Several individuals or groups known as parties to the crime may play a distinct role in committing international crimes. The involvement of some of them in the commission of the crime is so close, direct, and active. These persons impose greater danger to society as a whole. The participation of others in the commission of international crime may be indirect by incitement and conspiracy. It supports and legitimizes acts of violence and Persecutory measures against victims. A review of mass crimes, both from the past and the present reveals that incitement and conspiracy generally precede and accompany mass crimes such as genocide, persecution, and extermination.
Akka qajeeltootti seerri murtiin dirqisiisaa irratti kenname yoo haqame dhimmoota walfakkaatoo booddee jiraniif bu’aa dirqisiisummaa kan hin qabneedha. Fakkeenyaaf labsii Seera HH fooyyeessuuf bahe lakk. 639/2001 bahe qabeenya hin sochoone baankiif ykn dhaabbilee faayinaansiitiif liqiif akka wabiitti qabsiifame ilaalchisee mana murtiitti ykn qaama waliigaltee raawwachiisu fuulduraatti mallatta’uun barbaachisaa akka hin taanee tumuun SHH kwt 1723 jalatti akka haalduree kaa’ee walakkaadhaan hambisee jira. kanaafuu murtiileen kan dura SHH kwt 1723 irratti hundaa’uun qabeenya hin sochoone qabsiisuun walqabatee murtiileen dirqisiisaa kennaman hafaa ta’u.
የማታለል ወንጀል ከእምንት ማጉደል ወንጀል በምን ይለያል? በድንጋጌዎቹ የወንጀል ክስ ለማቅረብ በመሰረታዊነት መሟላት ያለባቸው የማስረጃ አይነቶችስ ምንድናቸው?
በወንጀል የሚጠረጠሩ ሰዎችን በፍርድ ቤት በመክሰስ ለማስቀጣት በቂና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረጃ አቅርቦ ማስረዳት በዐ/ህግ በኩል ይጠበቃል፡፡ የተለያየ አይነት ማስረጃን የመመዘን መርህ በወንጀል ክስ ለመክሰስና ጥፋተኛ ለማለት በስራ ላይ የሚውል ቢሆንም በጥቅሉ ሶስት አይነት የማስረጃ አመዛዘን መርህ በስፋት ይታያል፡፡
“በሕግ አምላክ” ካለ ሀገሬው ውልክፍ የለም፡፡ ሕግ የማኅበረሰብ የውል ገመዱ ነው፡፡ ሕግ የአንድ ሃገር ባህል፣ ልማድ፣ የኑሮ ዘይቤ ካስማና ባላ ነው፡፡ ሕግ ያለ ሰው፣ ሰው ያለ ሕግ ምሉዕነት የለውም፡፡ ሕግ ፈራጅ ነው በዳዩን ይቀጣል፤ ተበዳዩን ይክሳል፡፡ ሕግ አድራጊ ፈጣሪ ነው ይሾማል፤ ይሽራል፡፡ ሕግ ለጋስም ንፉግም ነው ይሰጣል፤ ይነሳል፡፡ ሕግ የእግር ብረት ሆኖ እግር ከወረች ያስራል፤ ሕግ ቁልፍ ሆኖ ይፈታል፡፡ ሕግ መንገድ ነው ያገናኛል፤ ያለያያል፡፡ሕግ ወረትን አያዉቅም፤ሕግ ዘላቂነትን የሚያልም የሩቅ ተጓዥ ነዉ፡፡ ሕግ አዉጪዎች ካልባለጉ ሕግ አይባልግም፡፡ ሕግ እንደ ፈጣሪ አይደለም፤ መረን የሚለቀዉ ሲመቸን የምናከብረዉ ሳይመቸን የምንጥሰዉ አድርግን ያወጣነዉ ቀን ነዉ፡፡
