In Response to the comment given by a Fitsum Yifrashewa

ፍጹም ይፍራሸዋ ለሰጠኀኝ አስተያየት እና ለላክልኝ ጽሁፍ አመሰግናለሁ፡፡ በጽሁፋ ላይ ለማንሳት የወደድኩት የንግድ ምልክት በኢትዮጵያ ህጎች ደረጃ ቀለል ባለ ሁኔታ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያህል ነው፡፡ በሌላው ጸሃፊ የተጻፈውንና አንተም የላክልኝን በዚሁ ድረ-ገጽ ላይ ስለ ንግድ ምልክት የተጻፈውን ጽሁፍ ለማየት ሞክሬያለሁ፡፡ ጸሃፊው በንድግ ምልክቶች ላይ የጻፈው ጽሁፍ ጠቃሚና ስለንግድ ምልክቶች ለማወቅ የሚረዳ መሆኑን ለማስገንዘብም እወዳለሁ፡፡ ይህም በጽ/ቤቱ በስራ ባሳለፍኩባቸው ግዝያቶች አጠቃላይ ከሚታዩ ሁኔታዎች ይልቅ በአሰራርና ህጉን በተገቢው መንገድ በኢንተርናሽናል ደረጃና ከህጉ አላማ አንጻር መሬት ላይ ለማውረድ ችግር ወደፈጠሩት ሁኔታዎች ትኩረት ሰጥቸ እንድጽፍ አነሳስቶኛል፡፡ሆኖም ግን በጽሁፉ ላይ መስተካከል ይገባቸዋል የምላቸውን ነገሮች ከዚህ በታች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

የንግድ ምልክት ማለት የአንድ ምርት ወይም አገልግሎት መይም ምንጭ(Origin) በማስመዝገብ እንደ ብቸኛ መለያ(Exclusive sign) ተወስዶ ሰዎች አንድን ምርት መይም አገልግሎት ከሌላው ምርት ለመለየት የሚያገለግል ምልክት ሆኖ ማሳከር(Confusion) የማስወገድ አላማ ያለው ነው፡፡ ተብሎ በጸሃፊው በተቀመጠው ላይ ከዚህ በታች ያሉት ማስተካከያዎች መግባት እንዳለባቸው አምናለሁ፡፡

በመጀመሪያ “የንግድ ምልክት ማለት የአንድ ምርት ወይም አገልግሎት መይም ምንጭ(Origin) በማስመዝገብ……” ተብሎ የተጠቀሰው በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ 501/1998 አንቀጽ 6(ሸ) ላይ በተጠቀሰው መሰረት የአንድን ምርት ወይም አገልግሎት የመነጨበትን ቦታ በንግድ ምልክቱ የቀረበ እንደሆነ የንግድ ምልክቱ ለምዝገባ ብቁ እንደማይሆንና ይህም ሁኔታ በዚሁ አዋጅ በአንቀጽ 6(2) መሰረትም ስናየው በምንም አይነት መልኩ በአንቀጽ 6(ሸ) ላይ የተቀመጠው የህግ አግባብ exception እንደሌለውም በግልጽ ሲያሳይ ይታያል፡፡ የአንድን ምርት ወይም አገልግሎት የመነጨበትን ቦታ በምልክትነት ማስመዝገብ የሚቻለው በንግድ ምልክት ሳይሆን በወል የንግድ ምልክት እንደሆነና በሁለቱ መሃከልም ብዙ ልዩነት እንዳለ ማጤኑም ተገቢ ይሆናል ብየ አስባለሁ፡፡

በሁለተኛነት “እንደ ብቸኛ መለያ (Exclusive sign) ተወስዶ ሰዎች አንድን ምርት መይም አገልግሎት ከሌላው ምርት ለመለየት የሚያገለግል ምልክት ሆኖ…” የሚለው አገላለጽ ጠቦ መተርጎም ብቻ ሳይሆን መስተካከልም አለበት ብየ አምናለሁ፡፡ ይህንንም ለማለት የፈለኩት አንድ የንግድ ምልክት ከሌሎች ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ሳይሆን ሌሎቹ ንግድ ምልክቶቹ ካልተመዘገቡ አንድ አይነት ወይም ተመሳሳይ ከሆኑ የንግድ ምልክቶች የተለየ እንዲሆን የሚጠበቅበት ሲሆን  በሌላ መንገድ ደግሞ ሌሎቹ የንግድ ምልቶች ከተመዘገቡ እንደሆነ ደግሞ  አንድ አይነት ወይም ተመሳሳይ ከሆኑ ምርቶቻቸው ወይም አገልግሎቶቻቸው በተጨማሪ በዕቃወቹ ወይም አገልግሎቶቹ መካከል ግንኙነት እንዳለ በማያሳይ መልኩ መቅረብ እነዳለበት እንጂ በአጠቃላይ ከሌላው ምርት ጋር መለየት አለበት ተብሎ መቀመጥ እንደሌለበት መታወቅ አለበት ፡፡

በሌላው የጸሃፊው የጽሁፍ አካል ውስጥ “የንግድ ምልክት ህጋዊነት የሚመሰረተው ወይም ጥበቃ የሚያገኘው በምዝገባ እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 4፣5፣15 እና 16 መረዳት የሚቻል ሲሆን……” ተብሎ የተገለጸው ውስጥ ከዚህ በታች በተገለጸው መልክ መታረም አለበት እላለሁ፡፡

Continue reading
  10000 Hits