ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ ዕይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ
Sesay Goa
Criminal Law Blog
መግቢያ ፡- ተበዳዮች በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ የነበራቸው የተሳትፎ ሚና፡ ጥቅል ምልከታ በኢትዮጵያ የወንጀል ተጎጂዎች በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ያላቸው ሚና ከነበረበት የማማ ደረጃ በጊዜ ሂደት ‹‹ከማማ የመውረድ›› ያህል ዝቅ እያለ መጥቷል። ሀገሪቱ በዳግም የኢጣሊያ ወረራ ተፈፅሞባት ከመያዝዋ እ.እ.አ ከ 1935 ዓ.ም በፊት በወንጀል ጉዳት ደርሶባቸው በቀጥታ ተበዳይ የሆኑ ሰዎች ወይም የተበዳይ ተወካይና ቤተዘመዶች በደል ካደረሰባቸው ሰው ፍትሕን በገዛ እጃቸው ያገኙ ነበር። ተበዳይ ጥቃት ያደረሰበትን ሰው ሲፈልግ ይበቀላል፣ ሲፈልግ በፍርድ አደባባይ ይከሳል ወይም ለደረሰበት በደል ከተበዳይ ከሳ ይቀበላል። አይ ይህን ሁሉ አልፈልግም ካለም ከሁሉም ታቅቦ ፍትሕን ከእግዚአብሔር እየጠየቀ ይኖራል። በዚህ ጊዜ ምርመራ አጣርቶ ክስ የሚመሰርት የዐቃቤ ሕግ ተቋም በሀገሪቱ አልነበረም። በግለሰቦች መሀከል የሚፈጠር አለመግባባቶችን ‹‹የወንጀል›› ጉዳይ እና የግለሰቦች የፍትሐብሔር ጉዳይ ብሎ የሚከፋፍል የሕግ ስርአት ባለመኖሩ ጥቂት በሀይማኖትና በመንግስት ላይ የሚፈፀሙ በአሁኑ ሰአት የፓለቲካ ወንጀል እየተባሉ ከሚጠሩ ወንጀሎች በስተቀር ሁሉም አለመግባባቶች ላይ ግለሰቦች በራሳቸው ከሳሽ በመሆን ጉዳያቸውን ለፍርድ ቤት ያቀርባሉ ወይም ፍትሕን በእጃቸው ያገኙ ነበር። ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት የሚወስዱ ከሆነ ክስ የመመስረት፣ የተጀመረን ክስ የሟቋረጥ፣ ቅጣትን በመምረጥ ተበዳይ ግለሰብ ሁሉን አድራጊ ነበር። የወንጀል ይዘት ያላቸው ጉዳዮችን ከፍትሀብሔር ጉዳዮች ጋር በማጣመር የጉዳት ካሳን መጠየቅም ይቻል ነበር። በዘመኑ የወንጀል ተበዳዮች በወንጀል ጉዳይ የሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች ነበሩ።
Continue reading
ዳኞች፣ ዐቃቤ ሕጎች፣ ጠበቆች እና ፖሊሶች ሊዘነጓቸው የማይገቡ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ መርህዎች
Liku Worku
Criminal Law Blog
መንግሥት የሃገርን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ እና የማስጠበቅ እንዲሁም የሕዝቦቹን እና የነዋሪዎቹን መሠረታዊ የግለሰብና የቡድን ነፃነት መብት እና ጥቅም የማክበርና የማረጋገጥ ግንባር ቀደም ኃላፊነትና ሚና አለበት፡፡ ይህንን ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል በግልጽ በሚመራ ሥርዓት የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ማዕቀፍን መዘርጋትና ማቋቋም አንዱና ዋነኛው ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ማዕቀፍን ከሚያቋቁሙ ምሰሶዎች መካከል የወንጀል ሕግ፣ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ እና የማስረጃ ሕግ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡
Continue reading