አባትነትን በDNA በትክክል ማወቅ ይቻላል?

አባትነትን DNA በትክክል ማወቅ ይቻላል?

ስለ ኪሜራ ምን ያውቃሉ?

 ሰላም እንዴት ናችሁ በማለት እስኪ ሙያችን በተመለከተ አንድ ቁምነገር ላንሳ፡፡

ሊዲያ ፌርቻይልድ አሜሪካዊ ሴት ናት። ስተኛ ልጇን እንደፀነሰች ከባሏ ጋር በፍቺ ትለያያለች። በፍቺ ወቅት ባሏ ለልጆቿ ማሳደጊያ ቀለብ እንዲቆርጥላት እንዲወሰንላት ለፍርድ ቤት ክስ ታቀርባለች። ርድ ቤቱም የወለደቻቸው ልጆቿ በትክክል ከባሏ ለመወለዳቸው የዲ ኤን ምርመራ እንዲደረግ ትእዛዝ ይሰጣል። ይሁን እንጂ ሁለቱም ልጆች ከባሏ መወለዳቸውን የዲ ኤን ምርመራ ውጤቱ ቢያረጋግጥም እሷ ግን የዘር እናታቸው (Biological Mother) አልነበረችም።

በዚህም ምክንያት ይህቺ ሴት ከሌላ የተወለዱትን ሁለት ልጆችን ይዛ ቀርባ ያለአግባብ ጥቅም ለማግኘት አጭበርብራለች የሚል ክስ ቀረበባት። ልጆቿም ከሷ ተነጥቀው ለመንግሥት የህፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ይሰጣሉ። ሦስተኛውን ልጇን አምጣ ስትወልድም የአይን ምስክር እንዲኖር ርድ ቤቱ ትእዛዝ ይሰጣል። ወዲያውም ከልጁና ከእሷ የደም ናሙና ተወስዶ ምርመራ እንዲደረግ ይታዘዛል። ሆኖም ግን አሁንም የዲ ኤን ምርመራው ፌርቻይልድ የልጇ እናት አለመሆኗን አረጋገጠ። ይህ ሁኔታ በተፈጠረ ሰሞን አንድ ዜና ከወደ እንግሊዝ ተሰማ። ኪጋን የተባለች ሴት ተመሳሳይ ክስተት እንዳጋጠማት ጆርናል ኦቭ ሜዲሲን የተባለ መጽሔት ዘገበ። እንደ መጽሔቱ ዘገባ ኪጋንን ለዚህ ያበቃት ኪሚራ እንደሆነና እናትነቷም የተረጋገጠው የልጇን ኤን ከኪጋን አያቶች ኤን ጋር በማነፃፀር ነበር።

ይህንን ዜና የሰማው የፌርቻይልድ ጠበቃም ጉዳዩን ከኪጋን ጋር ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል በሚል ለፍርድ ቤቱ ይግባኝ ይጠይቃል።

ልክ እንደ ኪጋን ሁሉ ከፌርቻይልድ የዲ ኤን ናሙና ከተወሰደ በኋላ በተመሳሳይ ሁኔታ ከፌርቻይልድ እናት ናሙና ተወስዶ ከልጆቹ ኤን ጋር ሲመሳከር የፌርቻይልድ እናት እና ልጆቹ የዘር ትስስር ያላቸው መሆኑ ተረጋገጠ። ማለትም የፌርቻይልድ እናት የልጆቹ ትክክለኛ አያት ሆና ተገኘች። ፌርቻይልድ ግን ልጆችን አምጣ በትወልድም እናት ያላስባላት ጉዳይ ኪሜራ ስለሆነች ነበር።

 

ኪሜራ ምንድነው?

(ኪሜራ የሆነ) ማለት በእርግዝና ወቅት ሁለት መንትያ ፅንሶች በማህፀን ውስጥ እያሉ ውህደት በመፍጠር አንድ ፅንስ ሆነው አንድ ሰው ሆኖ ሲወለድ ሳይንሱ ኪሜራ ይለዋል። ኪሜራ የሆነ ሰው የመንትያ ውህዱን ኤን አዳብሎ ይይዛል ማለት ነው። በዚህን ግዜ አንዲት እናት ወይም አባት ጽንስ ሲፈጠር ለልጃቸው ያካፈሉት ክሮሞዞም ከራሳቸው ሳይሆን ከተዋሃዳቸው መንትያ አካላቸው ሊሆን ይችላል ማለት ነው፡፡

ይህንን ሳነብ ካገኘሁት ያካፈልኳችሁ ምክንያት ይህም ችግር በእኛም ሀገር የሚከሰትበት አጋጣሚ ስለማይጠፋ ነው።
ለምሳሌ በእኛው ሃገር ከአንድ ዓመት በፊት በአንድ ርድ ቤት በቀረበ የአባትነት ክርክር ጉዳይ አንዲት ሴት ባሏን ስታገባ ፍፁም ድንግል ነበረች ባሏን ካገባችው በኋላም በእርግጥም ከባሏ ፀነሰች። ይሁን እንጂ በፍርድ ቤት ትእዛዝ የተደረገው የዲ ኤን የዘር ምርመራ ለልጅ አናት አስደንጋጭ ነበር። የልጅ አባት ነህ የተባለው ሰውዬ አባት አለመሆኑ ተረጋግጦ በነፃ ተሰናበተ። ምናልባት የሰውየውን ወላጆች ኤን ምርመራ ቢደረግ የህፃኑ አያት ሊሆኑ የሚችልበትና በዚህም አባትነቱ ማረጋገጥ ዕድሉ ነበረ የሚል ግምት አለኘ።

እንዴት አያችሁት Lawyers? እንዲህ አይነት ጉዳይ ቢገጥማችሁ ኪሜራን በማንሳት አባት ነህ የተባለው ሰው ወላጆች ጋር የህፃኑ ኤን ይነፃፀር ብላችሁ ትከራከራላችሁ? እስኪ አስተያየት ስጡበት።

×
Stay Informed

When you subscribe to the blog, we will send you an e-mail when there are new updates on the site so you wouldn't miss them.

የዞን ዘጠኝ አምስት ተከሳሾች ክስ መቋረጥ ብዥታ
ወስላትነት በኢትዮጵያ ሕግ ምን ማለት ነው

Related Posts

 

Comments

No comments made yet. Be the first to submit a comment
Already Registered? Login Here
Abebe
Saturday, 25 May 2024