Know Your Legal Rights - መብትና ግዴታዎን ይወቁ

Notice: All articles in this section are intended for informational purpose only and should not be used to replace the need to consult official documents and to seek the advice of a qualified Lawyer. If you need a professional advice you may need to navigate to Lawyers Directory!

(ለጉቦኞች አይላላኩ፤ ከተላኩ ዘብጥያ ይላካሉ!)

ይህ አጭር ጽሑፍ በማወቅም ባለማወቅም የወንጀል አድራጊዎች ተልእኮ የሚያስፈጽሙ ሰዎች እንዲጠነቀቁ ለማስቻል በግርድፉ የቀረበ ነው፤ ጥልቀት ያለው ትንተና እንዳይጠብቁ። ጽሑፉ ሰዎች የቆሸሸ ገንዘብ የሚያቀባብሉበት እጃቸው፣ እንዲሁም የጉቦኞች የገንዘብ መላላኪያ የሚያደርጉት የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸው አደገኛ መዘዝ ይዞባቸው እንዳይመጣ ሊጠነቀቁ ይገባል የሚል መልእክት ለማስተላለፍ፣ ምናልባትም ለማስጠንቀቅ የቀረበ የሕጉ አጭር መግለጫ ነው። ለሕግ ሙያተኞች ፈጽሞ ጥቅም የለውም ማለት ባይቻልም ዓይነተኛ ጥቅሙ ግን ከሙያው ዓለም ውጪ ላለው ለተራው ማኅበረሰብ ነው። ጽሑፉ ስለማቀባበል የሙስና ወንጀል ውስን የግንዛቤ ማስጨበጫ ነጥቦችን በመያዝ ተዘጋጅቷል። ሕግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንምና ይነበብ።

በቀድሞ አሠሪና ሠራተኛ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 377/1996) እና በአዲሱ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1156/2011) መካከል የተደረጉ ማሻሻያዎችን ወይም እንደአዲስ የተጨመሩትን የሚያሳይ ሰንጠረዥ

መግቢያ

የሰው ልጆች በዚች ምድር ላይ ሲኖሩ የተለያዩ ሕጋዊ ውጤት ያላቸውን ድርጊቶች ያከናውናሉ፡፡ ለአብነት ያክንል ቤት ይከራያሉ ያከራያሉ፣ ጋብቻ ይፈፅማሉ፣ ንብረት ይሸጣሉ ይገዛሉ፣ ወዘተ፡፡ ሕጋዊ ውጤት ከሚያስከትሉ ተግባራት አንዱ ውል ነው፡፡ ውል ሰዎች በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሕይወታቸው ውስጥ ከሚያከናውኗተው የግንኙነት መገለጫዎች አንዱ ሲሆን የፍትሐብሔር ግዴታ አንዱ ዘርፍ ነው፡፡

በዚህ አጭር ጽሑፍ የሕክምና ስህተት ምን ማለት ነው በሀገራችን ሕግስ እንዴት ተካትቷል የሕክምና ስህተት ተፈጽሟል የሚባለው ምን ምን ሲሟላ ነው የሚሉትን ነጥቦች ለመዳሰስና ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንሞክራለን፡፡ 

ተሸከርካሪዎችን ወደ ሀገር ማስገባት የሚችሉት እነማን ናቸው?

·   በተሸከርካሪ አስመጪነት የንግድ ፍቃድ ያላቸው በዘርፉ የተሰማሩ አስመጪዎች፤

·  በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሽከርካሪ ማበረታቻ የተፈቀደላቸው ኢንቨስተሮች፤

· በውጭ ሀገር 5 ዓመት በላይ ኖረው ጠቅልለው ወደ ሀገር ተመላሽ የሚሆኑ ዲያስፖራዎች ወይም ወደ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመኖር የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎች /እነዚህ ማስገባት (ማስመጣት የሚችሉት አንድ የግል መገልገያ አውቶሞቢል ብቻ ነው፡፡)

በአለማችን በየዓመቱ አምስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ሲጋራ በማጨስ ምክንያት በሚከሰቱ የጤና ችግሮች እንደሚሞቱም በዘርፉ የተደረጉ የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ በታዳጊ አገሮች ውስጥ ያለዕድሜ የሚከሰተውን ከፍተኛ የሞት መጠንና ህመምተኛነት በማባባስ ረገድ ትምባሆ ወይንም ሲጋራ ማጨስ ቁልፍ ሚና እንዳለው የሚያመላክቱት እነዚህ ጥናቶች፤ የሲጋራ አጫሾች ቁጥር በአደጉት አገራት እየቀነሰ መምጣቱንና በአንፃሩ ደግሞ በታዳጊ አገራት በከፍተኛ መጠን በመጨመር ላይ መሆኑን ይጠቁሟሉ፡፡

Page 1 of 3