የኢትዮጵያ የብር ኖቶችና የባንኮች አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓተ-ልማድ ከአካል-ጉዳተኞች መብት አንጻር  

መግቢያ

በሀገራችን ከ20 ሚሊዮን  በላይ የአካል ጉዳት ያለባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደማንኛውም ሰው የተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት አገልግሎቶችን ለመጠቀም የተለያዩ መሰናክሎች ይገጥሟቸዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ አካል-ጉዳተኞች በኢትዮጵያ የብር ኖቶች አጠቃቀም እና በባንክ አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ከሕግ እና ከአሰራር አንጻር እንዳስሳለን፡፡

Continue reading
  7170 Hits

Major Departures of the New Micro-Finance Business Proclamation

 

Unlike the mainstreaming financial institutions, microfinance institutions play an important role in providing access to finance for rural farmers, small businesses, and other people who are engaged in similar activities, and hence, it was necessitated to have a legal framework to govern this issue i.e., Proclamation No. 626/2009. However, for a variety of reasons the existing proclamation needs amendment and the lawmakers came up with a new proclamation, Proclamation No. 1164/2019 (‘the new proclamation’), which introduces some innovative concepts to the existing proclamation. Therefore, in this piece, I will display some of the fundamental issues which are introduced in the new amending Proclamation. 

 

The existing Proclamation defines ‘company’ as a share company in which capital is fully owned by Ethiopian nationals and hence, it clearly excludes foreign nationals of Ethiopian origin. As part of the policy shift however, the new Proclamation expands the meaning of ‘company’ as a share company as defined under the Commercial Code in which capital is fully owned by Ethiopian or Foreigners of Ethiopian origin (diaspora) or jointly owned by the Ethiopian and Foreigners of Ethiopian origin. Even though the company is registered in another country, as far as its capital is contributed by Ethiopian or Foreigners of Ethiopian origin, as stated under Proclamation No. 270/2002, the law still recognizes it as a ‘company’. Still and all, the new Proclamation excluded foreigners from the microfinance business. 

 

Continue reading
  6300 Hits

የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን በዋስትና በማስያዝ ብድር የመስጠት የባንኮች ኃላፊነት

 

 

መግቢያ

በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ባንኮችና አበዳሪ የገንዘብ ተቋማት ብድር ለማበደር እንደመያዣነት ከሚመርጧቸው ንብረቶች መካከል በዋናነት የማይንቀሳቀስ ንብረት (ማለትም ህንጻዎችንና ቤትን) እንዲሁም ከተንቀሳቃሽ ንብረቶች ውስጥ ደግሞ መኪናን እንዲሁም ትላልቅ ማሽነሪዎችን ብቻ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ በዚህም በተለይም አበዳሪ ባንኮች በዋናነት በቀላሉ ብድራቸውን ማስመለስ የሚችሉት በቀላሉ ሊጠፉ የማይችሉ ንብረቶችን በመያዣነት በመያዝ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታም በተለይም ተበዳሪዎች የብድር ገንዘብ አግኝተው የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ለመሳተፍ እና ለኢኮኖሚው እድገትም አስተዋጽኦ ከማድረግ አንጻር ሁኔታው አዳጋች እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ በዚያው ልክም የብድር አቅርቦት ውስኑነትም ባንኮች ብድርን በሰፊው ላለማቅረባቸው ሌላው ምክንያት ነው፡፡

አሁን በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ በነጋሪት ጋዜጣ የታተመው የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን በዋስትና በማስያዝ ብድር ለመበደር የሚያስችል አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1147/2011 (pdf)) (አዋጅ ቁጥር 1147/2011 በነጋሪ መተግበሪያ) በቅርቡ በስራ ላይ እንዲውል ታትሟል፡፡ በተለይም አዋጁ የያዛቸውና የሚያተኩርባቸው ነጥቦች ለአበዳሪ ባንኮችም ጭምር አዲስ በመሆናቸው አዋጁን የሚጠቀሙት አስፈጻሚዎችም ሆኑ የባንክ ባለሙያዎች እንዲሁም ከዚህ አዋጅ ተጠቃሚ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለአዋጁ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ውስብስብነት የሚታይበትን ይህንኑ አዋጅ መሰረታዊ ነጥቦቹን ለማስገንዘብ ከፍኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ከዚህ በዘለለም አዋጅ የያዛቸው ሀሳቦች አዳዲስና ውስብስብ በመሆናቸው አዋጁ ላይ ግንዛቤ ካልተፈጠረ አዋጁ ከመውጣቱ ውጪ ተግባራዊነቱ እጅግ ከባድ እንደሚሆን የአዋጁን ይዘት በመመልት በቀላሉ መናገር ይቻላል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጽሑፍ ስለአዋጁ እና በባንኮች እንደት ሊፈጸም እንደሚችል እንዲሁም የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ሲባል ምን ምንን ያካትታል፤ በዚህ አዋጅ ተጠቃሚ ለመሆን ምን ምን ጉዳዮችን ማማላት ያስፈልጋል፤ የአዋጁ ዋነኛ ትኩረት ምንድን ነው የሚሉና ሌሎች መሰረታዊ ነጥቦችን ጠቅለል ባለ መልኩ ዳሰሳ ተደርጎባቸዋል፡፡

Continue reading
  10151 Hits

የኤቲኤም ካርድ በጠፋ ጊዜ የባንክ ኃላፊነት

 

በዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ክፍያን ከሚያሳልጡ አሠራሮች መካከል አንዱ የኤቲኤም ካርድ አገልግሎት ነው፡፡ አንድ የባንክ ደንበኛ በባንኩ ውስጥ በከፈተው ሒሳብ ያጠራቀመውን ገንዘብ ለማውጣት የቁጠባ ሒሳብ ደብተሩን መያዝ፣ የባንክ ባለሙያን ማነጋገር፣ ገንዘብ ወጪ ለማድረግ የሚያስችል ፎርም መሙላት፣ ወረፋ መጠበቅ ወዘተ. አይጠበቅበትም፡፡ በደንበኛውና በባንኩ መካከል በሚፈጸም የኤቲኤም ካርድ አገልግሎት ውል ከባንኩ ካርዱንና የሚስጥር ቁጥሩን በመቀበል ባንኩ በተለያዩ ቦታዎች ካስቀመጣቸው የኤቲኤም ማሽኖች አገልግሎት ማግኘት ይችላል፡፡ በአገራችን ይህ አሠራር በተግባር ላይ ከዋለ የተወሰኑ ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ በጣም ውሱን ከሆኑ ጀማሪ ባንኮች በስተቀር በሁሉም የግልና የመንግሥት ባንኮች ተፈጻሚ ሆኗል፡፡ የኤቲኤም ካርድን መጠቀም የራሱ የሆኑ ጥቅሞች እንዳሉት የታመነ ቢሆንም፣ የተወሰኑ በአጠቃቀም ወቅት የሚስተዋሉ ችግሮች እንዳሉ ብዙ ሰው የሚያውቀው ነው፡፡ የኤቲኤም ካርድ በአንዳንድ ማሽኖች ተቀባይነት አለማግኘቱ፣ አንዳንዶቹ ፈጽሞ የማይሠሩ (Active ያልሆኑ) መሆናቸው፣ በአንድ ቀን ማውጣት የሚቻለው የገንዘብ መጠን መወሰኑ፣ የኔትወርክ አለመኖርና ተደጋጋሚ የማሽን ብልሽት፣ በቂ የክፍያ ማሽኖች በየቦታው አለመኖራቸው፣ በኤቲኤም አሠራር የሚታዩ ግድፈቶች ወዲያው ሊታረሙ አለመቻላቸው ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው፡፡ በዚህ ጽሑፍ የምንመለከተው ግን ከባንኩ ውጭ በሆኑ ምክንያቶች በኤቲኤም ካርድ አገልግሎት ላይ ከተጋረጡ ችግሮች ዐቢይ የሆነውን የካርድ መጥፋት ጉዳይ ነው፡፡

በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል የሚፈረም የኤቲኤም ካርድ አገልግሎት ውል ደንበኞች ካርዳቸውን ወይም የሚስጥር ቁጥራቸውን ለሦስተኛ ወገን አሳልፈው እንዳይሰጡ፣ ካርዳቸውን እንዳይጥሉ፤ ይህ ካልሆነ ግን ካርድ በመጥፋቱ፣ ወደ ሦስተኛ ወገን በመተላለፉ ወይም የሚስጥር ቁጥሩ በመገለጡ ምክንያት ለሚመጣው ጉዳት ደንበኞቹ ኃላፊ ሊሆኑ እንደሚገባ ነው፡፡ የኤቲኤም ካርድ በጠፋ ጊዜም ግን ባንኮች ኃላፊነት ሊኖርባቸው የሚችልበት ሁኔታ ዝግ አይደለም፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት 17 ቮልዩም አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ከሰጠባቸው ጉዳዮች ውስጥ የሰበር መዝገብ ቁጥር 96309 አንዱ ሲሆን፣ በዚህ ጽሑፍ ይህን አስተማሪ ፍርድ መነሻ በማድረግ አጠር ያለ ዳሰሳ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ

ጉዳዩ የጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ ከሳሽ አቶ ዓለማየሁ ግርማ ተከሳሽ ደግሞ ዳሸን ባንክ ነው፡፡ ደንበኛው በባንኩ የቁጠባ ሒሳብ ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ የቁጠባ ሒሳባቸውን በኤቲኤም ካርድ ያንቀሳቅሳሉ፡፡ ጥር 23 ቀን 2003 .. የደንበኛው የኤቲኤም ካርድ ይጠፋል፤ ደንበኛውም መጥፋቱን ጥር 25 ቀን 2003 .. በጽሑፍ ለባንኩ ያሳውቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ ባንኩ የኤቲኤም ሒሳባቸውን ባለመዝጋቱ ሪፖርት ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 9 ቀን 2003 .. ባንኩ ለማይታወቁ ሦስተኛ ወገኖች ብር 40,300 በኤቲኤም ክፍያ ይፈጽማል፡፡ በዚህ ጊዜ ነው ደንበኛው ባንኩ ሒሳቤን መዝጋት ሲገባው ባለመዝጋቱ ያለፈቃዳቸው ወጪ ለተደረገው ገንዘብ ወለድና ወጪ ባንኩ ኃላፊ እንዲሆን ክስ ያቀረቡት፡፡

Continue reading
  19563 Hits