Prosecution for Several Counts Resulting from a Single Criminal Act

Abstract

It is inevitable fact today that one criminal act can inflict upon several victims harm of certain nature. In doing so the criminal act though flowing from the same criminal intention or negligence and violating the same criminal provision may cause the same harm against the rights or interests of more than one person. In such instances the law dictates the liability to be equalled with the numbers of victims though the practice shows divergence among courts and also between prosecutors.

 

1.  Introduction

 

Continue reading
  16601 Hits
Tags:

Criminalizing and Prosecuting Illicit Enrichment in Corruption Cases

Corruption is becoming a major threat to the world. All countries of the globe are running the risks associated with it. Corrupt practices such as bribery and other abuses of public functions for private gain have been criminalised in almost all legal systems. Criminalisation of acts of corruption constitutes one of the major dimensions of the international anti-corruption instruments.

The clandestine nature of corruption crimes creates difficulties in gathering evidence for prosecution and effective implementation of the law. To overcome such problems, some indicators of corruption such as possession of property that far exceeds legitimate sources of income need to be criminalised. It is also imperative to deal with the challenges associated with such criminalisation. The international community, in combating corruption, calls upon states to outlaw and criminalise certain acts of corruption, and illicit enrichment is one of them. Since not all states of the world have criminalised illicit enrichment under the ambit of their anti-corruption legislation, this study mainly addresses the importance of its criminalisation so as to fight corruption in a broader and more effective way.

This article tries to analyse the challenges related to due process of law in the investigation and prosecution of illicit enrichment. Further, complexities associated with the process of recovering illicitly acquired assets, such as resources and expertise, as well as effective co-operation among various jurisdictions, need to be explored.

By giving special emphasis to the Ethiopian legal framework on the matter, the nature of the offence, its prosecution, and the challenges associated with recovering the proceeds of the crime, especially such proceeds as have already gone from the country, will be considered. In this regard, the effectiveness of the law in contributing towards the effort to eradicate corruption is the central point.

In addition to the law relating to the offence of illicit enrichment, the article analyses the Ethiopian anti-corruption laws and their effectiveness in combating corruption.   

Continue reading
  12286 Hits

ወንበዴ ማነው? ውንብድናስ ምንድነው?

የተከበራችሁ አንባቢዎች ለዛሬው ርዕሰ አንቀፅ መነሻ የሆነኝ የውንብድና ወንጀልን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች በአግባቡ ባለመረዳት ወይም በተለያዩ መልኩ በመተርጎም የሚፈፀሙ የክስ አመሰራረት ልዩነቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ያለውን አሰራር እና አንቀፁን እኔ በምረዳው መልኩ በማቅረብ ለአንባቢዎቼ እንደሚከተለው ለውይይት እና አስተያየት ክፍት አድርጊያለሁ፡፡

የቀድሞ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 636 ስር ተደንግጎ የነበረ ሲሆን በዚህም አንቀፅ መሰረት ወንበዴነት “የስርቆት ወንጀል ለመስራት አስቦ ወይም በስርቆት ወንጀል ተይዞ ወይም ደግሞ በስርቆት ያገኘውን ነገር ለመሰወር በማሰብ” የሃይል ተግባር ፈፅሞ እንደሆነ ተደንግጎ ይገኝ ነበር፡፡ በመሰረቱ ይህ ድንጋጌ ተሻሽሎ በ1996ቱ የወንጀል ህግ ውስጥ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ በአንቀፁ ላይ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት የስርቆት ወንጀል የሚፈፀመው ባለንብረቱ ወይም ሌላ ሰው እንደማያየው ወይም እንደማይዘው በማረጋገጥ ስለሆነ የሰውን ንብረት ከመውሰድ ጋር የሃይል ተግባር ከተጣመረ የንብረት አወሳሰዱ ስርቆት መሆኑ የሚቀር በመሆኑ መሆኑን የወንጀል ህግ ሐተታ ዘምክንያት ያትታል፡፡

በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ መሰረት ውንብድናን ከስርቆት አንፃር መቶረጎሙን በመተው ውንብድና እንደሚከተለው ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ማንም ሰው ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስቦ፣ የሌላ ሰው ንብረት የሆነውን ተንቀሳቃሽ ዕቃ ለመውሰድ እንዲያመቸው ወይም በሚወስድበት ጊዜም ሆነ ከወሰደ በኋላ የገጠመውን ተቃውሞ ውጤታማነት ለማስቀረት ሲል በሌላ ሰው ላይ የኃይል ድርጊት ወይም ከባድ የሆነ የማገላታት ተግባር ወይም ከባድ ዛቻ የፈጸመ፣ ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ ይህን ሰው ለመከላከል እንዳይችል ያደረገው ሲሆን ከአሥራ አምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እሥራት ይቀጣል፡፡

በመጀመርያ ደረጃ ውንብድና የሚፈፀመው ተገቢ ያለሆነ ብልፅግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት መሆን ይኖርበታል፡፡ የማይገባውን ብልፅግና የማግኘት ሃሳብ ተንቀሳቃሽ እቃ ለመውሰድ እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት በመውሰድ ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ከሃሳቡ ቀጥሎ የሚመጣው ውንብድናን የሚያቋቁመው የወንጀል ፍሬ ነገር የሌላ ሰው ንብረት የሆነውን ተንቀሳቃሽ ዕቃ ለመውሰድ እንዲያመቸው ወይም በሚወስድበት ጊዜም ሆነ ከወሰደ በኋላ የገጠመውን ተቃውሞ ውጤታማነት ለማስቀረት የሃይል ወይም የዛቻ ተግባር መፈፀም ነው፡፡ በአንዳንድ ክሶች ላይ እንደሚታየው ከሆነ ውንብድና ተፈፀመ የሚባለው ንብረት ተወስዶ እንደሆነ ነው፡፡ ነገር ግን በወ/ህ/ቁ. 670 ላይ በግልፅ እንደተደነገገው ተንቀሳቃሽ ዕቃ ለመውሰድ እንዲያመቸው ብሎ ብቻ የሃይል ተግባር መፈፀም በራሱ ወንጀሉን ያቋቁማል፡፡

Continue reading
  10767 Hits
Tags:

በኢትዮጵያ ሰው በፍርድ ቤት እና ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ስለሚያዝባቸው ሁኔታዎች

በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርአት ውስጥ የወንጀል ምርመራ አላማ ስለ ወንጀል የማወቅ፣ ወንጀል እንዳይፈፀም የማስቆም፣ ወንጀሉ ከተፈፀመ ጉዳቶችን የመቀነስ፣ የወንጀል ኢላማ የሆኑትን ሰዎች፣ ንብረቶች ወይም ጥቅሞችን የመከላከል፣ ወንጀል ፈፃሚዎችን ለሕግ የማቅረብ ወይም የወንጀል ተጎጂዎችን መብቶችና ጥቅሞችን ማስከበር እንደሆነ የኢትዮጵያ ወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ ይገልፃል፡፡ ጠበብ አድርገን ስናየው ደግሞ የወንጀል ምርመራ (Investigation) ማለት የአንድን ወንጀል መፈፀም ወይም አለመፈፀም እንዲሁም ማን እንደፈፀመው ለማረጋገጥ የሚረዳ ማስረጃን የማሰባሰብ ሂደት ነው፡፡ ፖሊስም ይህን ተግባር ሲያከናውን  ሕገ መንግስቱ፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርአት ህጉና ሌሎች ህጎች ባስቀመጡት ድንጋጌዎች መሠረት ማከናወን የሚገባው ሲሆን፣ በዚህ ሂደት የሚኖር የመብት ጥሰት ካለም ተጠያቂነትን ያመጣል፡፡  ወንጀል ከተሰራ በኋላ ፖሊስ በሁለት መንገድ ምርመራ ሊጀምር ይችላል አንደኛው ግለሰቦች ወንጀል ተፈፀመብኝ ብለው በሚያቀርቡት አቤቱታ መሠረት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የወንጀሉ ድርጊት ከፈተፈፀመ በኋላ ወንጀሉ ሲፈፀም ያዩ ወይም የሰሙ ግለሰቦች በሚያደርሱት ጥቆማ መሠረት ነው፡፡