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነው ጸሐፊው በሥራ ምክንያት በሚያያቸው መዝገቦች ስር ሲገጥሙት የነበሩ ክርክሮች እንዲሁም በተለያዩ አጋጣሚዎች ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ጋብቻ ከፍርድ ቤት ውሳኔ ውጭ በሁኔታዎች ስለሚፈርስበት አግባብ ያደረጋቸው ውይይቶች ሲሆኑ በዋነኛነት ግን የቅርብ ምክንያቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ ነው። በፌደራሉ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 75 ሥር እንደተመለከተው ጋብቻ የሚፈርስባቸው ብቸኛ ሦስት ምክንያቶች ሞት ወይም የመጥፋት ውሳኔ፤ ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ካለባቸው ሁኔታዎች አንዱ በመጣሱ ምክንያት ጋብቻው እንዲፈርስ ሲወሰን እንዲሁም ፍቺ መሆናቸው የተመለከተ ሲሆን በአንቀጽ 117 ሥር እንደተመለከተው ደግሞ ጋብቻን በፍቺ ለማፍረስ ሥልጣን የተሰጠው ለፍርድ ቤቶች ብቻ ነው።
ይህ ፅሑፍ “የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሰረተ-ሐሳቦች” ከሚለው 3ኛ ዕትም መፅሐፍ በ9ኛ ምዕራፍ ላይ የተከተበ ሲሆን በዚህ መፅሐፍ በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዕትም ምዕራፍ 9 ተብሎ የነበረውን በአዲስ መልክ የውርስ ጉዳይ ይርጋዎችን በማዋቀር በመፅሐፉ ተሰንዷል፡፡ በምዕራፍ 9 ላይ ከተቃኙ ከ20 በላይ የሆኑ የውርስ ይርጋ ጉዳዮች መካከል ለቅምሻ ያክል በጣም ጥቂቶቹን ማለትም ሶስት ጉዳዮች ብቻ እነሆ ጀባ ብያለሁኝ፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ መፅሐፉ በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) ተከትሎ የተጻፈ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ፅሑፍ በበየነ-መርብ በሚለቀቅ በድህረ-ገፅ ላይ የሚነበብ በመሆኑ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ለአንባቢዎች ይህንን ፅሑፍ ሲያነቡ በሚመች አግባብ የማጣቀሻ ሁኔታዎች ከመፅሐፉ ከነበረው በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) በተለየ መልኩ የተቀመጡ ለመሆኑ ለማሳሰብ እወዳለሁኝ፡፡
ይህ ፅሑፍ “የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሰረተ-ሐሳቦች” ከሚለው 3ኛ ዕትም መፅሐፍ በ10ኛ ምዕራፍ ላይ የተከተበ ሲሆን በዚህ መፅሐፍ በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዕትም ያልነበር ነው፡፡ በዚህ መፅሐፍ በ3ኛ ዕትም በምዕራፍ 10 ላይ ከተነሱ በርካታ ጉዳዮች መካከል ጥቂቶቹን ብቻ እነሆ ጀባ ብያለሁኝ፡፡
ማሳሰቢያ ይህ ፅሑፍ በመፅሐፉ በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) ተከትሎ የተጻፈ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ፅሑፍ በበየነ-መርብ በሚለቀቅ በድህረ-ገፅ ላይ የሚነበብ በመሆኑ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ለአንባቢዎች ይህንን ፅሑፍ ሲያነቡ በሚመች አግባብ የማጣቀሻ ሁኔታዎች ከመፅሐፉ ከነበረው በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) በተለየ መልኩ የተቀመጡ ለመሆኑ ለማሳሰብ እወዳለሁኝ፡፡
