ርዕስ

በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/1996 እና በሌሎች አዋጆች የነበሩ ድንጋጌዎች

በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 1156/2011 የተደረጉ ማሻሻያዎች ወይም በአዲስ መልክ የተካተቱ ድንጋጌዎች

ትርጓሜ

በተሻረው አዋጅ ላይ ያልነበሩ ትርጓሜዎች

ከዚህ ቀደም ከነበሩት ትርጓሜዎች በተጨማሪ አዲሱ አዋጅ ስለ ወሲባዊ ትንኮሳ፣ ወሲባዊ ጥቃት፣ በሰራተኞች መካከል ልዩነት ስለማድረግ እና ሌሎች ተጨማሪ ትርጓሜዎችን አካቷል፡፡

የህጉ ተፈፃሚነት ወሰን

አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 1 የአዋጁን የተፈፃሚነት ወሰን ሲያስቀምጥ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል በሚደረግ በቅጥር ላይ በተመሰረተ የሥራ ግንኙነት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል በማለት ይደነግጋል፡፡

አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 1 የአዲሱ አዋጅ ተፈፃሚነት በአሠሪና ሠራተኛ መካከል ባለ የቅጥር ግንኙነት በተጨማሪ በምልመላ ሂደት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የሙከራ ጊዜ

በአንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት የሙከራ ጊዜ ከአርባ አምስት ተከታታይ ቀን ሊበልጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡

በአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 11/3/ መሰረት የሙከራ ጊዜው ሠራተኛው ስራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ለስልሳ የሥራ ቀኖች ሊሆን እንደሚችል ይደነግጋል፡፡

የተከለከለ ድርጊት

ከዚህ በፊት በነበረው አዋጅ ላይ ይህ ክልከላ በግልጽ አልነበረም፡፡

አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 2/8/ ሠራተኞች ከአሠሪው ፈቃድ ሳያገኝ በስራ ሰዓት ስብሰባ ማድረግ የተከለከለ ተግባር መሆኑን ይደነግጋል፡፡

ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ስለማቋረጥ /በአሰሪው/

አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀፅ 1/ሀ/ መሠረት ያለበቂ ምክንያት ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በመደጋገም የሥራ ሰዓት አለማክበር ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውልን ለማቋረጥ በቂ ምክንያት እንደሆነ ቢቀመጥም ለምን ያህል ጊዜ ያረፈደ ሰራተኛ በዚህ አንቀጽ መሠረት የስራ ውሉ እንደሚቋረጥ በግልፅ አልተደነገገም ነበር፡፡

በአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ/ መሠረት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ በጠቅላላው ለስምንት ጊዜያት የሰራ ሰዓት አለማክበር ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ለማቋረጥ በቂ ምክንያት እንደሚሆን ተደንግጓል፡፡

ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ስለማቋረጥ /በአሰሪው/

ከዚህ ቀደም በነበሩት አዋጅ በተከታታይ ለአምስት ቀናት መቅረት ወይም በአንድ ወር ውስጥ በጠቅላላው ለአሥር ቀናት ወይም በአንድ አመት ውስጥ በጠቅላላ ለሰላሳ የሥራ ቀናት ያለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውልን እንደሚያቋርጥ የተደነገገ ሲሆን

በአዲሱ አዋጅ አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 1/ለ/ መሠረት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ ለአምስት ቀናት ከስራ መቅረት በሚል ተሻሽሏል፡፡

በማስጠንቀቂያ የስራ ውል ስለማቋረጥ /በአሰሪው/

በተሻረው አዋጅ ላይ ያልነበረ ድንጋጌ

በአንቀጽ 28 ንዑስ አንቀስ 2 መሰረት ሠራተኛው የስራ ችሎታውን በማጣቱ ምክንያት በማስጠንቀቂያ የስራ ውሉ እንዲቋረጥ በወቅቱ በሚደረገው የስራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት መረጋገጥ አለበት፡፡

 

ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል ስለማቋረጥ /በሠራተኛ/

በተሻረው አዋጅ ላይ ያልነበረ ድንጋጌ

በአንቀጽ 32 ንዑስ አንቀጽ 1/ለ/ መሠረት በአሠሪው ወይም በሥራ መሪው የወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት የተፈፀመበት ሠራተኛ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውሉን ማቋረጥ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡

ስለ ስራ ስንብት ክፍያና ስለካሣ

በተሻረው አዋጅ ላይ በግልጽ ያልተካተተ

በአንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 1/መ/ በአሠሪ ወይም በሥራ መሪ ወሲባዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ የተፈፀመበት እንደሆነ ወይም ድርጊቱ በሌላ ሠራተኛ እንደተፈፀመ ሪፖርት ተደርጎለት አሠሪው ተገቢው እርምጃ ባለመውሰዱ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ የስራ ስንብት ክፍያ ሊከፈለው እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡

ስለ ስራ ስንብት ክፍያና ስለካሳ

 

በተሻረው አዋጅ ላይ ያልነበረ ድንጋጌ

በአንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 2 በተደነገገው መሰረት በአንቀጽ 32 ንዑስ አንቀጽ 1/ለ/ መሰረት የስራ ውሉን ያቋረጠ ሰራተኛ ከስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የዘጠና ቀን ደመወዙን በካሳ መልክ ያገኛል፡፡

የሠራተኛው ካሣ የመክፈል ኃላፊነት

 

በተሻረው አዋጅ ላይ በግልፅ የአከፋፈሉ ሁኔታ አልተደነገገም

በአንቀጽ 45 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ሰራተኛው ከስራ በሚለቅበት ወቅት የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ከለቀቀ የ30 ቀን ደመወዙን ለአሰሪው በካሳ መልክ መክፈል እንዳለበት እና ይኸውም ለሠራተኛው ሊከፈሉ ከሚችሉ ክፍያዎች ላይ ተቀናሽ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡

ደመወዝ ቅነሳ

አንቀጽ 59 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት በማናቸውም አካኋን ከሰራተኛው ደመወዝ /በፈቃድም ይሁን ያለፈቃድ/ ሊቆረጥ የሚችለው ከአንድ ሶስተኛ በላይ ሊቆረጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡

በአንቀጽ 59 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ሠራተኛው በጽሁፍ ፍቃዱን ከሰጠ ከደመወዙ ከአንድ ሶስተኛ በላይ ሊቆረጥበት እንደሚችል የደነግጋል፡፡

የትርፍ ሰዓት ሠራ አከፋፈል

አንቀጽ 68 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ/ እና/ለ/ መሠረት የትርፍ ሰዓት አከፋፈል በተመለከተ፡-

 

ሀ- ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት የሚሰራ የትርፍ ሰዓት ከፍያ ለመደበኛ ሥራ በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በአንድ ከሩብ ተባዝቶ

 

ለ- ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት የሚሰራ የትርፍ ጊዜ ክፍያ ለመደበኛ ሥራ በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በአንድ ተኩል ተባዝቶ

በአንቀጽ 68 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የትርፍ ሰዓት አከፋፈል በተመለከተ

 

ሀ- ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት የሚሰራ የትርፍ ሰዓት ከፍያ ለመደበኛ ሥራ በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በአንድ ተኩል ተባዝቶ

 

ለ- ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት የሚሰራ የትርፍ ጊዜ ክፍያ ለመደበኛ ሥራ በሰዓት የሚከፈለው ደመወዝ በአንድ ሶስት አራተኛ ተባዝቶ

የሳምንት የዕረፍት ጊዜን በተመለከተ

በተሻረው አዋጅ ላይ ያልተካተተ ድንጋጌ

አንቀጽ 69 ንዑስ አንቀጽ 4 በተደነገገው መሰረት ሠራተኛው በስራው ባህሪ ምክንያት የሳምንቱን የዕረፍት ቀን መጠቀም ያልቻለ እንደሆነ አሠሪው ለሠራተኛው በወር ውስጥ 4 ቀናት ዕረፍት እንዲያገኝ ማድረግ አለበት፡፡

የዓመት ፈቃድ መጠን

አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ሠራተኛ ለመጀመሪያ ዓመት የአገልግሎት 14 ቀን እንዲሁም ለእያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎት አመት አንድ የሥራ ቀን ያገኛል

አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ለመጀመሪያ የአንድ አመት አገልግሎት 16 ቀን እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሁለት የአግልግሎት አመታት አንድ የሥራ ቀን እየጨመረ ይሰጣል፡፡

ለቤተሰብ ጉዳይ የሚሰጥ ፈቃድ

በተሻረው አዋጅ ላይ ያልተካተተ ድንጋጌ

አንቀጽ 81 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ሠራተኛው የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት ሶሶት ተከታታይ ቀናት ፍቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጠዋል፡፡

ለቤተሰብ ጉዳይ የሚሰጥ ፈቃድ

በተሻረው አዋጅ ላይ ፈቃዱ ሊሰጥበት የሚችለው ድግግሞሽ እልተደነገገም፡፡

አንቀጽ 81 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ሠራተኛው ልዩ እና አሳሳቢ ሁኔታ ሲያጋጥመው ለአምስት ተከታታይ ቀናት ያለክፍያ ፈቃድ የማግኘት መብት አለው፡፡ ሆኖም በዚህ ረገድ የሚሰጠው ፈቃድ በበጀት አመቱ ለሁለት ጊዜ ሊበልጥ አይችልም፡፡

የወሊድ ፈቃድ

 

በአንቀጽ 88 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከመውለድዋ በፊት አንድ ወር ከወለደች በኋላ ሁለት ወር ይሰጣታል፡፡

በአንቀጽ 88 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ነፍሰጡር የሆነች ሰራተኛ ከመውለድዋ በፊት አንድ ወር እንዲሁም ከወለደች በኋላ ሶስት ወር ይሰጣታል፡፡

Download the PDF version