ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታን ስለማስለቀቅ
Abyssinia Law Abyssinia Law
  • Home
  • Laws
    • Search Federal Laws
    • Regional Laws
    • Constitutions
    • Audio Legal Resources
  • Decisions
    • Cassation Decisions by Volume
    • Cassation Decisions Database
    • FFI Court Commercial Bench Decisions
  • Blog
  • Resources
    • Researches Papers
    • Policies and Strategies
    • Codes, Commentaries and Explanatory notes
    • Legal Forms
    • Bench Books
    • Human Right Documents
    • Modules and Materials
    • About Our Laws
    • Quick links
  • Study On-line
  • know your rights
  • Lawyers
  • About Us
    • Who Are We
    • Our Partners
    • Advertise with Us
    • Privacy Policy
    • Contact us
    • Professional Advice?
    • How to submit a blog post
  • login
  • Court Fee Calculator
Abyssinia Law Abyssinia Law
  • Home
  • Laws
    • Search Federal Laws
    • Regional Laws
    • Constitutions
    • Audio Legal Resources
  • Decisions
    • Cassation Decisions by Volume
    • Cassation Decisions Database
    • FFI Court Commercial Bench Decisions
  • Blog
  • Resources
    • Researches Papers
    • Policies and Strategies
    • Codes, Commentaries and Explanatory notes
    • Legal Forms
    • Bench Books
    • Human Right Documents
    • Modules and Materials
    • About Our Laws
    • Quick links
  • Study On-line
  • know your rights
  • Lawyers
  • About Us
    • Who Are We
    • Our Partners
    • Advertise with Us
    • Privacy Policy
    • Contact us
    • Professional Advice?
    • How to submit a blog post
  • login
  • Court Fee Calculator
Details
Category: Property Law
13.Feb
Hits: 16559

ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታን ስለማስለቀቅ

ህገ መንግስታዊ  መስረቱ

የኢ ፌ.ዲ.ሪ  ህገ - መንግስት የመሬት ባለይዞታነትን በማስመልከት  ቀደም ሲል ለመዳሰስ እንደተሞከረው በአንቀፅ 40 እና 89(5) ላይ ዜጉች በገጠርን ሆነ በከተማ መሬት አጠቃቀም ስለሚኖሩዋቸው መብቶችና ግዴታዎች እንዲሁም አስተዳደሩን በማስመልከት የመሬት ባለቤትና የመንግስትና የህዝብ መሆኑን በእርግጠኛነት የሚደነግግ መሆኑን እያየን መጥተናል፡፡ አሁን ከያዝነው ርእስ ጉዳዩ አኳያም አንቀፅ 40(8) ላይ ‘’የግል ንብረት  ባለቤትነት መብት እንደተጠበቀሆኖ መንግስት ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ ተመጣጣኝ  ካሳ በቅድምያ በመክፈል  የግል  ንብረትን ለመወስድ  ይችላል ፡፡’’ በማለት  ይደነግጋል ከዚህ  ህገ - መንግስታዊ ድንጋጌ ለመረዳት የሚቻለው ማንኛውም ዜጋ ንብረት የማፍራት፣ ተጠቃሚ የመሆን መብት እንዳለውና ይህ የግል ሆነ የጋራ ባለንብረትነት መብት በህግ ለህዝብ ጥቅም  ሲባል  የሚወስድበት  ሰው በቅድምያ ካሳ የማግኝት  መብት  እንዳለው የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ይህም መሬት የመንግስትና የህዝብ ነው የሚለውን ህገ-መንግሰታዊ መርህ መሰረት በማድረግ ዜጎች በመሬት ላይ በገንዘባቸውና በጉልበታቸው ሰለሚሰሩት ቤት ወይም ስለሚያፈሱት ሃብት የሚኖራቸው መብት የባለቤትነት መብት በመሆኑ ለዚህ የግልም ሆነ የጋራ ንብረት ካሳ የማግኘት መብታቸውን በማስመልከት የሚደነግግ ህግ ነው፡፡ ካሳ ይከፈለኝ ብለው በልበሙሉነት እንዲከራከሩ የሚያስችላቸውም ነው፡፡ የአቅማቸውን ያህል  በመሬቱ  ላይ ኢንቨስት እንዳያደርጉ፡ ጉልበታቸውን፤ ጥረታቸውንና እውቀታቸውን እንዳያፊሱ  ከሚኖር ሰጋት ተላቀው ህግ-መንግስትና እሱን መስረት  በማድረግ የወጡ  ሕጎች  ዋስትና ሰጪነታቸውን ተገንዝበው  የልማቱ  ተሳታፊ እንዲሆኑ  የሚያስችላቸው  ነው፡፡  በመሆኑም ህግ - መንግስቱ ግዴታን ብቻ  ሳይሆን መብቱም ያቀፈ  በመሆኑ ከዚህ አቅጣጫ ሲታይ የዜጎችን የንብረት መብት እጦት  ስጋት የቀረፈ ነው ፡፡

 

የአዋጅ ቁጥር 455/97 አላማዎች 

Øየከተማ መሬትን ማልማት

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 40(8) የያዘዉን ህገ መንግስታዊ መርህ መስረት በማድረግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/97 በመግብያው ላይ

  የአገሪቱ ከተሞች ከግዜ ወደ ግዜ እያደጉና የነዋሪዎችም ቁጥር  እየጨመረ በመሄዱ በከተሞቹ ፕላን መስረት ለመኖርያ ቤት ግንባታ ለመሰረተ ልማት፤ ለኢንቨስትመንትንትና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውል የከተማ መሬትን መልሶ ማልማት አስፈላጊ በመሆኑ እንዲሁም በገጠር ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች መሬት አዘጋጅቶ ማቅረብ በማስፈለጉ፤

በማለት የአዋጁን  አስፈላጊነት ይገልፃል፡፡ የከተሞች  የልማት  ስትራተጂ  ውጤታማ  ለማድረግ ልማቱ በራሱ የሚጠየቀው የመሬት ግብአት እንዳለና ይህን ደግሞ አንድም ከቆየው የከተማ ቦታ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ባለይዛታውን ካሳ  እየከፈሉ በማስለቀቅ አልያም በከተምች  አከባቢ ያለን የገጠር መሬት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ማስለቀቅ የግድ  ነው፡፡ በመሆኑም የከተማ መሰረተ ልማት ለመዘርጋት፣ ለኢንዱስትሪና የገበያ ቦታዎች ሲባል እንዲሁም ለመኖርያ ቤት ሲባል የከተማ ቦታን በማስለቀቅ ወይም ሌላ ተጨማሪ የገጠር መሬት ወደ ከተማ ክልል በማስገባት ማልማት የሚጠይቅ ነው ፡፡

Øየገጠር መሬትን  ማልማት

የዚህ አዋጅ ሌላው አላማ የገጠር  ልማት ስትራተጂው  ተግባራዊ ለማድረግ ለምሳሌ  የገጠር መስረተ ልማት  ስራዎችን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለማስፋፋት የግድ  የገጠር መሬትን  መጠቀም ስለመሚጠይቅ እነዚህን የልማት ስራዎች ማለትም እንደ ገጠር ኢንቨስትመንት ለማከናወን ስራው የሚጠይቀው የገጠር መሬት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ማስለቀቅ እንደሚቻል  በመገንዘብ የገጠር  መሬት  ልማትን ማእከል ያደረገ ህግ  እንዲወጣ መደረጉ ለልማት ሲባል ዜጎች በዚህ ይዞታቸው የመገልገል መብት ላይ የተጣለ ህጋዊ ገደብ ቢሆንም ለዘላቂና ዋስትና ላለው ልማት ሲባል የሚደረግ ስለሆነ ህ/ሰቡን የሚጐዳ አይደለም፡፡

Øየካሳ አከፈፈል  ስርዓት መዘርጋት

የከተማ ይሁን የገጠር መሬት ለዝህብ ጥቅም ሲባል ባለይዞታውን ማስለቀቅ እንደሚቻል ሁሉ በህግ መንግስትና ከዚያ በታች ባሉ ህጉች ጥበቃ ያገኘውን ቅድምያ ካሳ የማግኘት መብትን እንዴት ባለ ሁኔታ ከይዞታው እደሚለቅና  በሚለቅበት ግዜም ስለሚኖሩ የካሳ አከፋፈል ስርዓቶች በአዋጁ አንቀፅ 7 እና 8 እንዲሁም በደንብ ቁጥር 135/99 ከአንቀፅ 3 እሰከ 18 በዝርዝር የተደነገገ  በመሆኑ በየጊዜው ይከሰት የነበረውን ወጥነት የሌለው የካሳ አከፋፈል ስርዓት ቢያንስ የተቀራረበ እንዲሆን የሚያስችል በመሆኑ ጠቀሜታው እጅግ የጉላ ነው ፡፡

Ø

በዚህ ርእሰ ጉዳይ ተደጋግመው የሚነሱና ለዓመታት በህግ ባለመያዎች መካከል ሳይቀር ልዩነት ሲፈጥሩ የሚስተዋሉትን እንደ “ ካሳና ” “ የህዝብ ጥቅም ” ያሉ በማያሻማ መንገድ  መተርጐሙ  ለአፈፃፀም  ካለዉ ፈይዳ አንፃር ብቻ ሳይሆን አፈፃፀሙ በዜጎች መብት ላይ ከሚፈጠረው ተፅእኖ  አንፃርም ጭምር ሲመዘን የህጉ አቀራረፅና አላማ መፍትሔ ሰጪነቱ ብእጅጉ ጎልቶ  እንዲታይ የሚያደርግ ነዉ፡፡ ለዚህም አዋጁ በአንቀፅ 2(1) ላይ ‘’ካሳ ማለት የመሬት ይዞታውን እንዲለቅ ለሚወሰንበት ባለይዞታ በመሬቱ ላይ ለሰፈረው ንብረት በዓይነት ወይም  በገንዘብ  ወይም በሁሉቱም የሚከፈል ክፈያ ነው ፡፡ ’’ በማለትና በአንቀፅ 2(5) ላይ ደግም ‘’የህዝብ ጥቅም ማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ህዝቦች በመሬት ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ማሕበራዊና ኢኮኖምያዊ ልማትን በቀጣይነት ለማጎልበት አግባብ ያለው አካል በከተማ መዋቅራዊ ፕላን ወይም  በልማት እቅድ መስረት የህዝብ ጥቅም ብሎ የሚወስነው ነው፡፡’’ ሲል ደንግጓል፡፡  ይህ ከአሁን ቀደም የነበረውን  የህዝብ ጥቅም ምንድን ነው? የሚል የአረዳድ ችግር በሚያስወግድ  መልኩ መተርጎሙ በእጀጉ ጠቃሚና መፍትሄ ሰጪም ነው፡፡ ዜጎች ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬታቸውንና  ለዓመታት ለፍተው ያፈሩትን ንብረት ለቀዉ እንዲሄዱ  ሲወስንባቸው  ከጥራጥሬ ነፃ ሆነው ያለማንገራገር ለሚመለከተው አካል እንዲያስረክቡ ካልሆነም ጉዳያቸውን በህግ ሰልጣን  ወደ ተሰጠው አካል አቅርበው ፍትህ እንዲያገኙ የሚያስላቸውም ነው፡፡

 

የባለይዞታዎች መብት

ü   ተመጣጣኝ ካሳ በቅድምያ የማግኘት መብት ማንኛውም ባለሃብት መሬቱንና  በመሬቱ ላይ ያስፈሪውን ሃብት ለህዝብ ጥቅም ሲባል እንዲለቅ በሚመለከተው አካል ሲወስንበትና  ይህን መስረት በማድረግ ማሰጠንቀቅያ ሲደርሰው ከ 90 ቀን ባላነስና ባልበዛ ግዜ  ውስጥ ቦታውን ለሚመለከተው አካል ማስረከብ ቢኖርበትም ለንብረቱ ተመጣጣኝ ካሳ በቅድምያ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ (ህገ መንግስት አንቀፅ  40(8) እና የአዋጁ አንቀፅ 7 እና 8 እና ደንብ ቁጥር 135/99)

ü  ካሳን መስረት  በማድረግ  አቤቱታ የማቅረብ  መብት፡፡  አንድ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ይዞታው እንዲለቅ የሚደረግ ስው በሚወስነው የካሳ መጠን ላይ አንሷዋል የሚል ከሆነ ወይም ያለተገመተ ንብረት ቀርቷል ወ.ዘ.ተ. በሚል ምክንያት የገማቾችን ውሳኔ በመቃወም አብዮቱታውን በገጠር የመሬት ነክ አብዮቱታ ሰሚ አሰተዳደራዊ አካል ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ይህ ባልተደራጀበት ሁኔታ ስልጣን ወዳለው መደበኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ  ይችላል፡፡  ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ማንኛውም ዜጋ ከህግ ውጭ የንብረት መብቱን እንደማያጣና በየደረጃው ባሉ አስተዳደር  አካላት በሚሰጡት ውሳኔዎች ላይ ይግባይ  በማለት  ቀጥሎ  ወዳለው  ይግባይ  ሰሚ መደበኛ ፍርድ ቤት መሄድ እንደሚችል ነው ፡፡ (አንቀፅ 10 እና 11) የመሬት ባለይዞታ ካሳ የማግኘት መብት እንዳለው ሁሉ ካሳዉን ተቀብሎ  መሬቱን የማስረከብ ግዴታም አለበት፡፡ ለዚህም የአዋጁ አንቀፅ 4 “አንድ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ከይዛታው እንዲለቅ የተወስነበት ስው ካሳውን ተቀብሎ በ90 ቀናት ውስጥ መሬቱን ለወረዳው ወይም ከተማው አስተዳደር ማስረከብ አለበት፡፡” ሲል ይደነግጋል ይህም የሚያሳየው የመብትና ግዴታ ያለመነጣጠልን ነው፡፡”

 

የአስተዳደር መብትና  ግዴታ

 

በከተማም  ሆነ በገጠር  ያለ አስተዳደር ለህዝብ ጥቅም ሲባል የከተማ ቦታን ወይም የገጠርን መሬትን  በሚያስለቅቅበት ግዜ  ለባለ  ይዞታው  ማሳወቅ፣ ካሳ የመክፈልና  ባለይዞታው ካሳውን ለመቀበል  ፊቃደኛ  ባለሆነበት  ግዜም ሂሳቡን በዝግ የባንክ ሂሳብ በማስቀመጥ የሚለቀው ዜጋ በተቻለ መጠን እንዲቋቋም የማድረግና የሚለቀቀውን ንብረት  መስረት ያደረገ መረጃ  የመያዝ ግዴታዎች ያሉት ሲሆን  ባለይዞታው ለመልቀቅ  ፊቃደኛ  ባልሆነበት  ግዜ የፓሊስ ኃይል  ተጠቅሞ ማስለቀቅ  እንደሚችል አዋጁ በአንቀፅ 4(5) በግልፅ ይደነግጋል ፡፡

ስለዚህ አዋጅ ቁጥር 455/97  ለህዝብ  ጥቅም ሲባል ስለሚለቀቅ  የገጠር መሬት  ወይም የከተማ ቦታ  በሚለቀቅበት  ግዜ የማሳወቅ ስርዓት፣ የመገመት፣ ካሳ ማለትም የንብረት ግምትና የመፋናቀያ ካሳ ስለሚከፈልበት  ሰርዓትና በተወስነው ካሳ ያለተስማማ ባለይዞታ አቤቱታውን  ወደሚመለከተው አካል የማቅረብና  አሁንም በተስጠው ውሳኔ ቅር ከተስኘ ይግባይ ብሎ የመሄድን  መብት ባካተተ መንገድ የህገ-መንግስቱን አንቀፅ 40(8) ካሳ  በቅድምያ የማግኘት መርህ  ተከትሎ  የወጣ ህግ በመሆኑ ዜጋች የንብረታቸው የወደፊት እጣ ፋንታ  ግልፅ  የሆነ የባለቤትነት ስሜት ኑራቸው በልማቱ መስክ በሙሉ አቅማቸው እንዲስሩ የሚያደርግ ነው፡፡

ለህዝብ ጥቅም ሲባል ከመሬት ባለይዞታነት ማስለቀቅን በሚመለከት ከገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/97 አንፃር ሲታይ ከፍ ብለን እንዳየነው ከህገ-መንግስቱና አዋጅ ቁጥር 455/97 ባልተለየ መልኩ በአንቀፅ 7(3) ላይ ፡-

‘’የገጠር መሬት በላይዞታነት ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬቱን በመንግስት  እንዲለቅ ሲደረግ በመሬቱ ላይ ላደረገው ማሻሻያና ላፈራው ንብረት ተመጣጣኝ ካሳ ይከፈለዎል፡፡ ወይም ለለቀቀው  መሬት ምትክ በታቻለ መጠን ሌላ ተለዋጭ  መሬት እንዲያገኝ  ያደረጋል’’  ­­­­­ሲል የሚደነግግ  ሲሆን  የከተማ  ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣዉ ኣዋጁ ቁጥር 272/1994 እንደዚሁ ተመሳሳይ በሆኑ  መንገድ በአንቀፅ  16 ላይ ፡­­-

  አግባብ ያለው ኣካል ለህዝብ ጥቅም ይውላል ብሎ በሚወስነው መስረት ለሚመለከተው ስው የማስለቀቅያ ትእዛዝ ወይም ማስጠንቀቅያ በፅሁፍ በመስጠት የሚፈለገውን  የከተማ ቦታ ማስለቀቅና መርከብ ይችላል ፡፡ ትእዛዙንም አመቺ በሆነ ሌላ መንገድ ይፋ ያደርጋል፡፡

በማለትና ለህዝብ ጥቅም ተብሎ ሲለቀቅ ካሳ መከፈል እንዳለበት በአንቀፅ 15(1)(ለ) ላይ  ቦታው  ለህዝብ ጥቅም ተብሎ ለሌላ ስራ ወይም አግልግሎት እንዲውል ሲወስን  በሚል አገላለፅ ካሳ  እንደሚከፈል አንቀፅ 15 ላይ ከወጣው የሊዝ ይዞታ ማቋረጥና ካሳ  አከፋፈል ከሚለው ርእስ መረዳት ይቻላል ፡፡ ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚችለውም ለህዝብ ጥቅም ሲባል ሊለቀቅ የሚችለው መሬት የገጠር መሬት ወይም በሊዝ ይዞታነት ያለ የከተማ ቦታ ሊሆን  እንደሚችልና ሁሉም ሰለሚኖራቸው  የካሳ አከፋፈል መብት ሰፋ ባለ መልኩ በአዋጅ ቁጥር 455/97 እና ደንብ ቁጥር 135/99 ላይ በዝርዝር ተደንግጎ የምናገኘው  መሆኑን ነው ፡፡

Read Next

  • Key Reforms in the 2021 Commercial Code
    31.Oct
  • "የግልግል ዳኝነት በኢትዮጵያ ሕግ" የሚል ርዕስ ያለው አዲስ የሕግ መጽሐፍ በገበያ ላይ
    17.Mar
  • Administrative Law (30)
  • African Human Rights Law (18)
  • African Union Law (6)
  • Alternative Dispute Resolution (33)
  • Agency (6)
  • Bankruptcy Law (4)
  • Civil Procedure (12)
  • Conflict Laws (3)
  • Constitutional Law (5)
  • Construction Law (3)
  • Contract Law (7)
  • Criminal Law (10)
  • Criminal Procedure (6)
  • Criminology (4)
  • Customary Law (4)
  • Employment and Labor Law (17)
  • Environmental Law (5)
  • Evidence Law (6)
  • Family Law (5)
  • Gender and the law (4)
  • Human Right Law (5)
  • Humanitarian Law (7)
  • Insurance, Banking and Negotiable Instrument Law (6)
  • Intellectual Property Law (4)
  • International Organizations (4)
  • Introduction to law and Law of Persons (4)
  • Investment Law (10)
  • Islamic Law (2)
  • Judgment writing (0)
  • Jurisprudence (1)
  • Land Law (10)
  • Law and Development (0)
  • Legal History (0)
  • Legal Profession (0)
  • Legal Research Methods (0)
  • Legal Writing (0)
  • Legislative Drafting (0)
  • Maritime Law (3)
  • Non-Contractual Liability (Tort Law) (10)
  • Pre-Trial Skills and Trial Advocacy (0)
  • Property Law (27)
  • Public Enterprises and Cooperatives (0)
  • Public International Law (0)
  • Refugee Law (0)
  • Sales and Security Devices (0)
  • Sentencing and Execution (4)
  • Succession Law (6)
  • Taxation Law (4)
  • Trade and Business Organizations (2)
  • Administrative Contract (16)
  • Federalism (3)
Copyright © 2025 Abyssinia Law | Making Law Accessible! . All Rights Reserved.
Maintained by Liku Worku Legal Service