ጊዜው እ.ኤ.አ 1954 ነው፡፡ ለአለም ሀገራት የዲሞክራሲ አርአያና መምህር ነኝ ብላ በምትደሰኩር በአሜሪካ ሀገር ነጭና ጥቁር ተማሪ በአንድ ላይ አይማርም ነበር አሉ፤ ምክንያቱም ጥቁር ተማሪ ከነጭ ተማሪ ጋር በአንድ ላይ እንዲማር መፍቀድ ማለት በነጭ ተማሪዎች ሞራልና ክብር መቀለድ ነው ብላ ታምን ነበር፤ አሜሪካ፡፡ በመሆኑም ጥቁሮችና ነጮች ተለያይተው ይማሩ ነበር ማለት ነው፡፡ በዚሁ አይን ያወጣ አድልዎ የተበሳጨው ብራውን የተባለው ግለሰብ በአሜሪካ ሀገር የካንሳስ ክልል የትምህርት ጉዳይ ቦርድን በፍርድ ቤት ገተረው፡፡ ሚስተር ብራውን ለጥቁሮች ሽንጡን ገትሮ ከተከራከረ በኃላ ጥቁሮችን አንገት የሚያቀና ፍርድ አስፈረደ፡፡ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቁርና ነጭ ተማሪዎች ተለያይተው እንዲማሩ ማድረግ የሰው ልጆች በተፈጥሮ እኩል ሆኖው የመፈጠር መብትን የሚቃረን በተለይም ደግሞ የጥቁሮች ክብርና ሞራል የሚነካ እኩል የትምህርት እድል የሚነፍግ ህገ ወጥ ድርጊት በመሆኑ ከተፈጥሮ ሕግና የአሜሪካ ህገ መንግስት ጋር የሚጣረስ ነው ሲል ለሰው ልጆች እኩልነት የሚያረጋግጥ ፍርድ ሰጠ፡፡ ጥቁሮች ከነጮች ጋር ያለአድልዎና ልዩነት ሳይደረግባቸው እኩል የትምህርት እድል የማግኘትና የመማር መብት አላቸው የሚል መደምደሚያ ላይ ተደረሰ፡፡ በዚሁ ውሳኔ የተበሳጨው "ጆርጅያ ኩሪዬር" የተባለ ጋዜጣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ዳኞችን እንዲህ ሲል ገለፃቸው፡፡
“No man knows today what his rights are in this country. No man today has any liberties left. His rights and his liberties are in the laps of the nine crazy men who sit on the Supreme Court bench. And the lord only knows what these crazy men will do next. Today they are most dangerous tyrants that ever existed. Like Hitler, Mussolini, and the other modern day tyrants, they are mentally deranged. They are crazed with a desire to serve a minority for political purposes. Their insanity has made them unscrupulous in the methods they have employed to do the bidding of this minority. They are mentally deranged tyrants ruling as unscrupulously as any tyrant in all of history. The members of this court must be curbed or they must be removed from the bench.”
ትችቱ ወደ አማርኛ ስንመልሰው በዚች ሀገር መብቱን እና ነፃነቱን የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ ነፃነቱንና መብቱን በጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንበር ቁጭ ባሉ በእነዚህ ዘጠኝ ያበዱ ዳኞች እጅ ላይ ነው፤በቀጣይም እነዚህ እብድ ዳኞች የሚሰሩት ነገር ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ አሁን በዘመናችን አይተነው በማናውቅ ሁኔታ እነዚህ ዳኞች አደገኛ አምባገነኖች ናቸው፤እንደ እነ ሂትለር፣ሙሶሎኒና ሌሎች ዘመናዊ አምባገነኖች በጭካኔ ያበዱ ናቸው፤ለፖሊቲካ አላማ ሲባል አናሳ ማህበረሰብን ለማገልገል አብደዋል፡፡ እብደታቸውን አናሳውን ለማገልገል ይሉኝታ እንኳን ሊገድበው አልቻለም፤እነዚህ ሰዎች ሊወገዱ ይገባል ለማለት ነው፡፡ (ትርጉም የራሴ)
እኔ ደግሞ እላለሁኝ፡፡ ያበዱት ዳኞቹ ሳይሆን ጋዜጣውን ያወጣው ፀኃፊ ራሱ ነው፡፡ ይህ ጋዜጣ በወቅቱ ይዞት የወጣ ትችት ብሽቅ እና በዘረኝነት የተነዳ ከአንድ ዲሞክራሲያዊት ሀገር ፈፅሞ የማይጠበቅ ነው፡፡ የእብደት እብደት፡፡ ይህ ማለት ከፍትህ እና ከእኩልነት አንፃር የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ከትክክልም በላይ ነበር፡፡