ፖሊስ ከላይ በገለፅነው መልኩ መረጃ ደርሶት ምርመራ ሲያከናውን የምርመራው አካል የሆነው አንዱና በጥንቃቄም መከናወን ያለበት ተግባር ተጠርጣሪውን መያዝ ነው፡፡ ምክንያቱም የወንጀል ድርጊት እስከተፈፀመ ድረስ የህብረተሰቡን ህይወት፣ ንብረትና ሰላም ለመጠበቅ ሲባል ወንጀል ፈፃሚዎችንና የወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡ ፖሊስ እስርን ተግባራዊ ለማድረግ በሁለት መንገድ ማለትም በፍርድ ቤት ትእዛዝና ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ናቸው፡፡ በመርህ ደረጃ ያለመያዝ ወይም ያለመታሰር መብት ሕገ መንግስታዊ ከለላ ያገኘ መብት በመሆኑ ከመያዝ ጋር ተያይዞ የሚከናወኑ ተግባራት በጥንቃቄ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

በዚች አነስተኛ ጽሑፍ መያዝ (arrest) ምንነትና ጥቅሙ፣ መያዝ በሀገራችን እንዴት እንደሚተገበርና በሀገራችን ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል ለማየት ጥረት የሚደረግ ሲሆን እንዲሁም በቀጣይ መያዝን አስመልከቶ ቢስተካከሉ ወይም በሕግ ደረጃ የሕግ ሽፋን ቢሰጣቸው የምላቸውን ሀሳቦች በአስተያየት መልኩ አቀርባለሁ፡፡

ስለመያዝ (arrest) ምንነት

ስለ መያዝ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግም ሆነ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርአት ሕግ ላይ ትርጉም ያልተሰጠው ሲሆን፣ በሌሎች የተለያዩ ሰነዶች ላይ የተሰጠውን ትርጉም ስንመለከት፣ ብላክ ሎው ዲክሽነሪ arrest የሚለውን ፅንሰ ሀሳብ ” it is a seizure or forcible restraint, the taking or keeping of a person in custody by legal authority especially in response to criminal charges”.  መያዝ ወይም በሀይል ይዞ ማቆየት ማለት አንድን ሰው በተለይ ለወንጀል ክስ መልስ እንዲሰጥ በህጋዊ ባለስልጣን ወደ ማቆያ መውሰድ ወይም መጠበቅ ማለት ነው በማለት ተርጉሞታል፡፡

Continue reading
  10463 Hits
Tags:

የዞን ዘጠኝ አምስት ተከሳሾች ክስ መቋረጥ ብዥታ

መግቢያ

 

መጠይቅ ደግ ነው፡፡ የአስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባራትን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 16(6) ፍትሕ ሚኒስቴር በቂ ምክንያት ሲኖር በሕግ መሠረት ሂደት ላይ ያለን ክስ ያነሳል በሚል ይደነግጋል፡፡ ፍትሕ ሚኒስቴር የተሰጠው ክስ የማንሳት ሥልጣን እስከምን ድረስ ነው? ክስ ማንሳት በማንኛውም ጊዜ ይቻላል? ክሱን ሲያነሳስ በቂ ምክንያቱን ለፍርድ ቤቱ ያቀርባል? በቂ ምክንያትስ የምንለው ምንድን ነው? የክስ መነሳትስ ተከሳሾች ላይ ያለው ውጤት ምንድን ነው? በዚህ ሂደት የፍርድ ቤቶች ሚና ምን መሆን ይገባዋል? የሚለው ጥያቄ ሊመለስ የሚገባው ነው፡፡

ክስ ማንሳት ለምን?

ፍትሕ ሚኒስቴር ከሳሽ አካል እንደመሆኑ ወንጀል ጉዳይ ተፈፅሟል ብሎ ሲያመን ክስ እንደሚመሰርተው ሁሉ ምክንያት ሲኖረው ክሱን ሊያነሳ እንደሚችል በአዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ክስ የሚነሳባቸው ምክንያቶች በሕግ ተዘርዝረው ያልተቀመጡ በመሆናቸው ለክርክር ምክንያት መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ ሆኖም ግን ክስ ለማንሳት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ከሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ በአንድ በኩል ቀጥታ ከክሱ ጋር በተገናኘ ቀጥተኛ ምክንያት ሲሆን ሕጋዊ ምክንያት በማለት ሊገለፅ የሚችል ነው፡፡ በሌላ በኩል ከክሱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የሌለው ፖለቲካዊ ምክንያት ነው፡፡ ሕጋዊ ምክንያት የምንለውን ከስሩ የሕግ ፍልስፍና ስናስበው ነፃ ሰው ጥፋተኛ እንዳይባል ወይም ወንጀል አድራጊ መቀጣት እያለበት ከሕግ እንዳያመልጥ የሚቀርብ ነው፡፡ እነዚህ ምክንያቶች ቀጥታ ከሳሹ አካል ከሚያቀርባቸው ማስረጃ ጋር የሚገናኙ ናቸው፡፡ ከሳሽ ማስረጃ በደንብ ወይም በአግባቡ ካለመሰብሰቡ በትክክል ወንጀል የሠራ ተከሳሽ ነፃ ሊባል የሚችልበት ሁኔታ ስለሚኖር ማስረጃ አሰባሰብ ላይ እርምት በማድረግ ለዳግም ክስ ለመዘጋጀት ትንፋሽ መግዣ ነው፡፡ ልብ ልንለው የሚገባው ክስ የሚነሳው ፍርድ ከመስጠቱ በፊት በመሆኑ ዳግም ክስ ከማቅረብ የሚከለክል አይደለም፡፡ ክስ ማንሳት ከዳግም ክስ ካልገደበ ከሳሽ ጎደለ የሚለውን ማስረጃ እንደገና ለማጠናከር እንዲያውም ክሱ ከተጀመረ በኋላ ማስረጃ ይሆነኛል የሚለው አዲስ ማስረጃ የተገኘ ሲመስለው ክሱን አንስቶ እንደገና ክንዱን አፈርጥሞ ለመመለስ መሽሎኪያ የሚሆነው መንገድ ነው፡፡ በተጨማሪም ነፃ ሰው ባልሠራው ወንጀል ጥፋተኛ እንዳይባልም ክስ ለማንሳት መነሻ ምክንያት ይሆናል፡፡ ነፃን ሰው ለማዳን ክስ ለማንሳት የሚበረቱት እንኳ አንድ ነፃ ሰው ጥፋተኛ ከሚባል ሺህ ወንጀለኞች ቢያመልጡ ይሻላል የሚል መርህ ያላቸው አገሮች ናቸው፡፡

Continue reading
  9084 Hits

የኢትዮጵያ የይቅርታ ሕግ አንዳንድ ነጥቦች

 

 

“…ይቅርታ ይደረግልን አዲስ የኢትዮጵያ ባህል ነው፡፡”

                         የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕ/ት ኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም

መግቢያ

Continue reading
  12245 Hits

በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ወንጀለኛን (ተጠርጣሪን) የመያዝ አጠቃላይ አካሔድ

 

በዚህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ የወንጅል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር ስለመዋል ወይም ስለመያዝ የሚመለከቱ መሠረታዊ ጉዳዮችን ለማብራራት ጥረት ተደርጓል፡፡ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን የሰዎች የነፃነት መብትና በፖሊስ በወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ስለመዋል መካከል ስላለስ ግንኙነት በትንሹ ገለፃ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎች የሚያዙባቸውን መንገዶችና እንዴት በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ የሚደነግገውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ክፍል በጥልቀት ለመርመር ሙከራ ተደርጓል፡፡

የመያዝና የሕገ መንግሥቱ የነጻነት መብት ግንኙነት

የኢ... ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17 (1) ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ነፃነቱን እንደማያጣ በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ይህም ማለት በንዑስ አንቀጽ (2) እንደተብራራው ማንኛውም ሰው ክስ ሳይቀርብበበት ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰር እንደማይችል ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን በሌሎች ሕጎች በግልፅ በተደነገጉ ሁኔታዎች የዜጎች የነፃነት መብት ሊገደብ እንሚችል የሕገ መንግሥቱ ‹‹በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ›› የሚለው አገላለፅ ያሳያል፡፡ በመሆኑም  በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት ማንኛውም የወንጀል ድርጊት የፈፀመ ሰው ወይም በወንጀል ድርጊት የተጠረጠረ ሰው በፖሊስ የሚያዝበት አግባብ ሊፈጠር እንደሚችል መረዳት ይቻላል፡፡  ይህም ሲሆን ወንጀሉን የፈፀመው ሰው የሕገ መንግሥቱንላማና መንፈስ በጠበቀ መልኩ ነፃነቱ መገደቡን መረዳት እንችላለን፡፡ ከዚህ በመቀጠል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ እውቅና የተሰጣቸውና በአሁኑ ሰዓት በማገልገል ላይ የሚገኙትን ወንጀለኛን የመያዣ መንገዶችን እንዲሁም የአያያዝ ሥርዓቶች እንቃኛለን፡፡

በኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ወንጀለኛን የመያዣ መንገዶች

Continue reading
  11866 Hits

አዲሱ የፀረ ሙስና ሕግ በግል ኩባንያወች ላይ ተፈፃሚነቱና የሕግ አንድምታው

 

“Nothing will unlock Africa’s economic potential more than ending the ‘Cancer of Corruption”

Barack H. Obama, US President key note to African Union July 28 2015

 መግቢያ

ሙስና የአለማችን ብሎም የሀገራችን ስጋት እና የመነጋገሪያ አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ሀገራትም የሙስና ትግሉን ከግብ ለማድረስ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት እንቅስቃሴውን ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡

Continue reading
  21932 Hits

የረዳት አብራሪው ኃይለመድህን አበራ የወንጀል ክስ ጉዳይ በየትኛው አገር ፍ/ቤት መታየት አለበት?

ፌቡራሪ 17/2014 እ.ኤ.አ. ዕለተ ሰኞ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ በበረራ ቁጥር ET 702 የተመዘገበ ቦይንግ 767 የመንገደኞች ማመላለሻ አውሮፕላን ከአዲስ አበባ በሱዳን በኩል አድርጎ ወደ ጣሊያን ሲበር በረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ተገድዶ ስዊዘርላንድ ጄኔቭ ማረፉን ተከትሎ የስዊዘርላንድ መንግስት ረዳት አብራሪውን ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደማይሰጥና በስዊዘርላንድ መንግስት የህግ ከለላ እንደሚደረግለት እንዲሁም ረዳት አብራሪው ያቀረበው የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄም ከፍርድ ሂደቱ በኋላ ምላሽ እንደሚያገኝ ጉዳዩም በስዊስ ሃገር ፍ/ቤት የሚዳኝ መሆኑን መግለጹን ከተለያዩ ሚዲያዎች መገንዘብ ችለናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራል አቃቤ ህግ የወንጀል ህግ 507(1)ን በመተላለፍ አውሮፕላንን ያላግባብ መያዝ ወይም ማገት ወንጀል እና የወንጀል ህግ አንቀጽ 508(1)ን በመተላለፍ አውሮፕላንን አስጊ ሁኔታ ላይ መጣል ወንጀል ፈጽመሟል በማለት በረዳት አብራሪው ኃይለመድህን አበራ ላይ ሁለት የወንጀል ክሶችን መስርቷል፡፡

