የተሸከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ሕግ በኢትዮጵያ

 

መግቢያ

በሀገራችን ኢትዮጵያ የተሸከርካሪ አደጋእጅጉን እየበዛ እና ከፍተኛ የሆነ የሞትና የንብረት ጉዳት እያስከተለ ይገኛል፡፡ የበርካቶች ህይወት አጥፍቷል፣ አካል አጉድሏል እንዲሁም ንብረት አውድሟል። ሁልግዜ በየማለዳው በራዲዮ የምንሰማቸው የትራፊክ ዘገባዎችም እጅግ ዘግናኝ እና ሁላችንንም የሚያስደነግጥ፣ የህሊና እረፍት የሚነሳ እና ወቶ የመግባት ዋስትናችንን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከት ወደመሆን ደርሶል፡፡ ችግሩ እጅግ አሳሳቢ እና አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ ጉዳት አደራሾቹ በአደጋው ተጋላጭ ለሆኑት ግለሰቦች እርዳታ ከመስጠት ወይም እርዳታ እንዲያገኙ እና ህይወታቸው እዲተርፍ ከማድረግ ይልቅ ጉዳቱን አድርሰው የሚሰወሩ መሆናቸው ነው፡፡

በተሸከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች አንድም ጉዳት አድራሹ ባለመታወቁ በሌላ በኩል ደግሞ ጉዳቱን አድራሹ ቢታወቅም ጉዳቱን ያደረሰው ተሽከርካሪ የመድን ሽፋን የሌለው በመሆኑ ተጎጂዎቹን ለባሰ ስቃይ እና እንግልት የሚዳርጋቸው ጉዳይ ነው፡፡

ከእንዲህ ያለን ችግር ለማቃለል የተሸከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ሽፋን አስገዳጅ በሆነ መልኩ በሕግ ተደንግጎ መኖር እጂጉን ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡  በመሆኑም በሀገራችን ለዚህ ችግር መፍትሔ ሊሆን የሚችል ሕግ ወጥቶ በሥራ ላይ ውሎ ይገኛል፡፡ የተሸከርካሪ አደጋ የሦስተኛ  ወገን መድን አዋጅ ቁጥር 799/2002 በአሁኑ ሰዓት በሥራ ላይ የሚገኝ ሕግ ነው፡፡ የሕጉን ይዘት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ጽሑፍ በዝርዘር እንመለከተዋለን፡፡

Continue reading
  21594 Hits

የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥብቃ በኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ

 

መግቢያ

የሥነ ጽሑፍ፣ የኪነ ጥበብ፣ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች እና ተመሳሳይ የፈጠራ ሥራዎች የአንድ ሀገር ባህላዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ ልማትን በማፍጠን ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወቱ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም የዚህ ሥራ ፈጣሪዎች የሚበረታቱበትንና አዳዲስ ፈጠራዎችን የሚያበረክቱበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡

የሥነ ጽሑፍ፣ የኪነ ጥበብ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች እና ተመሳሳይ የፈጠራ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በሚከናወኑ ሥራዎች ላይ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች በሕግ እውቅና መስጠትና ጥበቃ ማድረግ አዳዲስ ፈጠራዎች እንዲበራታቱ እና የሚጠበቅባቸውን በህላዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ እድገት በኅብረተሰቡ ውስጥ እንዲያመጡ እንዲሁም የፈጠራው ባለቤቶች ከሥራቸው እንዲጠቀሙ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

የኢ... ሕገ መንግሥት አንቀጽ 91(3) ላይ መንግሥት አቅም በፈቀደ መጠን ኪነ ጥበብን፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የማስፋፋት ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በዚሁ መሠረት  መንግሥትም የቅጅና ተዛማጅ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር ይረዳው ዘንድ አዋጅ ቁጥር 410/1996 በማውጣት ሥራ ላይ አውሎ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ሁል ጊዜ እያደጉ እና እየተለዋወጡ የሚሄዱ በመሆናቸው በአዋጅ ቁጥር 410/1996 ላይ የተወሰነ ማሻሻያና ጭማሪ በማስፈለጉ ይህ አዋጅ በአዋጅ ቁጥር 872/2007 ማሻሻያ አድርጎ በሥራ ላይ አውሏል፡፡ ይህም መሆኑ ከአለም እና ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር ለመራመድ ያስችላል፡፡

Continue reading
  14136 Hits
Tags:

የውርስ ምንነት፣ የውርስ ዓይነቶች እና ወራሾችን ማጣራት በኢትዮጵያ የውርስ ሕግ

 

መግቢያ

የሰው ልጅ ወደዚች ምድር ከመጣበት /ከተወለደበት/ እለት አንስቶ እስከ ሕይወቱ ፍፃሜ ድረስ በዚች ምድር ላይ የሚኖረው ለተወሰነ ጊዜ ነው፡፡ የሰው ልጅ በዚች ምድር ላይ ዘላለማዊ አይደለም፡፡ ለያንዳንዱ ሰው በፈጣሪው የተጠው የምድር ቆይታ ጊዜ አለው፡፡ ይህ የምድር ላይ ቆይታው በአይቀሪው ሞት ይጠናቀቃል፡፡ የሰው ልጅ ወደዚች ምድር ከተቀላቀለበት እለት አንስቶ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ የሕግ መብት አለው፡፡

በዚች ምድር ላይ በቆይታው ጊዜው የሰው ልጅ የተለያዩ መብቶች እና ግዴታወች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ንብረት የማፍራት መብት የሚጠቀስ ነው፡፡ በእለት ተእለት ኑሮው የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ የራሱን ብሎም የቤተሰቡን ጉርስ ለመሸፈን ጥረት ያደርጋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የራሱ የሆነ ጥሪት ማፍራቱ አይቀሬ ነው፡፡ ይህን ጥሪት በምድር ላይ እስካለ ብቻ ነው የሚጠቀምበት፡፡ ሕይወቱ ካለፈች በኋላ ይህን ያፈራውን ንብረት በሕይወት ያሉ የሱ የቅርብ ሰዎች ናቸው የሚጠቀሙበት፡፡ እነዚህ በሕይወት ያሉ የሟችን ንብረት ሕይወቱ ካለፈ እለት በኋላ የሚጠቀሙበት በውርስ በመውረስ ነው፡፡ ውርስ የአንድ የሞተን ሰው ኃብትና ንብረት እንዲሁም ሊተላለፉ የሚችሉ መብትና ግዴታዎች ለአንድ ወይም ከአንድ በላይ ለሆኑ በሕይወት ላሉ ሰዎች የሚላለፋበት ሕጋዊ ሰርዓት ነው፡፡ ይህ ሰርዓት ደግሞ ሊያስከትል የሚችለው ሕጋዊ ውጤት ስለሚኖረው ራሱን የቻለ ሕግ ሊኖረው ይገባል፡፡

የሟችን ንብረት የሚወርሱት እንማንናቸው፣ ወራሽነትን የሚያሳጡ ነገሮች ምንድን ናቸው፣ ንብረቱ እንዴት ይከፋፈላል፣ ሟች ኑዛዜ ከተወ ኑዛዜው ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው ምን ምን መሟላት አለበት እና የመሳሰሉትን ነገሮች የሚመራው የሕግ ክፍል የወርስ ሕግ ይባላል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የሃገራችን የውርስ መሠረታዊ ጉዳዩች እንቃኛለን፡፡

Continue reading
  58024 Hits

የጋብቻ እና ፍቺ ሕጋዊ ውጤቶች ከተሸሻለው የቤተሰብ ሕግ አንፃር

 

መግቢያ

የሰው ልጆች በዚህ ምድር ላይ መኖር የጀመሩትና ማህበራዊ መስተጋብር እንድ ህብረተሰብ ክፍል ብሎም እንደ ሀገር መኖር የጀመሩበት ጊዜ እና ቦታ ላይ የታሪክ ሊቃውንት በእርግጥ ይሄ ጊዜና ቦታ ባይሉንም ረጅም ዘመናትን እንዳስቆጠሩ ይገልፃሉ፡፡ የአንድ ሀገር ወይም ማህበረሰብ መሠረት የሆነው ቤተሰብ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ የሕብረተሰብ መሠረት የሆነው ቤተሰብ የሚመሰረተው በተለያየ መልኩ ቢሆንም ዋናው ግን የህብረተሰቡ አካል የሆኑት ሰዎ (ወንድ እና ሴት) በሚፈጸሙት ጋብቻ ነው፡፡ ቤተሰብ የህበረተሰቡ ዋና መሶሶ በመሆኑ ትልቅ ቦታና ከበሬታ የሚሰጠው ነው፡፡ ይህ ትልቅ ቦታና ከበሬታ የሚሰጠው የህብረተሰቡ መሠረት የሆነ ተቋም እንደ ተቋም ከመቋቋሙ አንስቶ እስከ መጨረሻው ጊዜው ድረስ በሕግና እና ስርዓት መመራት ይኖርበታል፡፡ የቤተሰብ መመስርቻ የሆነው ጋብቻ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ኖሮት እንዲዘልቅ ህብረተሰቡ ባወጣው ሕግ መሠረት መመሥረት ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም በቆይታው ጊዜ የሚፈጠሩትን ግንኝነቶችና ውጤቶች እንዲሁም በሕግ መሠረት ከለላ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ለምሳሌ ያህል የልጅ አስተዳደግና አስተዳደር፣ በትዳር ውስጥ ስለሚፈጠሩ ንብረቶች፣ ከትዳር በፊት የነበሩ ንብረቶች፣ በባልና ሚስት መሀል ስለሚኖረው ግለሰባዊ ግንኙነቶች፣ በዚህ ትዳር ውስጥ ሆኖ ማድረግ ስለተከለከሉ ነገሮች እና ወዘተ የመሳሰሉት በሕግ መሠረት መደንገግ ይኖርባቸዋል፡፡

ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ይህን የህብረተሰብ ምሰሶ የሆነውን ትዳር (ቤተሰብ) ሊያፈርሱት ይችላሉ፡፡ ይህ በሕግ መሠረት የተቋቋመው ተቋም በሕግ መሠረት ሕጋዊ በሆነ መልኩ ነው መፍረስ ያለበት፡፡ ፍቺ በሕጉ መሠረት በመፈጸም ትዳር ሲፈርስ የራሱ የሆነ ሕጋዊ ውጤት ይኖረዋል፡፡ የልጆች ቀለብ በትዳር ውስጥ የፈሩ ንብረቶች አከፋፈል ወዘተ በሕግ መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡

በዚህ ጽሑፍ ውስጥም የጋብቻና ፍቺ ሕጋዊ ውጤቶቻቸው ከቀለብ መስጠት፣ ንብረት ግንኙነት (Pecuniary effect) እና ግላዊ የተጋቢዎቹ ግንኙነት (personal effect) ላይ በማተኮር በአሁኑ ሰዓት በፌዴራል መንግስት ደረጃ የወጣውን የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ ዙሪያ ያለውን የሕግ ማዕቀፍ እና አተገገባበሩ ላይ ትኩረት በማድረግ የሚዳሰስ ይሆናል፡፡

Continue reading
  55210 Hits