ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ለዲሞክራሲያዊ ማህብረሰብ መፈጠር የመሰረት ድንጋይ ነው፡፡ ይህ መብት በጣም ረጅም ጊዜ ያስቆጥረ የሰው ልጅ መብት ሲሆን በዘመናት መካከል በፈላጭቆራጭ ነገስታት እና መሪዎች ጫና ተደርጎበታል፡፡ ለአብነት ያህልም በጥንታዊ ባቢሎናዊያን የልዩነት ሃሳብ (being dissenter) መያዝ ወደ እቶን እሳት ያስጨምር እንደነበር ከመጽሃፈ ዳንኤል ምዕራፍ 3 ንባብ መረዳት እንችላለን፡፡
Copyright © 2023 Abyssinia Law | Making Law Accessible! . All Rights Reserved.
Maintained by Liku Worku Legal Service