሕግ ‹‹…ተከሳሽ ድርጊቱን የፈፀመው መጥፎ አመልን በሚያሳይ ሁኔታ በወስላታነት…›› መሆኑን ለፍርድ ቤት በማስታወስ ቅጣቱ ከብዶ እንዲወሰን ይጠይቃል፡፡ ይሄንን የሰማው ተከሣሽም ዐቃቤ ሕጉን አቋርጦ ‹‹ኧረ የተከበረው ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕጉ ራሱ ወስላታ ነው፣ መቀጣቴ ካልቀረ መሰደቤ ለምን?›› ብሎ መከራከሩን ሰምቻለሁ፡፡

ለመሆኑ ወስላታነት ምንድን ነው? ‹‹አንተ ወስላታ!›› የሚለው ግሳፄ ዕድሜያቸው ከፍ ባሉ አባቶችና እናቶች ተደጋግሞ ሲነገር መቼም ሰምተን እናውቃለን፡፡ የከሣቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት ውስልትና ማለት ‹‹አለመታመን፣ የማታለል ድርጊት፣ ማጋጣነት ሥራ ፈትነት›› እንደሆነ ይገልፃል፡፡ በአጠቃላይ ኅብረተሰባችን ወስላታነትን በበጎ ጎኑ አይመለከተውም፣ ዛሬ በዚህች አጭር ጽሑፍ ወስላታነት በተለምዶ ከሚሰጠው ትርጉም በዘለለ በሕጋችን ያለውን ትርጓሜ ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡

ቀደም ብሎ በዚህ ጽሑፍ መጀመሪያ ላይ በተጠቀሰው የችሎት አጋጣሚ ላይ ዐቃቤ ሕግ የቅጣት አስተያየቱን መሠረት ያደረገው የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 84(1)ሀ ሲሆን ድንጋጌው ተከሳሾች ጥፋተኛ የተባሉበትን ወንጀል የፈፀሙት በከሐዲነት ወይመ በወስላታነት፣ ወራዳነትን ወይም መጥፎ አመልን በሚያሳይ ምቀኛነት፣ ጥላቻ፣ ስግብግብነት… ከሆነ ቅጣቱ ከብዶ የሚወሰንበትን አግባብ ይዘረዝራል፡፡

በሌላ በኩል የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 859 ወስላታነት በሚል ርዕስ ሥር ‹‹ማንም ሰው መክፈል እንደማይችል እያወቀ ለሕዝብ አገልግሎት በሚሰጡ ምግብ ቤቶች፣ ሆቴሎች ወይም መኝታ ቤቶችና በመሳሰሉት የንግድ ተቋማት ገብቶ ምግቦችን፣ መጠጦችን፣ መኝታን ወይም ማናቸውም ዓይነት ጥቅሞችን ያዘዘ ወይም ያገኘ እንደሆነ፣ በመቀጮ ወይም ከአንድ ወር በማይበልጥ የማረፍያ ቤት እሥራት ይቀጣል፡፡›› ሲል ይደነግጋል፡፡

በመሆኑም እርስዎ ኪሶ ባዶ ሆኖ መክፈል እንደማይችሉ እያወቁ፣ ምግብ ቤት ገብተው፣ ሜኑ አገላብጠው፣ ያሻዎትን የሚያዙ ከሆነ እርሶ ወስላታ ነዎት!!!

…ጊዜው ደርሶ ቢሉ ሲመጣ የሚከፍሉት እንደሌሎት እያወቁም መጠጥ እያማረጡ ጠርሙስ የሚያስወርዱ ከሆነ አሁንም እርሶ ወስላታ ነዎት!!!

ቸር እንሰንብት!!

×
Stay Informed

When you subscribe to the blog, we will send you an e-mail when there are new updates on the site so you wouldn't miss them.

አባትነትን በDNA በትክክል ማወቅ ይቻላል?
በኢትዮጵያ ሰው በፍርድ ቤት እና ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ስለሚያዝባቸው ሁኔታዎች

Related Posts

 

Comments

No comments made yet. Be the first to submit a comment
Already Registered? Login Here
Abebe
Thursday, 25 April 2024