About the Law Blog - Blog - Page 5
“ለእግረኛ ቅድሚያ በመከልከል…” ከሕግ አንጻር ሲታይ
Filipos Aynalem
About the Law Blog
በሀገራችን እጅግ አሳሳቢ እና አነጋጋሪ ከሆኑት የወንጀል ድርጊቶች መካከል በአሽከርካሪዎች የሚፈጸመው ወንጀል ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል ለማለት ይቻላል፡፡ ከትራፊክ ፖሊስ ዕለታዊ ሪፖርት በየዕለቱ እንደምንሰማው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ እንኳን ያለበትን ሁኔታ ብንመለከት በንብረትና በሰው ላይ፣ ቢያንስ በአንደኛው ላይ አደጋ ሳይደርስ የዋለበት ቀን የለም ለማለት ይቻላል፡፡ የአደጋ ዜናው በ24 ሰዓት፣ በወርና በዓመት ስሌት ሲነገር ስንሰማው እጅግ አሳሳቢ ነገር ነው፡፡ በትርፊክ ፖሊስ የዘወትር ሪፖርት እንደምንሰማውም ብዙውን ጊዜ አደጋው የደረሰው ለእግረኛ ቅድሚያ መከልከል በአሽከርካሪ ጥፋት መሆኑን መዘገቡ የተለመደ ነው፡፡
Continue reading
የተሻሻለው የአማራ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ እና አከራካሪው የይርጋ ድንጋጌ
Fekadu Andargie Mekonnen
About the Law Blog
የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 133/98 የተካው የተሻሻለው የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 ቀደም ሲል በሕግ ደረጃ ሽፋን ያላገኙ አዲስ ነገሮችን ይዞ እንደወጣ ይታወቃል፡፡ አዲስ ከሚባሉ ነገሮች አንዱ በገጠር መሬት ላይ በሚነሱ ክርክሮች ላይ የይርጋ መቃወሚያ ተፈፃሚ ሊሆን እንደማይችል ያስቀመጠው ነገር ነው፡፡ ይህ የይርጋ ድንጋጌ በሕጉ የተካተተ አዲስ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ገና ከጅምሩ አከራካሪ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል፡፡ አከራካሪነቱም በባለሙያዎች መካከል ሁለት ጫፍ የያዙ አቋም እንዲኖር ከማድረግ አልፎ አዲስ የክርክር ምክንያትም እየሆነ ነው፡፡ አዋጁ ስራ ላይ ከዋለ ጀምሮም የገጠር መሬትን ተከትሎ የሚቀርቡ ክሶች ላይ የይርጋ መቃወሚያ ተፈፃሚነት የለውም በሚል  ብዙ ዶሴዎች ከተዳፈኑበት አቧራቸውን እያራገፉ በክስ መልክ  እየቀረቡ ነው፡፡ ፍርድ ቤቶችም በባለሙያዎች መካከል በይርጋው ተፈፃሚነት ላይ  ባለ ሁለት ጫፍ የያዘ አቋም ምክንያት ከወዲሁ ተገማችነታቸውና ወጥነታቸው አደጋ ላይ እየወደቀ ነው፡፡ ስለዚህም በጉዳዩ ዙሪያ  የሚነሱ አቋሞችን እና ምክንያቶችን በማየት ሃሳቡን መመልከቱ አስፈላጊ እና ትኩረት የሚያስፈልገው ነው፡፡ የፁሁፉ ዋና ትኩረትም በተሻሻለው የገጠር መሬት አዋጅ ላይ የተቀመጠጠው የይርጋ ድንጋጌ ወሰን አለው ወይስ የለውም የሚል ይሆናል፡፡
Continue reading
ጣዕም መቀየሪያዎች የተጨመሩባቸው የሺሻ ትምባሆ ምርቶች መስፋፋትና ሕገ ወጥነት
Abyssinia Law | Making Law Accessible!
