የቼክ ክፍያ ይቁም ትዕዛዝ (Stop Payment Order) የሚሰጠው መቼ እና እንዴት ነው?

ቼክ ጥሬ ገንዘብን ተክቶ በመገበያያነት አገልግሎት ላይ የሚውል የሚተላለፍ የንግድ ወረቀት አይነት ነው። በሀገራችን በቼክ መገበያየት እጅግ የተለመደ ተግባር ሲሆን ቼክም ሌሎች የሚተላለፉ የንግድ ሰነዶች ካላቸው እውቅናና ተቀባይነት በላቀ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለ እና በህብረተሰቡም ዘንድ እውቅና ያለው ሰነድ ነው። በሰነዱ ላይ ህብረተሰቡ የጣለው እምነትና በስፋት አገልግሎት ላይ መዋሉም በሰነዱ ላይ በተለያዩ ጊዜያት እና በስፋት የፍርድ ቤት ክርክሮች እንዲነሱ አንዱ ምክንያት እንደሆነ እሙን ነው። ታዲያ በዚህ ሰነድ በስፋት አገልግሎት ላይ መዋልና በሕጋችን ውስጥ ሰነዱን አስመልክቶ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ማሻሻል እና ክፍተቱን መሙላት አስፈላጊና ለሰነዱ ቀጣይነትም አስተማማኝ ዋስትና ነው።

  18246 Hits

 አንድ አንድ ነጥቦች ስለ ቼክ እና በተግባር የሚያጋጥሙ የሕግና የአሰራር ችግሮች

ቼክ በተግባር በሰፊው ከሚሰራባቸውና በሕግ ከተቀመጡት ንግድ ሰነዶች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡  በቼክ ላይ እምነት የሚታጣበት ከሆነ የንግድ ዝውውር ደህንነት (security of transaction) ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ የንግድ ሥራው እያደገ በመጣ ቁጥር በቼክ የሚደረጉ የንግድ ልውውጦች የሚጨምሩ እንደሚሆን የሚታመንና በተግባርም የሚታይ ነው፡፡ የቼክ ዝውውር እየጨረ እንደመጣም መገመት አያዳግትም፡፡ እየጨመረ የመጣውን የቼክን ዝውውር አስተማማኝነት ለማሳደግ ሕጎች ሥርዓቱን ሊቆጣጠሩት ይገባል፡፡ በዚህም መሠረት በእኛ ሀገር የንግድ ሕጉ እና የወንጀል ሕጉ ይህንኑ የቼክ ጉዳይ በዋናነት ይህን ሥርዓት ዘርግተው ይገኛሉ፡፡ ባብዛኛው የቼክ ጉዳይ የሚያከራክር ጉዳይ የሌለበት ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን አከራካሪ ጉዳዮች መታየታቸው አልቀረም፡፡ ይህ ጽሑፍ ዓላማውም በቼክ ዙሪያ ያሉትን አስፈላጊ የሕግ ድንጋጌዎችንና አስገዳጅ የፍርድ ውሳኔዎችን ማሳወቅና በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለአከራካሪ ጉዳዮች የጸሐፊውን እይታ ማንፀባረቅ ነው፡፡

  23890 Hits
Tags: