መግቢያ
የማንነት ጥያቄ ምንድን ነው? የድንበር አከላለል ለውጥ (የድንበር ውዝግብ) ጥያቄስ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ሕግስ እንዴት ነው የሚጠብቃቸው? የዚህ ማስታወሻ ዓላማ እነዚህን ጉዳዩች ስለሚመለከቱት የሕግ ክፍሎች በማጥናትና ስለአተረጓጎማቸው አስተያየት በማቅረብ እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ነው፡፡ ከእነዚህ ባሻገር ይህ ማስታወሻ ስለ ትግራይ ሕዝብ መልክዓ ምድራዊ አሰፋፈር ታሪካዊ ዳሰሳ ባጭሩ አድርጓል፡፡
ይህን ማስታወሻ ለመጻፍ ያነሳሱኝ ነገሮች የፌዴሬሽን ምክር ቤት የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ተወካዮች በቀረበለት በአዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀጽ 20 ድንጋጌ መሠረት የማንነት ጥያቄው በክልሉ በደረጃው ባሉ የአሰተዳደር እርከኖች ታይቶ ውሳኔ ማግኘት የሚገባው በመሆኑ ጉዳዩ በትግራይ ክልል እንዲታይ ብሎ በመወስን ማስተላለፉ እና የእኔ ማንነት ናቸው፡፡ በዚህ የተነሳ ዋናው ጥያቄ የሆነውን የማንነት ጥያቄ ምንነትና የድንበር አከላለል ለውጥ (የድንበር ውዝግብ) ጥያቄ ምንነት በመመርመር ስለአተረጎገማቸው አስተያየት ማቅረብ ወደድኩኝ፡፡