ተከሳሹም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ቢደረግለትም ሊገኝ ባለመቻሉ (ለፎርማሊቲ እንጂ በጋዜጣ ጥሪ እንደማይመጣ ይታወቃል) ጉዳዩ በሌለበት መታየቱ ቀጥሎ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ፍ/ቤቱ በቀን 07/07/07 ዓ/ም በዋለው ችሎት በወንጀል ህግ አንቀጽ 507(1) ስር አውሮፕላንን ያላግባብ መያዝ ወንጀል ስር ጥፋተኛ ነው ብሎ ሲወስን በሁለተኛው ክስ ግን ነፃ ነው ብሎታል፡፡

እዚህ ላይ ሊነሳ የሚገባው ዋና ጥያቄ የስዊዘርላንድ መንግስት ረዳት አብራሪውን አሳልፌ አልሰጥም የፍርድ ሄደቱ በስዊዘርላንደስ ሃገር ይታያል ባለበት ሁኔታ የፌደራል ዓቃቤ ህግ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በረዳት አብራሪው ላይ የወንጀል ክስ ማቅረቡና ፍ/ቤቱም ጉዳዩን ተቀብሎ ማስተናገዱ ከወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህጋችን እና ከወንጀል ህጋችን አኳያ ሲታይ አግባብ ነው ወይ? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት እወዳለሁ፡፡

በኢትዮጵያ መርከብም ሆነ በኢትዮጵያ አውሮፕላን ላይ ከኢትዮጵያ ግዛት ውጪ የሚፈጸም ወንጀልን በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንደ ተፈጸመ ይቆጠራል ተብሎ በወ/መ/ስ/ስ/ህጋችን አንቀጽ 104 ላይ ተደንግጓል፡፡ በኢትዮጵያ ግዛት የተፈጸመን ወንጀልን ለመዳኘት የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች የዳኝነት ስልጣን እንዳላቸው ቅቡል ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ተፈጸመ የተባለው ወንጀል ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነው በበረራ ቁጥር 706 ቦይንግ 767 ላይ በመፈጸሙ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 104 መሠረት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንደተፈጸመ ስለሚቆጠር የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ረዳት አብራሪው የፈጸመውን ድርጊት በተመለከተ የሚቀርቡለትን የወንጀል ክሶች ተቀብለው ማስተናገድ ይችላሉ በማለት በቀላሉ ድምዳሜ ላይ ልንደርስ እንችላለን፡፡

Continue reading
  13738 Hits
Tags:

Mediating Criminal Matters in Ethiopian Criminal Justice System: The prospect of Restorative Justice

In Ethiopia, the use of mediation process as a traditional method of dispute resolution has been practiced for centuries. Even today in rural areas, particularly criminal dispute resolution processes dealing with victims and criminal offenders are widely practiced and deep rooted with varying degrees among the different ethnic groups in the country. For instance, the use of mediation process through Jaarsaa Biyya or Jaarsaa Araara among the Oromo and the other ethnic groups has been used. However, despite the potential applicability of these institutions as an Alternative criminal Dispute Resolution process in the local community, it has not yet attained any significant position of usage and acceptance in the formal criminal justice system. In other words, despite its wide practice and importance in resolving criminal disputes, Ethiopian formal criminal justice system failed to integrate mediation process as an alternative criminal dispute resolution process. 

This paper is to deal with interrelated issues of integrating mediation process as a criminal dispute resolution program into the formal criminal justice system, and its importance in consolidation of the ideas of restorative justice in the administration of Ethiopian Criminal justice system. The paper also aims to provoke legislatures, policy makers and social workers to work towards promoting, adapting and applying compatible traditional criminal dispute resolution process in a criminal justice context as part of an overall package of Ethiopian Criminal Justice Reform.

 

Download the full text.

  8978 Hits
Tags: