ካሴ መልካም - Blog

ጸሐፊው የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሠረታዊ ሀሳቦች በሚል መጽሐፍ አሳትሞ ለአንባቢ ያበቃ ሲሆን በሕግ የመጀመሪያ ድግሪ እንዲሁም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋና ዳኝነት ከሰባት ዓመት በላይ በማገልገል ይገኛል። 

የመድህን እና የማጓጓዣ ሕግ ይርጋ
ካሴ መልካም
Insurance Law Blog
ይህ ጽሑፍ በቀጥታ የተወሰደው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች ከሚለው ተሻሽሎ ከታተመው መጽሐፍ ላይ ነው። ሆኖም ለዚህ የበየነ-መረብ ጽሑፍ ለንባብ እንዲመች በግርጌ ተቀምጠው የነበሩት ማጣቀሻዎች በፅሑፉ ውስጥ እንዲከተቱ ተደርጓል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 166/1952 ከ50 ዓመታት በላይ ያገለገለ ቢሆንም በከፊል በአዋጅ ቁጥር 1243/2013 የተሸሻለ/የተተካ/ ቢሆንም የድሮው የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 166/1952 ውስጥ መጽሐፍ 3 (ሦስት) ማለትም ከአንቀጽ 561 እስከ 714 እና መጽሐፍ 4 (አራት) ማለትም ከአንቀጽ 715 እስከ 967 ያሉ ድንጋገጌዎች ያልተሻሩ ለመሆኑ በአዲሱ የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 በመግቢያው አንቀጽ 3(3) ላይ በግልፅ ተደንግጓል። ስለዚህ የንግድ ሕግ ይርጋዎች በአዲሱ ሕግ እና በድሮው ሕግ ያልተሻሩ ድንጋጌዎችን ከሰበር አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ጋር በመጽሐፉ በጥልቀት ተዳሷል።
Continue reading
በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ትኩረት የሚሹ አወዛጋቢ ነጥቦችና መፍትሔዎቻቸው
ካሴ መልካም
About the Law Blog
ማስታዎሻ፡- ውደ አንባቢያን ይህ ጽሑፍ የተወሰደው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች በሚል ከታተመው በ2017 ዓ.ም ተሻሻሎ በቀረበው መጽሐፌ ላይ ሲሆን የግርጌ ማስታዎሻዎቹ እና ማጣቀሻዎቹ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ለንባብ በሚመች አግባብ እንደገና ተቀናጅተው ተሰርተዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የተካተቱት አብዛኛዎቹ ነጥቦች አወዛጋቢ ሆኖም በሕግ ባለሙያው ብዥታ እና ልዩነት የሚፈጥሩ ነጥቦች በመጽሐፉ የመጀመሪያ ዕትም ያልነበሩ አሁን ላይ በችሎት በሚገጥሙ ክርክሮች ሰበር ጭምር መፍትሔ የሰጣቸውን እና ሰበር መፍትሔ ያልሰጠባቸውን ደግሞ የመጽሐፉ አዘጋጅም የራሱን ምልከታ እና መፍትሔ የሚላቸውን ሃሳቦች ያሰቀመጠባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡
Continue reading
በይርጋ የማይታገዱ የውርስ ጉዳዮች እና ከኑዛዜ ጋር የተያያዙ ይርጋዎች
ካሴ መልካም
Succession Law Blog
ይህ ፅሑፍ “የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሰረተ-ሐሳቦች” ከሚለው 3ኛ ዕትም መፅሐፍ በ9ኛ ምዕራፍ ላይ የተከተበ ሲሆን በዚህ መፅሐፍ በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዕትም ምዕራፍ 9 ተብሎ የነበረውን በአዲስ መልክ የውርስ ጉዳይ ይርጋዎችን በማዋቀር በመፅሐፉ ተሰንዷል፡፡ በምዕራፍ 9 ላይ ከተቃኙ ከ20 በላይ የሆኑ የውርስ ይርጋ ጉዳዮች መካከል ለቅምሻ ያክል በጣም ጥቂቶቹን ማለትም ሶስት ጉዳዮች ብቻ እነሆ ጀባ ብያለሁኝ፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ መፅሐፉ በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) ተከትሎ የተጻፈ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ፅሑፍ በበየነ-መርብ በሚለቀቅ በድህረ-ገፅ ላይ የሚነበብ በመሆኑ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ለአንባቢዎች ይህንን ፅሑፍ ሲያነቡ በሚመች አግባብ የማጣቀሻ ሁኔታዎች ከመፅሐፉ ከነበረው በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) በተለየ መልኩ የተቀመጡ ለመሆኑ ለማሳሰብ እወዳለሁኝ፡፡
Continue reading
በፍርድ ቤት አወዛጋቢ የሆኑ የውርስ ጉዳዮች እና መፍትሔዎቻቸው
ካሴ መልካም
Succession Law Blog
ይህ ፅሑፍ “የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሰረተ-ሐሳቦች” ከሚለው 3ኛ ዕትም መፅሐፍ በ10ኛ ምዕራፍ ላይ የተከተበ ሲሆን በዚህ መፅሐፍ በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዕትም ያልነበር ነው፡፡ በዚህ መፅሐፍ በ3ኛ ዕትም በምዕራፍ 10 ላይ ከተነሱ በርካታ ጉዳዮች መካከል ጥቂቶቹን ብቻ እነሆ ጀባ ብያለሁኝ፡፡ ማሳሰቢያ ይህ ፅሑፍ በመፅሐፉ በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) ተከትሎ የተጻፈ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ፅሑፍ በበየነ-መርብ በሚለቀቅ በድህረ-ገፅ ላይ የሚነበብ በመሆኑ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ለአንባቢዎች ይህንን ፅሑፍ ሲያነቡ በሚመች አግባብ የማጣቀሻ ሁኔታዎች ከመፅሐፉ ከነበረው በሕግ የሚጻፉ ጉዳዮችን የማጣቀሻ ሥነ-ሥርዓት (based on legal citation rule) በተለየ መልኩ የተቀመጡ ለመሆኑ ለማሳሰብ እወዳለሁኝ፡፡
Continue reading