ዛሬ በጠዋቱ ዜናው በሙሉ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ሲጓዝ የነበረን 202 ሰዎችን ያሳፈረ የኢትዮጵያ አውሮፕላን 'መጠለፍ' ጉዳይ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ‹ጠላፊው ካርቱም ላይ የተሳፈረ ሰው ይመስላል› ቢሉም በመጨረሻ አውሮፕላኑ ካርቱም ላይ ከነጭራሹ እንዳላረፈና ጠላፊውም ረዳት ፓይለቱ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ ረዳት ፓይለቱ ለምን ይሄን ተግባር እንደፈፀመ ሲጠየቅም ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ስጋት ላይ እንደጣለው በመግለፅ፤ ሲዊዘርላንድ ጥገኝነት እንድትሰጠው ጠይቋል፡፡
ይህ ከሆነ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ መስሪያ ቤት እንደገለፀው ግን ጉዳዩ ጠለፋ (Hijacking) ሳይሁን እገታ ( Hostage Taking) ነው ብሏል፡፡ በሌላ በኩል ረዳት ፓይለቱ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ እንዳይሰጥ ስዊዝን ተማፅኗል፡፡ ሁለት የህግ ጥያቄዎች አሉ፡
1. ጠለፋ ወይስ እገታ?
2. በረዳት ፓይለቱ ላይ የዳኝነት ስልጣን (Legal Jurisdiction) ያለው አካል ማነው? ኢትዮጵያ ወይስ ስዊዘርላንድ?
እነዚህን ጉዳዮች የሚፈቱልን ሁለት አለማቀፍ ሕጎች አሉ (ኢትዮጵያም ስዊዘርላንድም የሁለትም የሕጎቹ ፈራሚ ሀገራት ናቸው)፡፡
1. Convention for the Suppression of Unlawful Seizure of Aircraft – Hijacking Convention on Hijacking – 1970 &,
2. International Convention Against the Taking of Hostages – Convention on Hostage taking - 1983.
በነዚህ ሁለት ሕጎች መሰረትም የረዳት ፓይለቱን ሁኔታ (Situation ) እንይ፡፡
1ኛ. ጠለፋ ወይስ እገታ?
ከላይ በመጀመሪያ የጠቀስነው የHijacking Convention 'ጠለፋ'ን በአንቀፅ አንድ ላይ እንዲህ ይፈታዋል:
Any person who on board an aircraft in flight:
unlawfully, by force or threat thereof, or by any other form of intimidation, seizes, or exercises control of, that aircraft, or attempts to perform any such act, or is an accomplice of a person who performs or attempts to perform any such act commits an offence [of Hijacking].
በሌላ በኩል ከላይ በሁለተኝነት የጠቀስነው የHostage taking convention 'እገታ'ን በአንቀፅ አንድ ላይ እንዲህ ይተረጉመዋል፡
Any person who seizes or detains and threatens to kill, to injure or to continue to detain another person in order to compel a third party, namely, a State, an international intergovernmental organization, a natural or juridical person, or a group of persons, to do or abstain from doing any act as an explicit or implicit condition for the release of the hostage commits the offence of hostage-taking.
የኢትዮጵያዊው ረዳት ፓይለት ተግባርም ጥገኝነት ለማግኝት ያደረገው ማስገደጃ መሳሪያ በመሆኑ የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ መስሪያ ቤት እንዳለው ተግባሩ ለእገታ የቀረበ ሲሆን፤ ተጠያቂነቱም ከእገታ ጋር በተያያዘ ይሆናል ማለት ነው፡፡
2ኛ. ኢትዮጵያ ወይስ ስዊዘርላንድ?
ጉዳዩ 'እገታ' ነው ካልን በጉዳዩ ላይ ተገቢ የሆነው ሕግ አለማቀፉ የፀረ እገታ ሰምምነት (Hostage taking convention) ነው ማለት ነው፡፡ በዚህም መሰረት በረዳት ፓይለቱ ላይ የዳኝነት ስልጣን ያለው የየትኛው ሀገር መንግስት ነው? የሚለው ቀጣዩ ጥያቄ ነው፡፡
ሕጉን ጠቅሰን ብናልፍ ይሻላል፡፡ ዓለማቀፉ የHostage taking convention በአንቀፅ አራት ላይ እንዲህ ይደነግጋል፡
State shall take such measures as may be necessary to establish its jurisdiction over the offence and any other act of violence against passengers or crew committed by the alleged offender in connection with the offence, in the following cases:
A. when the offence is committed on board an aircraft registered in that State (በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ስልጣን ይኖራታል);
B. when the aircraft on board which the offence is committed lands in its territory with the alleged offender still on board (በዚህ መሰረት ደግሞ ስዊዘርላንድ ስልጣን ይኖራታል ማለት ነው).
ስለዚህም በጉዳዩ ላይ የሁለት ሀገሮች የዳኝነት ስልጣን ያለ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ የአውሮፕላኑ ባለቤት በመሆኗ፣ ስዊዘርላንድ ደግሞ አውሮፕላኑ በግዛቷ በማረፉ ስልጣን አላት ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ማን ቀዳሚ ስልጣን ይኖረዋል? የሚለው የሚወሰነው ተጠርጣሪውን (በአሁኑ ጉዳይ ረዳት ፓይለቱ) በቁጥጥር ስር ቀድሞ በማዋል የሚወሰን ሲሆን በአሁኑ ጉዳይ ላይ የዳኝነት ስልጣኑ የስዊዘርላንድ ነው ማለት ነው፡፡
መውጫ፡
ኢትዮጵያ ተጠርጣሪው ተላልፎ እንዲሰጣት (Extradition) በፀረ እገታ ሰምምነቱ አንቀፅ 7ና 8 መሰረት መብት ቢኖራትም ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ የአሳልፎ የመስጠት ስምምነት (Extradition agreement) ስለሌላቸው (እኔ እስከማውቀው ድረስ) ተላልፎ የመሰጠት ጉዳዩ ብዙም አድል የለውም፡፡ የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ መስሪያ ቤትም ከአሁኑ ክስ ለመመስረት ጉዳዩን እያጣራ እንደሆነ መልለጫ ሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም:
ረዳት ፓይለቱ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኝ በስዊዘርላንድ የወንጀል ሕግ SR 311.0 አንቀፅ 185 መሰረት ከ3 ዓመት እስከ 20 ዓመት (እንደ ነገሩ ሁኔታ) የሚደርስ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ በሌላ በኩል 'ድንገት' ተላልፎ ለኢትዮጵያ ቢሰጥ ደግሞ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 507/1 መሰረት ከ15 አስከ 20 ዓመታት እስር ይጠብቀዋል ማለት ነው፡፡
እንግዲህ ምን ይደረጋል፤ ፈጣሪ ከእሱ ጋር ይሁን? :)
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ምክትል ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ስራ አስፈፃሚ የነበሩት “ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ የአሸባሪ ቡድን የሆነው ኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል ክስ ተመስርቶባቸው የ8 ዓመት እሥር የተበየነባቸው ሲሆን፤ ይግባኝ ጠይቀው እስሩ ወደ 5 ዓመት ዝቅ ተደርጎላቸዋል፡፡
ከ5 ዓመቱ የእስር ጊዜ ውስጥም 3ቱን ዓመት በመጨረሳቸው በአመክሮ ይፈቱ ዘንድ ለማረሚያ ቤቱ ያመለከቱ ሲሆን ማረሚያ ቤቱም ‹አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው› በማለት እስከአሁን ሊፈታቸው አልቻለም፡፡ ይህም ብዙ ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡
አንዳንድ ህጋዊ ሁኔታዎች ስለጉዳዩ፡
አመክሮ ምንደር ነው?
ሌላውን ትርጉም ትተን የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ‹በተወሰነ ጊዜ በአመክሮ መፈታት› በሚለው ክፍል በተለይም በአንቀፅ 202 እንደደነገገው፡
"ተቀጭው ከተወሰነበት የእስራት ጊዜ ከሶስት እጅ ሁለቱን እጅ ወይም ፍርዱ የእድሜ ልክ እስራት ሲሆን ሀያ ዓመት በፈፀመ ጊዜ አግባብ ባለው አካል ወይም በጥፋተኛው አሳሳቢነት ጥፋተኛውን ከቅጣቱ ነፃ ያወጣዋል፡፡"
ይህም ማለት አመክሮ 2/3ኛውን የቅጣት ጊዜውን የጨረሰ ታራሚ ከእስር የሚፈታበት አሰራር ነው፡፡
አመክሮ ለማግኝት ምን መስፈርት ማሟላት ያስፈልጋል?
የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ከላይ በጠቀስነው አንቀፅ 202 ላይ አመክሮ ለማግኝት አንድ እስረኛ ማሟላት የሚያስፈልገውን መስፈርቶች ይዘረዝራል፡፡ ይህም፡
- ‹ታራሚው በስራ ጠባዩ የተረጋገጠ መሻሻል አሳይቶ እንደሆነ…›
- ‹ካሳ የመክፈል ግዴታ ተጥሎበት ከነበረና ካሳውን መክፈሉ የተረጋገጠ እንደሆነ…›
- ‹አመሉና ጠባዩ መልካም አኗኗር ለመኖር የሚያስችለውና በአመክሮ መፈታቱ መልካም ውጤት ሊያስገኝ ይችላል ተብሎ የታመነ እንደሆነ..›
ነው ብሎ ይደነግጋል፡፡
ማረሚያ ቤት ወይስ ፍርድ ቤት?
ታራሚን በአመክሮ የመልቀቅ የመጨረሻው ስልጣን የፍርድ ቤት፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን ማረሚያ ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት ወይም በታራሚው አሳሳቢነት ለፍርድ ቤት ሲያቀርብ ነው ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሚሰጠው፡፡ እዚህ ላይ ማረሚያ ቤቱ ትልቁን ስልጣን ይዞ እናገኛለን፡፡ ማረሚያ ቤቱ ለፍርድ ቤት ማቅረብ ካልፈለገ ሊተወው የሚችልበት አግባብ አለ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ማረሚያ ቤቱ በሕግ ስር ያለ አካል እንደመሆኑ መጠን በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 202 ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን ላሟላ ታራሚ አመክሮ ሊከለክል አይችልም - የታራሚው መብት ነውና!
በቀለ ገርባስ?
አቶ በቀለ ገርባ ከተፈረደባቸው የአምስት ዓመት እስር ውስጥ 2/3ኛውን ወይም 3 ዓመት የሚሆነውን ጨርሰው የአመክሮ ጥያቄያቸው በማረሚያ ቤቱ በኩል ለፍርድ ቤት እንዲቀርብላቸው ቢጠይቁም ማረሚያ ቤቱ ‹አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው› የሚል መልስ እንደሰጣቸው ተሰምቷል፡፡
1ኛ. አመክሮ መስጠት የማረሚያ ቤት መብት ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው፡፡ መስፈርቱን ያሟላ ታራሚ አመክሮ የማግኝት መብት ያለው መሆኑ በሌላ በኩል አመክሮ ሰጭውን አካል ላይ ግዴታ ይጥላልና፡፡
2ኛ ሌላው አቶ በቀለ ገርባ መስፈርቱን አሟልተዋል ወይስ አላሟሉም የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ 2/3ኛውን የእስር ጊዜ መጨረስ የሚለውን Objective መስፈርት እንዳሟሉ ግልፅ ሲሆን፡፡ ችግሩ የተፈጠረው Subjective መስፈርቱ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ይህም ማለት በእስር ወቅት መልካም ፀባይ አሳይተዋል ወይስ አላሳዩም የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ አንድ ታራሚ በእስር ወቅት ለመልካም ፀባይ ተቃራኒ የሆኑ ነገሮችን ካሳየ የቅጣት ማስጠንቀቂያ ከመፃፍ እስከ ብቻውን ማሰር (Solitary Confinement) ድረስ ያሉ እርምጃዎች በማረሚያ ቤቱ ሊወሰዱበት ይችላሉ፡፡
አቶ በቀለ ገርባ ከፀባያቸው ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ቅጣት ያልተወሰደባቸው ከመሆኑም ሌላ መልካም ፀባይ እንዳሳዩ ከማረሚያ ቤቱ እንደተነገራቸው ራሳቸው ገልፀዋል፡፡ በቀለ ገርባ ምም መስፈር አሟልተዋል ማለት ነው፡፡ ታዲያ ምን ይሆን አቶ በቀለን በአመክሮ ከመፈታት ያገዳቸው?
አንዳንድ ነገሮች...
ባለው አካሄድ አብዛኛው ታራሚዎች በአመክሮ ይፈታል፡፡ ከሌባ እስከ ሙሰኛ፡፡ High Profile በሆኑ ክሶች የተከሰሱ ሰዎች ሳይቀሩ በአመክሮ ሲፈቱ እንደነበር እናስታውሳለን ለምሳሌ ቴዲ አፍሮ 24 ወራት ተፈርዶበት 16 ወራትን ጨርሶ በአመክሮ ተፈቷል፡፡ አቶ አሰፋ አብርሃ 9 ዓመት ተፈርዶባቸው ሰባት ዓመታት ታስረው ከብዙ ውዝግብ በኋላ በአመክሮ ተፈተዋል፡፡ በሌላ በኩል በቅንጅት ክስ ስር ተከሰው የነበሩት አቶ ዳንኤል በቀለና አቶ ነፃነት ደምሴ 30 ወራት የተፈረደባቸው ሲሆን 20 ወራትን በእስር አሳልፈው አመክሮ ቢጠይቁም ማረሚያ ቤቱ ‹ፍርዳችሁን ጨርሳችሁ ውጡ› በሚል ምክንያት አመክሮ ከልክሏቸው ነበር፡፡
እንግዲህ አቶ በቀለ ገርባ በሕጉ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው እያለ በአመክሮ የመፈታት መብታቸው አልተከበረም ወይም ማረሚያ ቤቱ ግዴታውን ሊወጣ አልፈለገም!
የሰው ልጅ ሐሳቡን ለሌላው መግለጽ መጀመሩ ሰዎች የጋራ ባሕርያትን ይዘው ወደ አዲስ ስልጣኔ፤ ወደ አዲስ ሕይወት እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ ነገር ግን የዚህ ትስስር ድንበር የለሽ መሆን ጉዳት አለው በማለት፤ በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩ ምክንያቶች መረጃን የመለዋወጡ ሂደት ገደብ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ ገደብ እንዲደረግ የሚያስገድዱት ዋነኛ ምክንያቶች ሦስቱን ዋነኛ ተቋማት መጠበቅ በሚል ሐሳብ ስር ይጠቃለል፡፡
እነዚህም ተቋማት ቤተሰብ፣ ቤተ እምነት እና ቤተ መንግሥት ናቸው፡፡ ቤተሰብን መጠበቅ ስንል ቤተሰብ የኅብረተሰብ መሠረት በመሆኑ ቤተሰብን እና ስርዓቱን የሚጎዱ ነገሮች (Obscene) በአደባባይ እንዳይኖሩ ማድረግ ማለታችን ነው፡፡ ቤተ እምነትን የሚያጎድፉ ነገሮችም (Blasphemous) እንዲሁ:: እንዲሁም በሦስተኝነት በሕግ የተዘረጋውን ስርዓት ለመጠበቅ ሲባል ሲሆን ይሄም የግደባ ሂደት ሳንሱር (Censorship) ይባላል፡፡
የሕግ ማዕቀፉ እና ልምዱ ምን ይላል?