Font size: +
2 minutes reading time (403 words)

ለተዋጣለት ወንጀል ምርመራ የሚጠቅሙ ቀዳሚ ነገሮች

የተዋጣለት የወንጀል ምርመራ ሥራ ለወንጀል ፍትሕ ሥርዓት መስፈን ቁልፍ የሆነ ሚና እንደሚጫወት በርካታ በወንጀል ምርመራ ሥራ ላይ የታተኮሩ መጽሐፍት የሚገልጹት ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በወንጀል ምርመራ ወቀት የተፈጸመ ወንጀልን ለማግኘት እና ጥፋተኛውን ለይቶ ለማውጣት ከሚጠቅሙ ቀዳሚ ነገሮች መካከል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

1. የወንጀል ሕጉን ይዘት በጥልቀት መረዳት

የማንኛውም የወንጀል ምርመራ የመጀመሪያ አቅጣጫ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት በትክክል በወንጀል ሕግ ወይም በሌሎች ሕጎች ላይ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑንና አለመሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ የወንጀል ሕጉን ይዘቶች ጠንቅቆ አለመረዳት መርማሪዎች፡-

  • ትክክል ባልሆነ መነሻ የወንጀል ክስ እንዲያቀርቡ፤ ወይም
  • ትክክል በሆነ መነሻ የወንጀል ክስ እንዳያቀርቡ፤ ወይም
  • በተፈጸመው ድርጊት ውስጥ ወንጀል የሚያሰኝ ነገር ሳይኖር ወይም በፍትሐብሔር ለሚታይ ጉዳይ፤ ወዘተ የወንጀል ክስን እንዲያቀርቡ ያደርጋቸዋል የሚሉት በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡

 

2. የወንጀል ምርመራን በተመለከተ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ ላይ ለሰፈሩት ድንጋጌዎች ትኩረት መስጠት

ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ሊጠቀስ የሚገባውና ማንኛውም የወንጀል ምርማሪ ሊዘነጋው የማይገባው ነገር ቢኖር በእያንዳንዱ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌ ውስጥ ጥልቀት ያለው የሕግ ሃሳብ መኖሩን እነሱም የእያንዳንዱን ዜጋ መሠረታዊ ወይም ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን ለማስከበር የተደነገጉ መሆናቸውን ነው፡፡ በመሆኑም መርማሪዎች የመርህ ሰዎች እንዲሆኑ ይጠበቃል፡፡ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የሚቀርቡ መረጃዎች በፍርድ ቤቶች ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖቸው ሊያስደርጉ ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ የግድ ይላል፡፡

 

3. የማስረጃ ድንጋጌዎችን ይዘት መረዳት

እያንዳንዱን ማስረጃን በሚመለከት በሕጉ ላይ የተደነገገው ድንጋጌ በይዘት ደረጃ ሲታይ የረጅም ጊዜ ምርመራ፣ ጥናት እንዲሁም የክሪሚናሊስቲከስ ሳይንስ ውጤት መሆናቸው የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ ለማንኛውም ዓይነትና በማናቸውም ደረጃ ለሚገኙ የወንጀል ምርመራ ተግባራት ስኬታማ መሆን እነዚህ የማስረጃ ድንጋጌዎች ውስጥ የተካተቱ ስልታዊ የተግባር እንቅስቃሴዎና አፈጻጸሞችን መርማሪዎች በሚገባ ሊረዷቸውና ጠንቅቀው ሊያከብሯቸው ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን የማስረጃ ድንጋጌዎች ማክበር የሚገባው በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ ውስጥም ቦታ በማግኘታቸው ብቻ ሳይሆን በእነሱ ውስጥ የተካተቱት ስልታዊ የተግባር እንቅስቃሴዎች ለማናቸውም የወንጀል ምርመራ ሥራዎች የተሟላና ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት ወይም ለማስገኘት የሚያስችሉ ነገሮች በመሆናቸውም ጭምር ነው፡፡

 

4. የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕጉን መንፈስ መከተል

እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት አንድ ሕግ መከበር አለበት ሲባል ሕጉ የሚለውን በቃል ወይም በደረቁ መከተልን ብቻ ሳይሆን የሕጉን መንፈስ ጨምሮ ነው፡፡ ይህኛው አስተሳሰብ በአብዛኛው የሚያርፈው በመርማሪው ሥነ ምግባር ላይ ነው፡፡ በርግጥ በምርመራ ስልት ውስጥ የሚካተቱ በርካታ ጉዳዮችን በሕጉ ውስጥ ማስፈር አስቸጋሪ ቢሆንም የተወሰኑና መርማሪው በምርመራ ሂደት እንዳይፈጽማቸው የሚፈለጉ ነገሮች ተደንግገዋል፡፡ ለምሳሌ፡- መርማሪው መሪ ጥያቄዎችን ያለማቅረብ፣ የተመርማሪዎችን ሰብዓዊ ክብር ያለመንካት፣ በምርመራ ሂደት ግልጽ የሆኑለትን በጣም ግላዊ ጉዳዮችን ይፋ ያለማድረግ፣ ወዘተ ናቸው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም መርማሪ የምርመራ ሂደቱ ሚዛናዊነትና ግብረ ገብነት የተላበሰ እንዲሆን፣ የሥነ ሥርዓት ሕጉን መንፈስ የተከተለና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ያልጣሰ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡

 

5. ክሪሚናሊስቲክስን በጥልቀት መገንዘብ

በመርማሪዎች ዘንድ ግንዛቤ ሊወሰድበት የሚገባ ሌላው አብይ ጉዳይ ለወንጀል ድርጊቱ መፈጸም መርጃ የሚሆኑ ነገሮች መሠረታዊ ክስተት፣ ሕልውና ለውጥና የመጥፋት መንስኤዎችን መረዳት አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡ ከዘመኑ የቴክኖሎጂ እድገት ጋር የወንጀል ድርጊቶች አፈፃፀም እየረቀቁ ስለሚመጡ መርማሪውም ራሱን ለነዚህ ለውጦች አዘጋጅቶ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡

 

×
Stay Informed

When you subscribe to the blog, we will send you an e-mail when there are new updates on the site so you wouldn't miss them.

የጋብቻ እና ፍቺ ሕጋዊ ውጤቶች ከተሸሻለው የቤተሰብ ሕግ አንፃር
ተከሳሽ ምስክር መሆን ይችላል?

Related Posts

 

Comments

No comments made yet. Be the first to submit a comment
Already Registered? Login Here
Abebe
Friday, 20 September 2024