በኢትዮጵያ የታክስ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የተርን ኦቨር ታክስን በመጠቀም ከሕግ አገልግሎት ሽያጭ ላይ ታክስ እንደሁኔታው በፌዴራሉ እና በክልል መንግሥታት በመጣሉ በተግባርም እየተሰበሰበ ይገኛል። ይሁን እንጅ ይህ ታክስ ሕጋዊ መሠረቱን እና አግባብነቱን በተመለከተ፤ ከታክስ መሠረቱ፣ ከታክስ ምጣኔው እና ከአስተዳደር ሂደቱ ጋር ተያይዞ በርካታ አዙሪት ጥያቄዎችና መውሰብስቦች ይስተዋላሉ፡፡ የዚህ ጥናት ዓላማም አነዚህን አዙሪት ጥየቄዎችና መውሰብስቦች በዓይነታዊ የምርምር ዘዴ በማጥናት የመፍትሔ ኃሳብ መጠቆም ነው፡፡ ለዚህም ያስችል ዘንድ የተለያዩ መዛግብቶች፣ ቃለመጠይቆችና ቡድንተኮር ውይይቶች በግብዓትነት ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን ለንፅፅር ይረዳ ዘንድ የሌሎች አገራት ተሞክሮንም ለመቃኘት ተሞከሯል፡፡ በዚህም መሠረት ጥናቱ ባለሶስት አማራጭ የመፍትሔ ኃሳብ ያቀረበ ሲሆን የመጀመሪያው አሁን ከሕግ አገልግሎት በአገሪቱ እየተሰበሰበ ያለውን የሽያጭ ታክስ እንዳለ በማስቀጠል ለፍትሕ ተደራሽነትና ለሕገመንግስታዊ መብቶች መከበር ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር መወሰድ ያለባቸውን ርምጃዎች አመላክቷል፡፡
በሰዎች የእለት ከዕለት መስተጋብር ዉስጥ ከሚፈጠሩ ነገሮች መካከል አንዱ ቅራኔ ነዉ። ቅራኔ ሲኖር ደግሞ የመረጃ ወይም ማስረጃ ጉዳይ አብሮ ይነሳል። በተለይ ለዳኝነት አካላት ማለትም ለፍርድ ቤት፤ ለግልግል እና ለመሳሰሉት በሚቀርቡ ክርክሮች ላይ ማስረጃን ወይም መረጃን የሚመለከቱ ጉዳዮች መነሳታቸዉ አይቀሬ ናቸዉ። እዚህ ላይ የመረጃ እና ማስረጃን ልዩነት መረዳት ተገቢ ነዉ። ማስረጃ አንድን አከራካሪ ፍሬ ጉዳይ ለማረጋገጥ ወይም ለማስተባበል የሚቀርብ ተጨባጭ ጉዳይ ሲሆን፤ መረጃ ግን አንድን ነገር ለማረጋገጥ ወይም ለማስተባበል የሚሰጥ መግለጫ (Information) ብቻ ነዉ። ሁሉም ማስረጃ የመረጃነት ባህሪ ያለዉ ሲሆን፤ ሁሉም መረጃ ግን ማስረጃ አይደለም። ማስረጃ ለፍትሕ አካል የሚቀርብ መረጃ ሲሆን፤ ይህ መረጃም ፍሬ ነገርን የሚመለከት ነዉ። ፍሬ ነገር ማለትም በፍርድ ቤት ወይም በሌላ የዳኝነት አካል ፊት አከራካሪ ሆኖ የወጣ እና የተያዘ ጭብጥን የሚመለከት ነዉ። ማስረጃ የሚቀርበዉም ይህንን አከራካሪ ጭብጥ ወይም ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ ወይም ለማስተባበል ነዉ። የማስረጃ ሕግ ተፈጻሚነት የሚታየዉም በዚህ ጊዜ ነዉ።
Introduction
Criminal reinstatement (simply reinstatement) also known as “Expungement” or “Expunction” in the common law legal system is a legal process that allows individuals with criminal records to have their convictions removed from public records. This means that the records are destroyed; making them inaccessible to organizations that may conduct background checks. Reinstatement is a concept included in our criminal code and criminal procedure code, but the law and its details are hardly known in our society. As a result, it is not widely used. This paper explores the concept of reinstatement, its difference from pardon, the eligibility criteria, the process involved, its relevance in helping individuals reestablish their lives following a conviction, and the impact it has on individuals and society as a whole. It also highlights the gaps in the current practice of criminal reinstatement and concludes with recommendations for improvements.