የዚህ ጽሑፍ ዋና ትኩረት ከሙግት በፊት ያሉ ሥነ-ሥርዓታዊ ሂደቶች አንድን ክርክር ላይ ያላቸዉን ሚና ማጉላት እና ፋይዳቸዉን ማሳየት ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ክርክር ሂደት ቅደመ ሙግት የሚባለዉ ለክርክሩ መሪ ጭብጥ ተይዞ ግራ ቀኙ ማስረጃ ማሰማት ከመጀመራቸዉ በፊት ያለዉ ሂደት ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ክርክር ዋናዉ ሙግት የሚጀምረዉ ጭብጥ ተይዞ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 257 እና ተከታይ ድንጋጌዎቹ ተከራካሪዎች ማስረጃዎቻቸዉ የሚያስረዷቸዉን ጭብጥ እያስመዘገቡ ማስረጃ ማሰማት ሲጀምሩ ነዉ፡፡ ከዋናዉ ሙግት በፊት ባለዉ የቅድመ ሙግት ሂደት በዋናነት ክስና ማስረጃ ማቅረብ፣ መጥሪያ ማድረስ፣ መልስ እና ማስረጃ መቅረብ፣ ክስ መሰማት እና የክስ መቃወሚያዉ ላይ የመወሰን ተግባሮች ይፈፀማሉ፡፡ ይህ የክርክር ሂደት ክርክሩን ለመምራት ዋና መሰረት የሆነዉ ነዉ፡፡ የክርክሩ አቅጣጫ የሚወሰነዉም በዚህ የክርክር ደረጃ ላይ በሚሰሩ ስራዎች ነዉ፡፡ ክርክሩን ግልፅ እና አጭር በሆነ ሂደት ለመፈፀም የሚያስችለዉም የቅድመ ሙግት ሂደቱ ጤናማ መሆን ከቻለ ነዉ፡፡
Courts; as one and perhaps as the most tasks of their purposes and responsibilities, engage in rendering a fair and equitable decision among parties in law suit. Decisions of a court can either be criminal or civil nature. If the case brought before the court involves criminal nature, the court will give decision by adhering to the rules and procedure provided under criminal law and criminal procedure respectively. Police or prison administration is an organ entrusted with enforcing court’s decision.
ባለንበት ዘመን ሕገ መንግሥት ወይም ስለመንግሥት አሠራርና አመራር የሚደነግግ ሕግ የሌሎው ሀገር ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ ሳስበው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት መደንገግና በዛው ልክ መቆጣጠር ያስፈለገበት መሠረታዊ ምክንያት የሰው ልጅ ካለፈባቸው የችግርና የጦርነት ውጤት የቀሰመው አብይ መፍትሔ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ አብዛኞቹ ሀገራት በሕገ መንግሥታቸው ውስጥ ከሚያካትቱት መሠረታዊና ጥቅል ድንጋጌዎች መካከል የመንግሥት ሥልጣንና ተግባር፣ የዜጎች መሠረታዊ መብትና ግዴታ፣ የመንግሥት አስተዳደርና የሥልጣን ክፍፍል እንዲሁም የአሠራር ሁኔታ ይገኙበታል፡፡
Before the enactments of the Federal Administrative Procedure Proclamation, there is a gap in the Ethiopian legal regime due to the absence of administrative procedure law. This is a neglected subject both by the legal academia and practitioners. It is very difficult and challenges to talk about the history of administrative law in Ethiopia. Administrative law is still not well developed, and it is an area of law characterized by the lack of legislative reform.
Introduction
The federal court proclamation no 25/96 its amendment, which has been in force for many years, is repealed and replaced by the federal courts' proclamation number 1234/2021. When we see in view of the existing proclamation, the new law introduced new elements. In these short notes, we will briefly explore the new features of the proclamation and the reason behind the improvements of the proclamation to its current content.
ከሰሞኑ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍቺን በተመለከተ ለየት ያለ ውሳኔ ተሰጥቷል፡: ይህን ውሳኔ ለሕዝብ ይፋ ቢደረግ ጠቃሚ ሃሳብ እንዲሸራሸር ሊረዳ የሚችል ከመሆኑም በላይ ሕጉንም ለመፈተሸ ይረዳል በሚል አስተያየት ለአንባብያን ለማድረስ እሞክራለሁ፡፡ ጉዳዩ ይፋ ቢሆንም ይግባኝ ሊቀርብበት የሚችል በመሆኑ ለጊዜው የግለሰቦችን ስም ተቀይሯል፡፡ የጉዳዩ ዝርዝር ሁኔታውም ከዚህ በታች ባለው መልኩ ተቀምጧል፡፡
አቶ ሀ እና ወ/ሮ ለ 42 ዓመታት በትዳር ቆይተዋል፡፡ ትዳራቸውም የተደላደለ ነበር፡፡ በዚህ ትዳራቸው ጊዜ ውስጥ ልጅ ያልወለዱ ሲሆን አቶ ሀ ግን ከሌላ የወለዱት አንድ ወንድ ልጅ አላቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አቶ ሀ በእድሜ መግፋት (እድሜያቸው 90 ይሆናል) ምክንያት አእምሮአቸው ላይ ከፍተኛ ችግር የተከሰተ በመሆኑ የሚሰሩትን አያውቁም፡፡ የአእምሮ ችግሩን መሰረት በማድረግም የአቶ ሀ ልጅ ወላጅ አባቴ በአእምሮ ችግር የተነሳ የሚሰሩትን አያውቁም በማለት በፍርድ ይከልከሉ፤ የሞግዚትነት ስልጣንም ይሰጠኝ ሲል ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመለከቱ፡፡ ፍርድ ቤቱም የግለሰቡን የጤና ሁኔታ የሚያሳይ የሕክምና ማስረጃ እንዲቀርብ እና ግለሰቡም በችሎት ቀርበው ሁኔታቸው እንዲታይ በማድረግ ፍርድ ቤቱ ግለሰቡ በራሳቸው ራሳቸውንና ንብረታቸውን ለመቆጣጠር የማይችሉ መሆኑን ተገንዝቧል፡፡ ይህን ተከትሎም ፍርድ ቤቱ አቶ ሀ ላይ የክልከላ (Judicial Interdiction) ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በመቀጠልም የአቶ ሀ ልጅ አሳዳሪና ሞግዚት አድርጎ ሾሟቸዋል፡፡
የአቶ ሀ ልጅም ሞግዚትና አሳዳሪ የሚለውን ሹመት ካገኘ በኋላም ይህንን ሥልጣን መሰረት በማድረግ፣ ሞግዚት አድራጊዬ በእድሜ መግፋት ምክንያት በአእምሮአቸው ላይ የጤና መታወክ የተከሰተ ቢሆንም ተጠሪ ሊንከባከቧቸው አልቻሉም፤ ተለያይተው መኖር ከጀመሩም ረጅም ጊዜ ተቆጥሯል፡፡ ስለዚህ የሞግዚት አድራጊዬና የተጠሪ ጋብቻ እንዲፈርስ ይወሰንልኝ በማለት ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልክተዋል፡፡ ወ/ሮ ለ ሞግዚቱ የፍቺ ጥያቄ ይወሰንልኝ ጥያቄ ለማቅረብም ሆነ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለመከራከር አይችሉም፣ ለፍቺ የሚያበቃም ምክንያት የለም ሲሉ መቃወሚያና መልስ ሰጥተዋል፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትም፣ ሞግዚቱ ጋብቻ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ስልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም? የግራ ቀኙ ጋብቻ ሊፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚል ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምሮታል፡፡ አንደኛውን ጭብጥ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ሲተነትን
“… በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 370(1) መሰረት ሞግዚት አድራጊ ጋብቻ እንዲፈርስ ለመጠየቅ የሚችል መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ስለዚህ የአቶ ሀ ሞግዚት የሆኑት ልጃቸው ጋብቻው እንዲፈርስ ለመጠየቅ በሕግ ሥልጣን አላቻው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በወ/ሮ ለ የቀረበውን ሞግዚት አድራጊው ጋብቻ እንዲፈርስ ለመጠየቅ አይችሉም የሚል ክርክርን አልተቀበለውም፡፡”
የጉዳዩ መነሻ
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ በመዝገብ ቁጥር 78398 በአቶ ሽፈራዉ ደጀኔ እና ወ/ሮ ጸሀይ ተስፋዬ በአንድ በኩልና በአቶ ሲሳይ አበቡ በሌላ በኩል በተደረገ ሙግት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ጥቅምት 19 2005 የሰጠዉ ዉሳኔ ነዉ፡፡ ጉዳዩ የተጀመረዉ በወረዳ ፍርድ ቤት በአቶ ሲሳይ አበቡ ከሳሽነትና በአቶ ሽፈራዉ ደጀኔ እና ወ/ሮ ጸሀይ ተስፋዬ ተከሳሽ ነዉ፡፡ ከሳሹ እንደሚለዉ በእሱና በተከሳሹ መካከል ሐምሌ 17 2003 የተቋቋመ የቤት ሽያጭ ዉል አለ፡፡
መግቢያ
የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ክልከላ ይጥላል፡፡ በዚህ አጭር ጽሑፍ የደንቡን ህጋዊነት ለሕግ የበላይነት ያለውን መጥፎ ተምስሌትነት በርግጥ ሊፈታ ያሰበውን ችግር ለመፍታት ያለውን ፋይዳ በአጭር ባጭሩ ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡ አንባቢያንን ለተራዘመ እና አሰልቺ የንባብ ሂደቶች ላለመዳረግ ጉዳዩን በቀጥታና በጭሩ ለመዳሰስም ተሞክሯል፡፡
- መግቢያ
ሰዎች ንብረታቸውን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በተመለከተ አንድን ግዴታ ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸው ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መካከል ስምምነት ሲፈፅሙ ውል እንዳደረጉ ከኢትዮጵያ የፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 1675 መረዳት ይቻላል፡፡ አንድ ውል ከተደረገ በኋላ በአንደኛው ወይም በሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ላይ ግዴታን ይጥላል፡፡ ይህንን ግዴታ በተባለው ጊዜ አለመፈፀም ወይም ጊዜ ካልተቀመጠ ደግሞ ማዘግየት የሚያስከትለውን ኪሳራ በተመለከተ ተዋዋይ ወገኖች ገደብ ወይም ቅጣት ወይም አንድ የተወሰነ ወለድ ግዴታውን ያልፈፀመ ተዋዋይ ወገን ውሉን ላከበረው ወገን እንዲከፍል ሲዋዋሉ መመልከት ወይም በፍርድ ቤቶች ሲወሰን ማየት የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ወለድና የወለድ ወለድ (Interest on interest or compound interest) አስተሳሰብ ደንቦችን በተመለከተ እና ተያያዥ ጉዳዮችን የኢትዩጵያ ህጎች ላይ ተመስርተን በጨረፍታ እንደሚከተለው እንዳስሳለን፡፡
- ትርጓሜ
