ጸሐፊው በደቡብ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለአሥራ አራት ዓመት በዓቃቤሕግነት ያገለገለ ሲሆን በሕግና ፖሊስ ሳይንስ ትምህት ዘርፍ ጥናትና ምርምር አድርጓል። ጸሐፊው የሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ክልል ምሥረታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የሕግ አማካሪና የሕግ አርቃቂ ሆነው ሠርተዋል። ጸሐፊውን በኢሜል አድራሻቸው hihoney3@gmail.com ማግኘት ይችላሉ።

ጠበቃ በጋብቻ ፍቺ ሂደት ስለሚኖረው የሙያ ወሰን እና የሰበር ተቃርኖ

ጋብቻ በሁሉም ባህሎችና ሃይማኖቶች ትልቅ ክብር እና ልዩ ቦታ የሚሰጠው የሃገር ምሶሶ የሆነ የቤተሰብ ተቋም የሚፈጥ ሕጋዊ ኩነት ነው፡፡ በመሆኑም ፀንቶ እንዲቆይ በመንግስት እና በህብረተሰቡ ጥበቃ ይደረግለታል፡፡ መንግስት ጋብቻ ሲመሰረት፣ በጋብቻ ውስጥ እና ሲፈርስ ግንኙነቱ የሚመራበትን ሥነ ስርዓት በህግ በመደንገግ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ ጋብቻ በፍች እንዲፈርስ ጥያቄ በሚቀርብበት ወቅት ፍርድ ቤት ጋብቻው ፀንቶ እንዲቆይ ለማስቻል ሊከተላቸው እና ሊፈፀማቸው የሚገቡ የጥበቃ ሥነ-ሥርዓት በቤተሰብ ህግ ተደንግጓል፡፡ (አንቀፅ 76 - 82 ይመለከቷል)። 

  2861 Hits

በሠራተኛ ቅጥር ሂደት ስለሚፈፀም የኋላ ታሪክ ፍተሻ፣ አስፈላጊነት እና ሕጋዊነት

መግቢያ

በዚህ የውድድር ዘመን አሰሪዎች ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ወይም ምርት በጥራት እና በፍጥነት ለደንበኞቻቸው ማቅረብ ይገባቸዋል። ከዚህም ባለፈ አንዳንድ ሙያዎች በባህሪያቸው በአደራና እምነት ላይ የተመሰረቱ (positions of trust) ስለሆነ ሰራተኛው ለዚህ የሥራ መደብ የተገባ መሆን ይገባዋል።  በመሆኑም አሰሪዎች መልካም ስማቸውን ጠብቀው የገበያ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ በቴክኖሎጂ እና በሰለጠነ የሰው ሃይል ተቋማቸውን ያጠናክራሉ። ሆኖም ግን የሰው ሃይል ቅጥር በሚፈፅሙበት ወቅት ከግለሰብ የግል ባህሪ እና በዲጅታል ቴክኖሎች መሳሪያዎች ሀሰተኛ ሰነድ ለማዘጋጀት ከመቼው ጊዜ በላይ ለመለየት በሚያስቸግር መልኩ ረቂቅ፣ በቀላሉ የሚገኝና ተግባር ላይ የሚውል በመሆኑ የቅጥር መስፈርቱን የማያሟላ እና ለስራው ትክክለኛና ተገቢ ያልሆነው ስራተኛ እንዲቀጥሩ በማድረግ ከገበያ ተወዳዳሪነት የሚያስወጣ የስጋት ተጋላጭነታቸውን አሳድጎታል።

  3391 Hits