የባንክ ሕግን በተመለከተ በዋናነት የባንክ ብድር ግንኙነቶችን፣ የባንክ ሂሳብ እንቅስቃሴዎችና የሕግ ማዕቀፎች፣ ኤሌክትሮኒክ የባንክ አገልግሎቶች የሚገዙባቸውን ሕጎች፣ የባንክ አገልግሎቶች በዋናነት የባንክ ዋስትና ሰነዶች (Letter of Guarantees)፣ በሰነዶች ብድር የመክፈት አገልግሎት(L/C)፣ የሚተላለፉ የንግድ ሰነዶችን በተመለከተ በዋናነት ቼክ፣ የሐዋላ ወረቀት፣ የተስፋ ሰነድ፣ ሲፒኦ የመሳሰሉ ሰነዶች የሚገዙባቸውን የሕግ ማዕቀፎች ከተግባራዊው የባንክ ሥራ፣ የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን እንዲሁም ሌሎች የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ብዛት ካላቸው ማጣቀሻዎች ጋር በማገናዘብ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው።

መጽሐፉ በንግድ ሕጉ ያልተሸፈኑና በተግባር እየተሰራባቸው ያሉ አሰራሮች የሚገዙባቸው የሕግ ማዕቀፎች እንዲሁም ማሻሻያ የሚያሻቸውን የሕግ አንቀጾች ያመላክታል።  

መጽሐፉ ገዙ አየለ መንግስቱ በተባለ የሕግ ባለሙያ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ጸሐፊው ከጅማ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን፣ ከአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ድግሪውን አግኝቷል፡፡ ጸሐፊው ለአምስት ዓመታት በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሕግ ትምህርት ቤት በሕግ መምህርነት፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በሕግ ባለሞያነት እያገለገለ ይገኛል፡፡

መጽሐፉን ከሜጋ መጽሐፍት ማከፋፈያ፣ ከጃፋር ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ ዩኒቨርሳል፣ ኤዞፕ መጽሐፍት መደብሮች ያገኙታል።