በኢትዮጵያ ከሕግ አገልግሎት የሚሰበሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስና የተርን ኦቨር ታክስ አዙሪት ጥያቄዎችና መውሰብስቦች

393 Downloads

በኢትዮጵያ የታክስ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የተርን ኦቨር ታክስን በመጠቀም ከሕግ አገልግሎት ላይ የሽያጭ ታክስ እንደ ሁኔታው በፌዴራሉና በክልል መንግስታት በመጣሉ በተግባርም እየተሰበሰበ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ታክስ ሕጋዊ መሠረቱን እና አግባብነቱን በተመለከተ፤ ከታክስ መሠረቱ፣ ከታክስ ምጣኔው እና ከአስተዳደር ሂደቱ ጋር ተያይዞ በርካታ አዙሪት ጥያቄዎችና መውሰብስቦች ይስተዋላሉ፡፡ የዚህ ጥናት ዓላማም አነዚህን አዙሪት ጥየቄዎችና መውሰብስቦች በዓይነታዊ የምርምር ዘዴ በማጥናት የመፍትሔ ኃሳብ መጠቆም ነው፡፡ ለዚህም ያስችል ዘንድ የተለያዩ መዛግብቶች፣ ቃለመጠይቆችና ቡድንተኮር ውይይቶች በግብዓትነት ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን  ለንፅፅር ይረዳ ዘንድ የሌሎች አገራት ተሞክሮንም ለመቃኘት ተሞከሯል፡፡ በዚህም መሠረት ጥናቱ ባለሶስት አማራጭ የመፍትሔ ኃሳብ ያቀረበ ሲሆን የመጀመሪያው አሁን ከሕግ አገልግሎት በአገሪቱ እየተሰበሰበ ያለውን የሽያጭ ታክስ እንዳለ በማስቀጠል ለፍትሕ ተደራሽነትና ለሕገመንግስታዊ መብቶች መከበር ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር መወሰድ ያለባቸውን ርምጃዎች አመላክቷል፡፡ በሌላኛው የአማራጭ መፍትሔ ከሕግ አገልግሎት የሚሰበሰበውን የሽያጭ ታክስ ሙሉ በሙሉ በማስቀረት ሌሎች አማራጭ የገቢ ምንጮችን መጠቀም እንደሚቻል ጠቁሟል፡፡ የመጨረሻው የመፍትሔ ኃሳብ ደግሞ ሁኔታዎችን ያገናዘበ ስልት በመቀየስ ለሕግ አገልገሎት ራሱን የቻለ አዲስ ሠንጠረዥ ማዘጋጀትን የሚጠይቅ ነው፡፡ ለዚህም ያግዝ ዘንድ የሕግ አገልግሎቶችን አስፈላጊነትና በሕገመንግስት ጥበቃ ከተደረገላቸው መብቶች ጋር ያላቸውን ቁርኝት፣ የሕግ አገልግሎት ተጠቃሚውን የመክፈል አቅምና የመንግስትን የገቢ ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ በሠንጠረዥ በመከፋፈል በተለያዩ የታክስ ምጣኔዎች የሽያጭ ታክስ እንዲሰበሰብ የሚመክር ነው፡፡ 

ጸሐፊ፦ ሙሐመድ ዳውድ አልቃድር 

File Name: በኢትዮጵያ ከሕግ አገልግሎት የሚሰበሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስና የተርን ኦቨር ታክስ አዙሪት ጥያቄዎችና መውሰብስቦች.pdf
File Size: 1.13 MB
Download: 393 times
Created Date: 01-30-2024