About the Law Blog
በኅብረተሰብ ጤና ዘርፍ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባል ለውጥ ካስመዘገቡ አገሮች ተርታ ትመደባለች፡፡ የጤና አገልግሎትን በቀበሌ ደረጃ ለማስፋፋት፣ በተለይም በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የኅብረተሰብ ክፍል ማዕከል ያደረገና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የተቸረውን የጤና ኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ተግባራዊ በማድረግ፣ የዓለም መንግሥታት ድርጅትን የጤና የሚሊኒየም ግቦችን ለማሳካት ችላለች፡፡ እንደ አብዛኛው ታዳጊ አገሮች ሁሉ ባለፉት ዓመታት የመንግሥት የጤና ፕሮግራሞችና የአጋር ድርጅት ትኩረቶች ውስጥ ወባ፣ ኤችአይቪ/ኤድስና ሳንባ ነቀርሳ የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎች የመከላከልና ቁጥጥር ሥራ፣ እንዲሁም የሕፃናትና እናቶች ጤናን ማሻሻል በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የአገሪቱ የበሽታዎች ሥርጭት ሁኔታ በለውጥ ሒደት ላይ ያለ ሲሆን፣ በተለይም በከተማዎችና በዙሪያቸው ባሉ ሥፍራዎች በመስፋፋት ላይ የሚገኙት የልብ፣ የመተንፈሻ አካላት፣ ስኳርና ካንሰርን የመሳሰሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ይጠቀሳሉ፡፡
Continue reading
በቂ ምክንያት ሳይኖር ዳኛ ከችሎት ይነሳልኝ በሚል የሚቀርብ ማመልከቻ ላይ ስለተቀመጠው ቅጣት
Solomon Tesfaye Dejene
About the Law Blog
ለዚህ ጽሑፍ ምክንያት የሆነኝ ከታች እንደተገለጸው አንድ ተከራካሪ ወገን በፍ/ቤት ክርክር በሚያቀርብበት ወቅት ሊያጋጥሙት ከሚችሉ ጉዳዮች አንዱ ከችሎት ይነሳልኝ (ችሎት ይቀየርልኝ) በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ሲሆን ዳኞች ከችሎት የሚነሱባቸውን ምክንያቶችና ባለጉዳዮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው በአዋጅ ቁጥር 25/88 ከአንቀጽ 27 እስከ 30 ባሉት ድንጋጌዎች የተመለከተ ሲሆን የዚህ ጽሑፍ ዋነኛ አላማ እነዚህን ምክንያቶች ማብራራት ሳይሆን ማመልከቻው ውድቅ ቢደረግ አመልካቹ (ተከራካሪው) ሊቀጣ የሚችለውን አዋጁ በአንቀጽ 30 ላይ ያስቀመጠውን የገንዘብ መቀጫ አግባብነትና ፍትሃዊነት ላይ ሃሳብ ለመስጠት ነው፡፡
Continue reading
የፍርድ አፈፃፀም መሠረታዊ ታሳቢዎችና ያጋጠሙ ችግሮች
Abyssinia Law | Making Law Accessible!
About the Law Blog
አፈፃፀም ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ በእራሱ አማካኝነት ወደ ተግባር የሚለውጥበት ሥርዓት ነው፡፡ ስለፍርድ አፈፃፀም የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመከተል ፍርድን በተግባር መተርጎም እንደመሆኑ መጠን የማስፈፀሚያ ሥርዓቱ በጥቅሉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ ህጉን መሠረታዊ ዓላማ ተከትሎ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲፈፀም በሚያስችል አኳኋን የተዋቀረ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተግባር እንደሚታየው ክስ አቅርቦ ለማስፈረድ ከሚወሰደው ውጭ ጊዜና ጉልበት ባልተናነሰ ሁኔታ የተፈረደን ፍርድ ለማስፈፀም የሚጠይቀው ወጭና ጊዜ በልጦ የሚታይበት ጊዜ ይከሰታል፡፡ ምክንያቶቹ በርካታ ናቸው፡፡
Continue reading
ችሎት መድፈር በኢትዮጵያ ሕግ: ሕጉና አተገባበር
Yonas Alemayehu
About the Law Blog
"ችሎት መድፈር" ወይም Contempt of Court በአብዛኛው ሃገራት የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ግልጋሎት ላይ እየዋሉ ካሉ የሕግ ፅንሰ ሃሳቦች አንዱ ነው። ይህ የሕግ ፅንሰ ሃሳብ በእኛ ሃገር በሰፊው ሥራ ላይ እየዋለ ቢሆንም ከሕጉ መንፈስ ውጭ አተገባበሩ ላይ የሚታየው የሕግ አተረጓጎም ክፍተትና ልዩነት የተለያዩ የዜጎች መብት ጥሰቶችን ሲያስከትል ይታያል። 
Continue reading
ሕዝባዊ ፍርድ፣ ፍርድ ቤቶች እና ገላጋይ ዳኞች
Abyssinia Law | Making Law Accessible!
About the Law Blog
የፍርድ ቤቶችን ችግር ለመፍታት፣ ጫናቸዉን ለመቀነስ፣ የሚያቀርቡትን የዳኝነት አገልግሎት ጥራት ለመጨመር ከሚቀርቡት የመፍትሄ ሃሳቦች መካከል አማራጭ የሙግት መፍቻ ስልቶችን (ለምሳሌ ግልግል ዳኝነት) ማበረታት ነዉ። አማራጭ ስልቶችን ማበረታታት ተገቢ ነዉ፣ ጠቃሚ እስከሆነ ድረስ።  ነገር ግን ፍርድ ቤቶች በችግሮች በተተበተቡበት ሁኔታ፣ ምንም እንኳን ሕጉ ለአማራጭ ስልቶች እውቅና እና ድጋፍ ቢሰጥም፣ የፍድ ቤቶችን ችግር በመፍታት ወይም አለመግባባትን በመቀነስና በመፍታት ረገድ ግን የሚፈይደው ነገር ጥቂት ነው፡፡
Continue reading
የግብይት ወጪ በግብርና
Abyssinia Law | Making Law Accessible!
About the Law Blog
የግብይት እና የምርት ወጪ የሚባሉ ሁለት መሰረታዊ ወጪዎች አሉ። የምርት ወጪ የምትለው፥ አንድን አገልግሎት ወይም ሸቀጥ ወይም ነገር ለማምረት የምታወጣው ነው። ቋሚ እና ተቀያያሪ ወጪ ሊሆን ይችላል። ቋሚ የሚባለው ወጪ መጠን፥ በምርትህ መጠን አይወሰነም እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ። ስለዚህ አንድም አመረትህ ሺተሚሊዮን ቋሚ ወጪዉ ተመሳሳይ ነው። ስለዚህ ብዙ ማምረት ከመጠን እንድትጠቀም ያደርግሃል። ነገር ግን ምን ታመርታለህ? ምንድን ነው ፍላጎትህ? ያመረትከውንስ ለማን እና በምን ያህል ትሸጣልህ? ግብይት ከማን ጋር ትፈጽማለህ? በድርድር ሂደት ያኛው ተዋዋይ ወገን የሚነግርህን መረጃ እንዴት ታረጋግጣለህ? ያኛው ሰውየ ያልነገረህ መረጃ ስለመኖሩ እንዴት ታረጋግጣለህ? እንዴት ትደዳደራለህ? ስምምነት ከገባህ በዃላ ያኛው ሰው ግዴታውን ለመወጣቱ ምን ማረጋገጫ አለህ? ግዴታውንስ በተባለው መጠን እና ጥራት ስለመወጣቱ እንዴት ትከታተላለህ? እነዚህ ሁሉ የግብይት ወጪ ይባላሉ።
Continue reading
በፍትሐብሔር ጉዳይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ብቻ በሚደረግ የክርክር ሥነ-ሥርዓታዊ ሂደት የተከራካሪዎች አለመቅረብ ውጤት፡ ሕጉና ትግበራ
Dagim Assefa
About the Law Blog
“Law is nothing else, but the best reason of wise men applied for ages to the transaction and business of mankind” Abraham Lincoln መነሻ ክስተት ነገሩ እንዲህ ነው! የሙያ ባልደረቦቼ ደንበኞቻቸው ተከሳሽ በሆኑባቸው የፍትሐብሔር የፍርድ ሂደት ላይ መከላከያ መልሳቸውን ሲያቀርቡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(2) (ለ) መሠረት “ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ” መሆኑን እና (ሠ) መሠረት የቀረበው ክስ “በይርጋ የታገደ” መሆኑን ጠቅሰው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን በዋናው ክርክር ላይ ካላቸው መልስ ጋር አያይዘው አቅረበው ነበር፡፡ ነገር ግን ፍ/ቤቶች በቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ክርክር ለመስማት በተያዘ ቀነ ቀጠሮ ከሳሾች ሳይገኙ በመቅረታቸው ምክንያት ጉዳዩን እየመረመሩ የነበሩት ፍ/ቤቶች ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ እንደሚክዱ ከጠየቁ በኃላ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሠረት ክስ ለመስማት በተያዘ ቀነ-ቀጠሮ ከሳሾች ባለመቅረባቸው እና ተከሳሾች ክደው በመከራከራቸው መዝገቡን ዘግተናል በማለት ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
Continue reading
የሰበር ዓላማ ወጥነትን ማስፈን ወይስ ሕገ-ወጥነትን ማስፋፋት?
ገብረእግዚአብሔር ወልደገብርኤል
About the Law Blog
ጊዜው እ.ኤ.አ 1954 ነው፡፡ ለአለም ሀገራት የዲሞክራሲ አርአያና መምህር ነኝ ብላ በምትደሰኩር በአሜሪካ ሀገር ነጭና ጥቁር ተማሪ በአንድ ላይ አይማርም ነበር አሉ፤ ምክንያቱም ጥቁር ተማሪ ከነጭ ተማሪ ጋር በአንድ ላይ እንዲማር መፍቀድ ማለት በነጭ ተማሪዎች ሞራልና ክብር መቀለድ ነው ብላ ታምን ነበር፤ አሜሪካ፡፡ በመሆኑም ጥቁሮችና ነጮች ተለያይተው ይማሩ ነበር ማለት ነው፡፡ በዚሁ አይን ያወጣ አድልዎ የተበሳጨው ብራውን የተባለው ግለሰብ በአሜሪካ ሀገር የካንሳስ ክልል የትምህርት ጉዳይ ቦርድን በፍርድ ቤት ገተረው፡፡ ሚስተር ብራውን ለጥቁሮች ሽንጡን ገትሮ ከተከራከረ በኃላ ጥቁሮችን አንገት የሚያቀና ፍርድ አስፈረደ፡፡ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቁርና ነጭ ተማሪዎች ተለያይተው እንዲማሩ ማድረግ የሰው ልጆች በተፈጥሮ እኩል ሆኖው የመፈጠር መብትን የሚቃረን በተለይም ደግሞ የጥቁሮች ክብርና ሞራል የሚነካ እኩል የትምህርት እድል የሚነፍግ ህገ ወጥ ድርጊት በመሆኑ ከተፈጥሮ ሕግና የአሜሪካ ህገ መንግስት ጋር የሚጣረስ ነው ሲል ለሰው ልጆች እኩልነት የሚያረጋግጥ ፍርድ ሰጠ፡፡ ጥቁሮች ከነጮች ጋር ያለአድልዎና ልዩነት ሳይደረግባቸው እኩል የትምህርት እድል የማግኘትና የመማር መብት አላቸው የሚል መደምደሚያ ላይ ተደረሰ፡፡ በዚሁ ውሳኔ የተበሳጨው "ጆርጅያ ኩሪዬር" የተባለ ጋዜጣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ዳኞችን እንዲህ ሲል ገለፃቸው፡፡
Continue reading