ተገዶ የመያዝን ሕጋዊነት ለማጣራት የሚቀርብ ክስ (Habeas corpus) እና የፍትሐብሔር እንድምታው

የአካል ነጻነት መብት በኢፌዲሪ ህገ መንግስት እውቅና ከተሰጣቸው የሰብአዊ መብቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ይኸውም የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 17 ድንጋጌ በግልጽ ማንም ሰው በህግ ከተደነገገው ስርአት ውጪ ሊያዝ እንዲሁም ክስ ሳይቀርብበት እና ሳይፈረድበት ሊታሰር የማይችል ስለመሆኑ ያስቀምጣል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት በዚሁ ሕገ መንግስት መሰረት የሀገሪቱ የህግ አካል የሆኑ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነነት ሰነዶችም ቢሆን እውቅና ከተሰጧቸው የሰብአዊ መብቶች መካከል አንዱ ስለመሆኑ እሙን ነው፡፡ 

ይሁን እና የዚህ አጭር ጽሁፍ ዋነኛ አላማ የዚህን መብት መሰረታዊ  ነጥቦችን ወይም ወሰኑን ለማብራራት ሳይሆን አንድ የአካል ነጻነት መብቴ ተገፏል የሚል ሰው ይህ መብቱን ፍ/ቤት እንዲያስከብርለት አቤቱታ ቢያቀርብ ክርክሩ ከመደበኛው የፍታብሄር ጉዳዮች ክርክር የሚለይበትን ዋና ዋና የሥነ-ሥርዓት  ነጥቦች ለማብራራት ነው፡፡

Continue reading
  3648 Hits

በፍትሐብሔር ክርክር ቅድመ-ሙግት ሂደት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

የዚህ ጽሑፍ ዋና ትኩረት  ከሙግት በፊት ያሉ ሥነ-ሥርዓታዊ ሂደቶች አንድን ክርክር ላይ ያላቸዉን  ሚና ማጉላት እና ፋይዳቸዉን ማሳየት ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ክርክር ሂደት ቅደመ ሙግት የሚባለዉ ለክርክሩ መሪ ጭብጥ ተይዞ ግራ ቀኙ ማስረጃ ማሰማት ከመጀመራቸዉ በፊት ያለዉ ሂደት ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ክርክር ዋናዉ ሙግት የሚጀምረዉ ጭብጥ ተይዞ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 257 እና ተከታይ ድንጋጌዎቹ ተከራካሪዎች ማስረጃዎቻቸዉ የሚያስረዷቸዉን ጭብጥ እያስመዘገቡ ማስረጃ ማሰማት ሲጀምሩ ነዉ፡፡ ከዋናዉ ሙግት በፊት ባለዉ  የቅድመ ሙግት ሂደት በዋናነት ክስና ማስረጃ ማቅረብ፣ መጥሪያ ማድረስ፣ መልስ እና ማስረጃ መቅረብ፣ ክስ መሰማት እና የክስ መቃወሚያዉ ላይ የመወሰን ተግባሮች ይፈፀማሉ፡፡ ይህ የክርክር ሂደት ክርክሩን ለመምራት ዋና መሰረት የሆነዉ ነዉ፡፡ የክርክሩ አቅጣጫ የሚወሰነዉም በዚህ የክርክር ደረጃ ላይ  በሚሰሩ ስራዎች ነዉ፡፡ ክርክሩን ግልፅ እና አጭር በሆነ ሂደት ለመፈፀም የሚያስችለዉም የቅድመ ሙግት ሂደቱ ጤናማ መሆን ከቻለ ነዉ፡፡

Continue reading
  6818 Hits

Executions of Civil Judgement and the need to Reform the Enforcement System in Ethiopia

Courts; as one and perhaps as the most tasks of their purposes and responsibilities, engage in rendering a fair and equitable decision among parties in law suit. Decisions of a court can either be criminal or civil nature. If the case brought before the court involves criminal nature, the court will give decision by adhering to the rules and procedure provided under criminal law and criminal procedure respectively. Police or prison administration is an organ entrusted with enforcing court’s decision.

Continue reading
  17401 Hits

የ‹‹ያስቀርባል … አያስቀርብም›› እንቆቅልሽ

 

/ ትዝታ በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩዋን ለመከታተል በችሎት ታድማለች፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በቤቷ ላይ ያለአግባብ ፍርድ ተሰጥቷል ብላ ስላመነች የተማረ ጠበቃ የይግባኝ አቤቱታ ጽፎላት ጉዳይዋን በራሷ ትከታተላለች፡፡ እንደ እርሷ አስተሳሰብ ጉዳይዋን ከእርሷ ይልቅ የሚረዳው የለም በሚል ከዳኛ ፊት ቀርባ ለማስረዳት ጓጉታለች፡፡ በዛሬው ቀጠሮ ይህ ሐሳቧ እንደሚሳካላት በውጭ የሚያማክራት ጠበቃ ነግሯታል፡፡

መዝገቡ ለዛሬ በቀጠሮ ያደረው ቀደም ሲል ረዳት ዳኛ ፊት ቀርባ ስለጉዳዩ ካሳሰበች በኋላ የይግባኝ አቤቱታውን ለመስማት በሚል ነው፡፡ ችሎት ተቀምጣ የምትሰማው የዳኛው ድምፅ ‹‹አያስቀርብም ብለናል!›› ‹‹አያስቀርብም›› የሚሉ አጭርና መርዶ ነጋሪ ቃላት ናቸው፡፡ የእሷ ጉዳይ ገና ያልተሰማ በመሆኑ እንዲህ ያለውን ፍርድ ዛሬ እንደማትሰማው አምናለች፡፡ የሕግ አማካሪዋም ልቧን አጽንቶላታል፡፡ ተራዬ እስኪደርስ በሥር ፍርድ ቤት ተፈጸመ የተባለውን ስህተት ለማስረዳት ከማስታወሻዬ ላይ ነጥቦቹን ተራ በተራ በወፍ በረር ልቃን ብላ ጀምራለች፡፡ ከተመሰጠችበት ንባብ ያናጠባት በዳኛው የተጠራው ስሟ ነበር፡፡
‹‹
/ ትዝታ በረደድ›› ብለው ዳኛው ሲጠሩ ከመቅጽበት ከዳኛው ፊት ተገተረች፡፡ ዳኛው ማንነቷን ካረጋገጡ በኋላ ‹‹ይግባኙ አያስቀርብም ብለናል፤›› ሲሏት በደንብ አልሰማቻቸውም፡፡ ‹‹እህ እህ ምን አሉ?›› ብላ ስትጠይቅ ‹‹አያስቀርብም ተዘግቷል፣ ጨርሰናል፤›› አሏት፡፡ ‹‹ይግባኜ አልተሰማም፣ ረዳቱ ነው ያናገረኝ፣ እርስዎን ዛሬ ማየቴ ነውለውሳኔ አልተቀጠረምመዝገቡ የሌላ እንዳይሆን …›› ብዙ ለማለት ብታስብም ባህላዊው የፍርድ ቤት ፍርኃት አላስችላት አለ፡፡ ከእሷ በፊት የተስተናገዱት አቀርቅረው እንደወጡ እሷም በቁሟ አቀረቀረች፡፡ ከዳኛው ፊት እንደቆመች ዳኛው ሌላ ባለጉዳይ ማስተናገድ ቀጠሉ፡፡
በዚህ መነሻ ነበር ከችሎት ስትወጣ ጨዋታ የጀመርነው፡፡ ‹‹አያስቀርብም›› ማለት ምንድነው? በምን ምክንያት ነው? የማያስቀርበውስ እንዴት ነው? ዳኛው ይግባኜን አይሰሙም እንዴ? የሚሉትንና እኔ መልስ ልሰጣት የማልችላቸውን ጥያቄዎች ያዥጎደጎደችው፡፡ ሕጉ የሚለውን፣ ዳኛው ሊፈጽሙት ይገባ የነበረውን ሥርዓት ብነግራት ይባሱኑ ትበሳጫለች በማለት በቀልድ ነገሯን ለማጣጣል ጥረት አደረግኩ፡፡
እናንተ ሐኪሞችስ በማይነበብ ጽሑፍ ለበሽታህ መድኃኒቱ ይሄ ነው ብላችሁ ብጣቂ ወረቀት ትሰጡ የለም እንዴ? አልኳት፡፡ / ትዝታም መለሰች ‹‹እንዴ እኛ እኮ ደማችሁን ለክተን፣ ሙቀታችሁን አይተን፣ የሚሰማችሁን በዝርዝር ሰምተን፣ ደምና ሰገራ፣ ኤክስሬይና ራጅ ተመልክተን ነው፤ ከጻፍነውም በኋላ የመድሃኒት ባለሙያ የማይነበበውን አንብቦ ተገቢውን መድሃኒት ይሰጣችኋል አለች›› በልቤ ‹‹ልክ ነሽ›› አልኩ፡፡ እንዲያውም የመደመጥ መብት በሐኪሞች የተሻለ ይተገበራል፡፡ በእኛ አገር ሐኪሞች ከዳኞች ይልቅ ደንበኛቸውን ይሰማሉ፣ ጊዜ ይሰጣሉ፣ ሰፊ ምርመራም ያከናውናሉ አልኩ፡፡ እርሷንም እንድትጽናና ነግሬያት የነጋሪት ጋዜጣ ወደ መግዣው ሱቅ በመሔድ ከእሷና ከሐሳቧ ሸሸሁ፡፡

‹‹ያስቀርባል - አያስቀርብም›› ነገር ግን የሕግ ዕውቀቱ የሌላቸውን ቀርቶ ለሕግ ባለሙያዎችም በአግባቡ የሚገባ ወይም የተረዳ አይመስለኝም፡፡ ፀሐፊው በፍርድ ቤቶች አካባቢ ከገጠሙት ጉዳዮችና በችሎት ከሚያስተውለው ተግባር አንፃርአያስቀርብም እንቆቅልሽ፣ ያስቀርባል ሎተሪእየሆነ መምጣቱን አስተውሏል፡፡ ‹‹አያስቀርብም›› ልማድ በሰበር ችሎት ሳይቀር የሚስተዋል ቢሆንም፣ በዚህ ጽሑፍ በከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የታዘብኩትን አጠር አድርጌ ለመቃኘት እሞክራለሁ፡፡ ተሞክሮው በጎ የተሠራውን፣ ጊዜ ወስዶ መዝገብ መርምሮ በምክንያት ወይም ያለምክንያት አያስቀርብም የሚሉትን ተሞክሮዎች ስለማይመለከት የአሠራር ክፍተት ባለባቸው ላይ ማተኮሩ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ አያስቀርብም በሕጉ ያለውን ቦታ፣ ከዳኛው የሚጠበቀውን ሥርዓት፣ በተግባር የሚታዩ ክፍተቶችን፣ የክፍተቶቹን አንድምታ በመቃኘት የሚስተካከልበትን መፍትሔ ለመጠቆም እሞክራለሁ፡፡

ስለ ይግባኝ መብትነት

Continue reading
  13351 Hits

The Effects of a Vacated Arbitral Awards in a Comparative Law Perspective: A Recommendation to Ethiopia

 

 

 

 

Continue reading
  5095 Hits

የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ አግባብነትን በተመለከተ

ግምቱ ተለይቶ የሚታወቅ የፍትሐ ብሔር ክርክር ጉዳይ በመያዝ በፍርድ ቤት ክስ የሚመሰርት ወይም የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የሚያቀርብ ማንኛውም ተከራካሪ በፍትሐብሔር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 215/1 እና ስለ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል በ1945 ዓ/ም በተደነገገው ደንብ መሠረት የዳኝነት ክፍያ ይከፍላል። በዚህ ክሱን በከፈተበት ፍርድ ቤት በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ተከራካሪ ደግሞ የይግባኝ አቤቱታውን ይግባኝ ለመስማት ሥልጣን ወዳለው ፍርድ ቤት ያቀርባል። ይህ የይግባኝ አቤቱታ እንዲሰማለት ደግሞ በሥር ፍርድ ቤት የከፈለውን የዳኝነት ክፍያ 50% መክፈል ይጠበቅበታል። የዚህ አጭር ማስታወሻ ዓላማም የዚህ የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ አግባብ የማይሆንበትን ኹኔታ መጠየቅ ነው።  

ከሶስቱ የመንግሥት አካላት አንደኛው የሆነው ፍርድ ቤት በተለያዩ ምክንያቶች (በማስረጃ ምዘና፣ በሕግ አተረጓጎምና አተገበባበር ወዘተ) ለተገልጋዩ/ለተከራካሪው ተገቢውን እና ትክክለኛውን አገልግሎት/ውሳኔ ባለመስጠቱ ምክንያት ተከራካሪው ውሳኔውን ለማሳረም የሚያወጣው የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ አግባብነት በሁለት ተከፍሎ ሊታይ ይገባል። ይኸውም፣ ይግባኝ ባዩ በሥር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ አግባብ አይደለም ተብሎ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚሻር ከሆነ፣ ቀድሞውኑ ወደ ይግባኝ የሄደው በሥር ፍርድቤቱ ሥህተት ነውና የከፈለው የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ ተመላሽ ሊደረግለት ይገባል። ነገር ግን የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የሚፀና ከሆነ ይግባኝ ባዩ ላገኘው አገልግሎት የዳኝነት ክፍያውን ሊከፍል ይገባል።

ይህ የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ ይግባኝ ባይ ጉዳዩ በይግባኝ ከታየለት በኋላ የረታ ወይም የቀድሞው ውሳኔ የተሻረለት ከሆነ የወጪና ኪሣራ ዝርዝር በማቅረብ ከተረቺው ሊጠይቅ ይችላል የሚል መከራከሪያ ሊቀርብ ይችላል። ነገር ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ የሕጉ አንድምታ እና የሰበር ውሳኔዎች ትርጓሜ ሁል ጊዜ ተረቺ ወጪና ኪሣራ ሊሸፍን ይገባል የሚባለው ከቅን ልቦና ውጪ ሌላኛውን ተከራካሪ ለወጪ የዳረገ ተከራካሪ ካለ ብቻ ነው እንጂ በሁሉም ጉዳዮች ወጪና ኪሣራ ይሸፍናል ማለት እንዳልሆነ መገንዘብ ይቻላል። ከዚህ ባለፈም አሁን አሁን በሰፊው እየተለመደ የመጣው «ግራ ቀኙ ወጪያቸውን ይቻሉ» የሚል ትዕዛዝ ይህ እንዳይቻል ያደርጋል።

በመሆኑም፣ ይህ ሀሳብ ቢተገበር ሁለት ጥቅም አለው። አንደኛው ጥቅም አንድ ተከራካሪ ያለጥፋቱ በመንግሥት አካል (በሥር ፍርድ ቤት) በተሰራበት ስህተት በይግባኝ መንገላታቱ ሳያንስ ለተጨማሪ ወጪ ከመዳረግ የሚያድነው መሆኑ ነው። ከላይ እንደገለፅነው የውሳኔው በይግባኝ መሻር የሚያመላክተው የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሥህተት መሆኑን ነው። ሁለተኛው እና ዋነኛው ጥቅም ግን መንግሥት እንደማንኛውም ግለሰብ እና አገልግሎት ሰጪ ሁሉ ራሱ በዘረጋው አሰራር ከገዛ ራሱ ሥህተት ተጨማሪ ገቢ ማግኘት የለበትም የሚለውን መሠረታዊ የፍትሐዊነት ዕሳቤን በመተርጎም የፍትሕ ተደራሽነትን ማጎልበት ነው።

በአጭሩ የዚህች አጭር ማስታወሻ ድምዳሜ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ታይቶ የተሻረ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የተከፈለ የዳኝነት ክፍያ ለይግባኝ ባዩ ተመላሽ ሊሆን ይገባል የሚል ነው፤ ምክንያቱም ለዚህ ወጪ የተዳረገው በሥር ፍርድ ቤቱ ሥህተት ነውና።

  6230 Hits

በፍትሐብሔር ጉዳይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብቻ በሚደረግ የክርክር ሥነ-ሥርዓታዊ ሂደት የተከራካሪዎች አለመቅረብ ውጤት፡ ሕጉና ትግበራ

 

 

“Law is nothing else but the best reason of wise men applied for ages to the transaction and business of mankind” Abraham Lincoln

 

መነሻ ክስተት

Continue reading
  19110 Hits

የፍርድ አፈፃፀም መሠረታዊ ታሳቢዎችና ያጋጠሙ ችግሮች

 

 

አፈፃፀም ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ በእራሱ አማካኝነት ወደ ተግባር የሚለውጥበት ሥርዓት ነው፡፡ ስለፍርድ አፈፃፀም የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመከተል ፍርድን በተግባር መተርጎም እንደመሆኑ መጠን የማስፈፀሚያ ሥርዓቱ በጥቅሉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ ህጉን መሠረታዊ ዓላማ ተከትሎ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲፈፀም በሚያስችል አኳኋን የተዋቀረ ነው፡፡

ይሁን እንጂ በተግባር እንደሚታየው ክስ አቅርቦ ለማስፈረድ ከሚወሰደው ውጭ ጊዜና ጉልበት ባልተናነሰ ሁኔታ የተፈረደን ፍርድ ለማስፈፀም የሚጠይቀው ወጭና ጊዜ በልጦ የሚታይበት ጊዜ ይከሰታል፡፡ ምክንያቶቹ በርካታ ናቸው፡፡

ከነዚህም ጥቂቶቹ፡-

Continue reading
  17128 Hits

የልማድ አቤቱታ የፍርድ ጥራት ላይ ያለው ተፅዕኖ

 


