የወራሽነት ማረጋገጫ፣ መቃወሚያ እና ልጅነት፡- ክፍተተ ወሕግ ወአሰራር እና መፍትሔዎቻቸው

 

ስልጣን

የርዕሰ መዲናዋን አስተዳደር ለመመስረት በቻርተር ደረጃ የወጣው አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41(1) (ሸ) እና ማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 408/96 አንቀጽ 2 የወራሽነት ማረጋገጫን ጨምሮ ሌሎች ምስክር ወረቀቶች የመስጠት የስረ ነገር ስልጣንን ለአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ሰጥቷል። በዚህም መሰረት ከሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አምስት ዓመተ ምህረት ጀምሮ እስካሁን ድረስ እነዚህ ፍ/ቤቶች እገሌ የእገሌ ወራሽ ነው፣ አንቺ የእንትና ሚስት ነበርሽ፣ አንተ ደግሞ የእገሊት አበዋራ ነበርክ …….. ወዘተ እያሉ በሕግ ዓይን ህያው ይሆን ዘንድ በሞት የፈረሰን የዓይነ ስጋ ዝምድና በወረቀት ማረጋገጫ ሲቀጥሉ ኖረዋል።

Continue reading
  7366 Hits

የውርስ ኃብት ማጣራትን የተመለከቱ አንዳንድ ነጥቦች ከሰበር ውሳኔ ጋር ተገናዝቦ የቀረበ

መግቢያ

የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የተለየ ንብረት ይቆጠራል፡፡ ይህም ማለት የሟች ንብረት ከሌሎች ሰዎች ወይም ወራሾች ንብረት ጋር ሳይቀላቀል የባለቤትነት መብቱ ለወራሾች ሳይተላለፍ እንደ አንድ ልዩ ንብረት ሆኖ ሊያዝ እንደሚገባ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 942 ይደነግጋል፡፡

Continue reading
  18400 Hits

የውርስ ጉዳይን የተመለከቱ የይርጋ ገደቦች

መግቢያ

ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ባለመብት የሆነ ወገን መብቱን ለመጠየቅ ተገቢውን ትጋት ማድረግና የመብት ጥያቄውን ማቅረብ ያለበት ሲሆን ይሄን ሳያደርግ ቢቀር ግን መብቱ በይርጋ (በጊዜ ገደብ) ቀሪ የሚሆን ይሆናል የሚል ነው፡፡

Continue reading
  23907 Hits

ከውርስ ኃብት ክፍፍል ጋር የተያያዙ አንዳንድ ነጥቦች ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከሰጣቸው ውሰኔዎች ጋር በማገናዘብ የቀረበ

የሟች የውርስ ኃብት ተጣርቶ ከተዘጋ በኋላ የውርስ ኃብት ባለቤትነት ወደ ሟች ወራሾች ይተላለፋል፡፡ በመሆኑም ውርስ ከተዘጋ በኋላ ወራሾች መሀከል ክፍያ እስኪፈ...

Continue reading
  12622 Hits
Tags:

የውርስ ምንነት፣ የውርስ ዓይነቶች እና ወራሾችን ማጣራት በኢትዮጵያ የውርስ ሕግ

 

መግቢያ

የሰው ልጅ ወደዚች ምድር ከመጣበት /ከተወለደበት/ እለት አንስቶ እስከ ሕይወቱ ፍፃሜ ድረስ በዚች ምድር ላይ የሚኖረው ለተወሰነ ጊዜ ነው፡፡ የሰው ልጅ በዚች ምድር ላይ ዘላለማዊ አይደለም፡፡ ለያንዳንዱ ሰው በፈጣሪው የተጠው የምድር ቆይታ ጊዜ አለው፡፡ ይህ የምድር ላይ ቆይታው በአይቀሪው ሞት ይጠናቀቃል፡፡ የሰው ልጅ ወደዚች ምድር ከተቀላቀለበት እለት አንስቶ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ የሕግ መብት አለው፡፡

በዚች ምድር ላይ በቆይታው ጊዜው የሰው ልጅ የተለያዩ መብቶች እና ግዴታወች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ንብረት የማፍራት መብት የሚጠቀስ ነው፡፡ በእለት ተእለት ኑሮው የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ የራሱን ብሎም የቤተሰቡን ጉርስ ለመሸፈን ጥረት ያደርጋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የራሱ የሆነ ጥሪት ማፍራቱ አይቀሬ ነው፡፡ ይህን ጥሪት በምድር ላይ እስካለ ብቻ ነው የሚጠቀምበት፡፡ ሕይወቱ ካለፈች በኋላ ይህን ያፈራውን ንብረት በሕይወት ያሉ የሱ የቅርብ ሰዎች ናቸው የሚጠቀሙበት፡፡ እነዚህ በሕይወት ያሉ የሟችን ንብረት ሕይወቱ ካለፈ እለት በኋላ የሚጠቀሙበት በውርስ በመውረስ ነው፡፡ ውርስ የአንድ የሞተን ሰው ኃብትና ንብረት እንዲሁም ሊተላለፉ የሚችሉ መብትና ግዴታዎች ለአንድ ወይም ከአንድ በላይ ለሆኑ በሕይወት ላሉ ሰዎች የሚላለፋበት ሕጋዊ ሰርዓት ነው፡፡ ይህ ሰርዓት ደግሞ ሊያስከትል የሚችለው ሕጋዊ ውጤት ስለሚኖረው ራሱን የቻለ ሕግ ሊኖረው ይገባል፡፡

የሟችን ንብረት የሚወርሱት እንማንናቸው፣ ወራሽነትን የሚያሳጡ ነገሮች ምንድን ናቸው፣ ንብረቱ እንዴት ይከፋፈላል፣ ሟች ኑዛዜ ከተወ ኑዛዜው ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው ምን ምን መሟላት አለበት እና የመሳሰሉትን ነገሮች የሚመራው የሕግ ክፍል የወርስ ሕግ ይባላል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የሃገራችን የውርስ መሠረታዊ ጉዳዩች እንቃኛለን፡፡

Continue reading
  66371 Hits

ስለ ኑዛዜ ከውርስ ሕግና ከሰበር ውሳኔዎች ጋር ተገናዝቦ የቀረበ

 

 መግቢያ

የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ ኑዛዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ትርጉም ባይኖርም አንድ ኑዛዜ ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ምን ምን እንደሆኑ በዝርዝር የሚያስቀምጡ የሕግ ድንጋጌዎችን ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 857 እስከ 908 ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡

በዚህ ጽሁፍ ኑዛዜ በምን አግባብ ቢደረግ በሕግ ዘንድ ውጤት ይኖረዋል፤በውርስ ሕጋችን ላይ የተቀመጡት የኑዛዜ አደራረግ ስርዓቶች አስገዳጅነታቸው እስከምን ድርስ እንደሆነና ኑዛዜ በፍርድ ቤት ቢጸድቅ ሊያስገኝ የሚችለው ውጤትና ባለመጽደቁ የሚያመጣው ተጽእኖ ምን እንደሆነ ከውርስ ሕግ እና አስገጋጅ ከሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ውሳኔዎች አንጻር  በአጭሩ ዳሰሳ ለማድርግ ተሞክሯል፡፡ 

ለኑዛዜ ዋጋ መኖር አስፈላጊ የሆኑ የስረ ነገር ሁኔታዎች    

Continue reading
  9742 Hits