እንደ መነሻ
የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት ለረጅም ጊዜ በተለያዩ የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አተሰሳሰቦች የነበረ፤ ያለ እና የሚኖር መስተጋብር ነው፡፡
ታሪኩንም በወፍ በረር መለስ አድርገን ስንመለከት ከካፒታሊስታዊ ሥርዓተ ማኅበር በፊት በነበሩት ሥርዓቶች በተለይም በባሪያ አሳዳሪ /slave-owning/ ሥርዓተ ማኅበር እና በፊውዳል /feudal system/ ሥርዓተ ማኅበር ወቅት ይሰተዋል የነበረው ሠራተኛው እንደ ጪሰኛ የሚቆጠርበት ሥርዓት ነበር፤ የሚያገኘው ጥቅምም ከአሠሪው ምግብ እና መጠለያ እንጂ መደበኛ ደምወዝ አልነበረውም፡፡
የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ ብቅ ማለት የጀመረው በኢንዲስትሪ አብዮት ወቅት ሲሆን የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትም ከትናንሽ የጎጆ ኢንዱስትሪ ወደ ትላላቅ ፍብሪካዎች በተሸጋገረበት ጊዜ ነበር፡፡ በአንጻሩ አሠሪዎች ደግሞ በቀላሉ ሠረተኛ ቀጥረው ያሠሩ ነበር ለምን ቢባል በወቅቱ በጣም ርካሽ የሰው ኃይል ስለነበር ነው፡፡ በወቅቱም የሠራተኛች አንገብጋቢ ጥያቄ የነበረው የተሻለ የሥራ ሁኔታ /minimum working condition/ እንዲሁም ከሠራተኛ ማኅበር አባልነት ጋር የተያያዙ መብቶች ነበሩ፡፡