መነሻ ነገር

መኳንንት ከሕግ ትምህርት ቤት ተመርቆ ሲወጣ ግር ያለው ነገር የትምህርቱና የአተገባበሩ ልዩነት ነው፡፡ በአብዛኛው በንድፈ ሐሳብ አስተምህሮና ትንተና ላይ የሚተኮረው ትምህርቱ በተግባር ከሚታየው የፍርድ ቤት ነባራዊ ሁኔታ ጋር አልታረቅ ብሎት ተቸግሯል፡፡ ይህን ችግሩን ያባባሰው ደግሞ ከቤተሰቡ አንዱ የወራሽነት የምስክር ወረቀት ከፍርድ ቤት እንዲሰጠው በማሰብ አቤቱታውን እንዲያዘጋጅለት ሲጠይቀው ነው፡፡ አቤቱታውን አዘጋጅቶ ለቤተሰቡ አባል ቢሰጠውም በአንዱ ክልል ከሚገኘው የወረዳ ፍርድ ቤት የገጠመው ነገር ሌላ ነው፡፡ ቤተ ዘመዱ በፍርድ ቤቱ አቤቱታው በትክክል አለመጻፉ ተነግሮት በፍርድ ቤቱ ደጃፍ ከሚገኙት ራፖር ጸሐፊ ተጽፎ እንዲመጣ ተመከረ፡፡ ሰውየውም የተባለውን ፈጽሞ አቤቱታው ተቀባይነት አግኝቶ የወራሽነት የምስክር ወረቀት አገኘ፡፡ የመኳንንትና የራፖር ጸሐፊው አቤቱታ ልዩነት ቀላል ነበር፡፡ የመኳንንት አቤቱታ ፍሬ ነገሩን በአጭር የሚገልጽ፣ የሕግና የማስረጃ ትንተና የሌለው፣ ግልጽ ዳኝነትን የሚጠይቅ ነበር፡፡ የራፖር ጸሐፊው አቤቱታ ግን ረዥም፣ ውስብስብ የሕግ ቃላትን የሚጠቀም፣ በብዙ የሕግ ድንጋጌ የተዘበዘበ ነበር፡፡ ይህን የተረዳው መኳንንት አምስት ዓመት የተማረበት የሕግ ትምህርት ሥልጠና የማይፈልግና በፍርድ ቤት ተግባራዊ ረብ የሌለው መስሎት ተከዘ፡፡ የተወሰኑ ዓመታትን በሕግ ሙያ አገልግሎት ካሳለፈ በኋላ ግን ለዘመናት የዳበረውን ልምድ መስበር አስቸጋሪ ስለመሰለው ራሱን በተወሰነ ደረጃ ከተለመደው አሠራር ጋር አቀራረበ፡፡ አሁን ለአቤቱታ ርዝመት ጭንቀት የለውም፣ የሕግ ድንጋጌዎችን በዓይነት ለመዘብዘብ፣ የሕግና የማስረጃ ትንታኔዎችን ለማግተልተል ቀዳሚ አይገኝለትም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍርድ ቤቶች የአሠራር ማሻሻያ በማድረግ፣ የሬጅስትራርና ተያያዥ ሥራዎችን የሚሠሩ ሰዎች ከሕግ ትምህርት ቤት የተመረቁ፣ የሕግ ሥልጠና ያገኙ መሆናቸው የተወሰነ ለውጥ ማምጣቱን ያምናል፡፡ ያም ሆኖ አሁንም የአቤቱታ ፎርም፣ ይዘት፣ እና ሕጋዊ ብቃት አሰፋፈር/አተያይ ላይ ምሉዕ ለውጥ አለመምጣቱን መኳንንት ያምናል፡፡ ሰሞኑን ያጋጠመው የሬጅስትራር ሠራተኞች ድርጊት ለዚህ አስረጅ ነው፡፡ መኳንንት ሕጉን ተከትሎ ያዘጋጀውን የመከላከያ መልስ ምንም ዓይነት የሕግ ድንጋጌ ያልጠቀሰ መልስ የሕግ አቤቱታ አይሸትም ሲሉት እጅጉን ተበሳጨ፡፡ ጸሐፊውም ይህን በሰማ ጊዜ ትንተና ባይበዛውም በዚህ ጽሑፍ የአቤቱታን ምንነት፣ መሥፈርት፣ የብቃት አተያይ በአጭሩ ለግንዛቤ በሚመች መልኩ ለመዳሰስ ሙከራ አደረገ፡፡

አቤቱታ ምንድን ነው?

በዕለት ተዕለት የሕይወት ተሞክሮ ለማንኛውም አካል በቃል ወይም በጽሑፍ የሚቀርብ ጥያቄ፣ ማመልከቻ፣ ይግባኝ አቤቱታ ይባላል፡፡ በሕግ ሙያ ግን ‹‹አቤቱታ›› ወይም ‹‹Pleading›› የሚለው ቃል በፍርድ ቤት የሚቀርብ ማመልከቻን ሁሉ የሚያካትት አይደለም፡፡ ፍርድ ቤት ለመዋሉ ማስረጃ የሚጠይቅ፣ የውሳኔ ግልባጭ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ወዘተ በሕጉ ቃል አቤቱታ አቅርቧል ለማለት አያስችልም፡፡ ለቃሉ ፍቺ የሚሰጠው ብላክስ የሕግ መዝገበ ቃላት ‹‹Pleading is a formal document in which a party to a legal proceeding (esp. a civil lawsuit) sets forth or responds to allegations, claims, denials or defenses›› በሚል ይገልጸዋል፡፡ በዚህ ትርጉም መሠረት አቤቱታ ማለት በአንድ የሕግ ሙግት ተከራካሪ የሆነ ወገን ሙግት ለመጀመር ወይም ለቀረበ ጥያቄ፣ ዳኝነት፣ ክህደት ወይም መከላከያ መልስ ለመስጠት የሚያቀርበው መደበኛ ሰነድ ነው፡፡ በዚህ ፍቺ መሠረት አቤቱታ መብት የሚጠየቅበት ወይም ለቀረበ ጥያቄ መልስ የሚቀርብበት ነው፡፡

Continue reading
  10297 Hits

በቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት ያለመቅረብ ውጤቶች

 

ተከራካሪ ወገኖች እራሳቸው ወይም በተወካያቸው አማካይነት ፍርድ ቤት በሚወስነው በማንኛውም ቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሳሽ አንድ ጊዜ ጉዳዩን ይዞ ከቀረበ በኋላ ተከታትሎ ከዳር ማድረስ መቻል ያለበት ሲሆን ተከሳሽም በእያንዳንዱ ቀጠሮ እየቀረበ የቀረበበትን ክስ በአግባቡ መከላከል መቻል አለበት፡፡ክስ ያቀረበ ሰው በሁሉም ቀጠሮዎች ንዲገኝ የሚጠበቅበት ቢሆንም በተያዘው ቀጠሮ ባለመገኘቱ ምክንያት ያቀረበውን ክስ መዝጋት ጨምሮ እንደ ቀጠሮው ምክንያት ሌሎች ትእዛዞች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ክሱ ሊዘጋ የሚችለው ሕጉ ለይቶና ዘርዝሮ ባስቀመጣቸው ምክንያቶችና ጋጣሚዎች ብቻ ነው፡፡ የፍርድቤት ክርክር በከሳሽ እና ተከሳሽ ይሁንታ ላይ ተመስርቶ በፈለጉ ቀን የሚቀርቡበት ደስ ካላላቸው ደግሞ የማይቀርቡበት ሂደት አይደለም፡፡

ንድን ጉዳይ ለማየት የተሰየመ /ቤት የተለያዩ ክንዋኔዎችን ለመፈፀም በርካታ ቀጠሮዎች ንደሚሰጥ የታወቀ ነው፡፡ በሙግት ሂደት ፍርድ ቤት የተለያዩ ጉዳዮች መከናወናቸውን ለማረጋገጥ የተለያዩ ቀጠሮዎችን ይሰጣል ይላል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር 14184፡፡ ንድን ጉዳይ ይቶ ውሣኔ ለመወሰን በርካታ ቀጠሮዎችን ፍርድ ቤት ንደሚሰጥ የሚታወቅ ሲሆን ከነዚህ በርካታ ቀጠሮዎች መካከል ንዱ ወይም በሌላኛው ወይም በሁለቱም ለመቅረብ ምክንያት ፍርድ ቤት የተለያዩ ትዕዛዞችን እንደሚሰጥ አትቶታል መዝገቡ፡፡ የቀጠሮ ለመከበር ቀጠሮ ከተሰጠበት ምክንያት ተነጥሎ የሚታይ ባለመሆኑ የቀጠሮውን ምክንያት ከግምት በማስገባት የሚሰጠውም ትእዛዝ የተለያየ ነው፡፡

አንድ የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ተከራካሪ ወገኖች ክሱ በማንኛውም ደረጃ ላይ ባለበት ጊዜ መቅረብ ባይችሉ ተፈፃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ድንጋጌዎች ነዚህን ሁኔታዎች በቅጡ ለመገንዘብ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጋችን የከሣሽ ና/ወይም የተከሣሽ ለመቅረብ (non appearance of parties) ስመልክቶ ያስቀመጠውን ሥርዓት ጠቃላይ የሙግት ሂደት ጋር ገናዝቦ መመልከቱ ጠቃሚ ነው ይላል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በተመለከቱ ፍርዶቹ፡፡

በዚህ ጽሑፍም ፍርድ ቤት ከሚሰጣቸው የተለያዩ ቀጠሮዎች እና ውጤታቸው ጋር በተያዘ የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉን ድንጋጌዎች እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

Continue reading
  22229 Hits