ወለድ የሚለውን ፅንሰ ሀሳብ ስንመለከተው አንድ ገንዘብ ያበደረ ሰው ተበዳሪው ብድሩን በመጠቀሙ ላበዳሪው ወገን በበኩሉ የሚከፍለው ወይም አንድ የባንክ ደንበኛ ያለውን ገንዘብ በአንድ ባንክ ገንዘብ ተቀማጭ ሲያደርግ በመቶኛ የሚታሰብ ገንዘብን የሚመለከት ወይም ተበዳሪ የወሰደውን ገንዘብ ወይም እቃ በወቅቱ ባለመመለሱ የተነሳ የሚከፈል የገንዘብ ካሳ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ወለድ ለገንዘብ ብድር ብቻ የሚከፈል ሳይሆን አንድ ግዴታን ባለመፈፀም ወይም በማዘግየት እና ይሄ ፍሬ ነገር ሲረጋገጥ የሚከፈል ጭምር ነው፡፡ በተጨማሪም ወለድ በስምምነት ወይም ያለስምምነት ማለትም በህግ አግባብ ሲወሰን ሊከፈል የሚችል ገንዘብ ነው፡፡ ለዚህ ፅሁፍ ዓላማ ሲባል በመቶኛ የሚታሰበውን ገንዘብን በሚመለከት ብቻ ያለውን እናያለን፡፡
የወለድ ወለድ ማለት በሚከፈል ወለድ ላይ በስምምነቱ ወይም በህግ መሰረት ወለዱን በወቅቱ ያልከፈለ ወገን በወለዱ ላይ የሚከፍለው ተጨማሪ የወለድ ወለድ እንደመቀጫ ያለ ገንዘብ ማለት ነው፡፡
ሰሞኑን የአቶ ጀዋር መሐመድን ኢትዮጵያዊ ዜግነት መልሶ የማግኘት ጉዳይ በኦፌኮ እና በምርጫ ቦርድ መካከል ክርክሮችን ማስነሳቱን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየሰማን እንገኛለን፡፡ በመሆኑም የዜግነት ሕጉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት መልሶ ስለማግኘት ስላሰቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች እና ዜግነት መልሶ ማግኘት ስለሚረጋገጥበት መንገድ ያለኝን መረዳት ለማካፈል ወደድኩኝ፡፡
አቶ ጀዋር መሐመድ አስቀድመው የኢትዮጵያ ዜጋ የነበሩ በመሆናቸው ነገር ግን በሕግ ዜግነታቸውን ከቀየሩ በኋላ መልሰው ዜግነታቸው እየጠየቁ በመሆኑ ለዚህ ጉዳይ ተገቢነት ያለው ድንጋጌ ስለዜግነት የሚደነግገው የአዋጅ ቁጥር 378/96 አንቀፅ 22 እና 23/2/ሐ ነው፡፡ በዚህ መሠረትም ኢትዮጵያዊ የነበረ ነገር ግን በሕግ የሌላ ሀገር ዜግነት ያገኘ ሰው የሚከተሉትን መሠረታዊ ጉዳዮች ከተሟሉ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን መልሶ ያገኛል፤
- አስቀድሞ ኢትዮጵያዊ የነበረ መሆኑ፤
- ወደኢትዮጵያ ተመልሶ በመምጣት መደበኛ መኖሪያውን በኢትዮጵያ ውስጥ ከመሠረተ፤
- ይዞት የነበረውን የሌላ ሀገር ዜግነት ከተወ፤
- ዜግነቱ እንዲመለስለት ለኢሚግሬሽን እና ስደተኞች ባለሥልጣን ካመለከተ፤
- ጥያቄው ለዜግነት ጉዳይ ኮሚቴ ቀርቦ በባለስልጣኑ ተቀባይነት ካገኘ፡፡
ከፍ ሲል በዝርዝር የተመለከቱ ጉዳዮች አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን መልሶ ለማግኘት ቅድመ ሁኔታዎች በመሆናቸው እና እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች የተሟሉ መሆን አለመሆናቸውን የማረጋገጥ እና የውሳኔ ሐሳብ የመሰጠት ሥልጣን ደግሞ የዜግነት ጉዳይ ኮሚቴ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 23/3 መሠረት የዜግነት ይመለስልኝ ጥያቄው በባለሥልጣኑ አማካኝነት ለኮሚቴው ቀርቦ ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ ለባለሥልጣኑ አቅርቦ መወሰን ይገባዋል፡፡