Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በ1996 ዓ.ም የኦሮሚያ ክልል የጠበቆች ፈቃድና ዲሲፕሊን ጉዳይ ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 86/1996 በ2005 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 182/2005 አሻሽሎ ማውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡ ተሻሽሎ በወጣው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የጠበቆችና የህግ ጉዳይ ፀሐፊዎች ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 10 ሥር የሁለተኛ ወይም የአንደኛ ደረጃ የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት አመልካቾች 1.…
‹‹ዶ/ር ኢንጂነር ነኝ›› በሚል ሐሰተኛ ማዕረግ በማጭበርበር ወንጀል ተርጥረው፣ ከተመሠረቱባቸው ሦስት ክሶች አንዱን ክደው በሁለቱ ጥፋተኛ የተባሉት አቶ ሳሙኤል ዘሚካኤል አዲስ ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ ሰሞኑን በዮድ አቢሲኒያ ባለቤት አቶ ትዕዛዙ ኮሬ አዲስ ክስ የተመሠረተባቸው አቶ ሳሙኤል፣ ‹‹30,000 ብር ተበድረው ክደውኛል›› ተብለው ነው፡፡ በወቅቱ ‹‹ዶ/ር ኢንጂነር›› ተብለው ይጠሩ የነበሩት አቶ ሳሙኤል፣ ወደ…
-ሕዝብ የሚበዛባቸው ኤድና ሞልና ፍሬንድሺፕ ዒላማ ነበሩ ተብሏል ዜግነታቸው ሶማሊያዊ የሆኑና በተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው አልሸባብ አባል ናቸው የተባሉ አምስት ተጠርጣሪ ሶማሊያውያን፣ በአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ በሚበዛባቸው የመዝናኛ ሥፍራዎች የአጥፍቶ መጥፋት ወንጀል ለመፈጸም በመዘጋጀት ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ የአጥፍቶ መጥፋት ወንጀል በመፈጸም በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ አሳድረው፣…
በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት ጦማሪያንና ጋዜጠኞች፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ19ኛ ወንጀል ችሎት ሰብሳቢ (የመሀል) ዳኛ አቶ ሸለመ በቀለ እንዲነሱላቸው አቤቱታ አስገቡ፡፡  ችሎቱ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ተሰይሞ የነበረው የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ቢሆንም፣ ተከሳሾቹ በጠበቃቸው አቶ አመሐ መኮንን አማካይነት ባስገቡት አቤቱታ፣ ‹‹ዳኛው ላለፉት ስድስት ወራት በነበረው ክርክር የተፋጠነ ፍትሕ…
የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ለማስገንባት ላቀደው ብሔራዊ ስታዲየም የዲዛይን ጨረታ በ2006 ዓ.ም. የተጀመረው የሕግ ክርክር ሰበር ሰሚ ችሎት ደረሰ፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ ተከሳሽ የሆነውን የስፖርት ኮሚሽንን ምላሽ ጠይቋል፡፡ ክርክሩ የተነሳው በጄዳው አማካሪ አርክቴክቶችና መሐንዲሶችና በፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን መካከል በፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ጄዳው አማካሪ አክርቴክቶችና መሐንዲሶች…
-ከሁለት ዓመታት በላይ ታስረዋል ጀመአተ ሙስሊም ጀሀድ አሸባሪ ቡድን በሚባል በህቡዕ ተደራጅቶ በሚንቀሳቀስ አሸባሪ ድርጅት ውስጥ፣ አባል ሆነው ‹‹በሸሪዓ የሚተዳደር እስላማዊ መንግሥት እንመሠርታለን›› የሚል ዓላማ ይዘው ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸው ተገልጾ በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩ ሁለት እንግሊዛውያንና አንድ የሶማሊያ ዜጎች፣ በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ተወሰነባቸው፡፡  የፌዴራል…
በአሁኑ ጊዜ የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው ቀድሞ የጋምቤላ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦኮሎ አኳይ ላይ ተሰምተው የነበሩ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል ሳይቀረፅ በመቅረቱ፣ ከሳሽ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በድጋሚ እንዲያሰማ ታዘዘ፡፡  ጉዳዩን እየመረመረው የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የክስ መዝገቡን ለጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጥሮ የነበረው፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ…
የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአሁኑ ወቅት ካለው ሙስናን የመከላከል አቅም በእጅጉ የገዘፈ ኃላፊነት የሚሰጡትን ሦስት ረቂቅ አዋጆች ፓርላማው ጥር 5 ቀን 2007 ዓ.ም. አፀደቀ፡፡ የፀደቁት አዋጆች የሙስና ወንጀልን ለመደንገግ፣ የፀረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅን ለማሻሻል፣ እንዲሁም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ሲሆኑ፣…
-ማረሚያ ቤት ‹‹ተዘረፍን›› ላሉ ተጠርጣሪዎች ምላሽ እንዲሰጥ በድጋሚ ታዘዘ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙትና የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለመሠረተባቸው ክስ ቅደመ መቃወሚያ ባቀረቡት አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ አብረሃ ደስታን ጨምሮ አሥር ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ውድቅ እንዲደረግለት ታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ቤትን ጠየቀ፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ…
-79 ሰዎች መሞታቸውና 13,034 ነዋሪዎች መፈናቀላቸው በክሱ ተጠቅሷል ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ወደ ጋምቤላ ክልል በመሄድ በማዣንግ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በሕጋዊ መንገድ ሠፍረው ለበርካታ ዓመታት ሲኖሩ የነበሩ የሌላ ብሔር ተወላጆችን በአካባቢው አጠራር ‹‹ደገኞች›› የሚሏቸውን በመግደል፣ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት በማድረስና በማፈናቀል የተጠረጠሩ፣ የጋምቤላ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ አዛዥን ጨምሮ 17 ባለሥልጣናትና…
ሃና ላላንጐ የተባለችውን የ16 ዓመት ታዳጊ ተማሪ አስገድደው በቡድን በመፈራረቅ ደፍረው ለሞት ዳርገዋታል ተብለው ታኅሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ የተመሠረተባቸው የአምስት ተጠርጣሪዎች፣ ክሱ በዝግ እንዲታይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ታኅሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ወሰነ፡፡ የሟች ሃና እህቶች፣ ቤተሰቦችና ሌሎች ታዳሚዎች ታኅሳስ 24 ቀን…
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የወንጀል ችሎት የ16 ዓመቷ ሃና ላላንጎን አስገድደው ደፍረው ለህልፈተ ዳርገዋታል በሚል በተጠረጠሩ አምስት ተከሳሾች ላይ የአቃቤ ህግን ምስክር ለመስማት ቀጠሮ ያዘ። ፍርድ ቤቱ ክስ አሰምቶ መቃወሚያ ካለ ለመቀበል ነበር ቀጠሮ ይዞ የነበረው። የሟች ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድና ሌሎች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቀደም ብለው ነው ወደ ፍርድ…
የአርቲስት አስቴር ከበደ፣ ነዋይ ደበበ፣ ሙሉ ገበየሁ እና ደበሽ ተመስገን ስራዎችን አስመስሎ በማዘጋጀት ለገበያ ያቀረበው ቃቂ ተስፋዬ በሶስት አመት ከሰባት ወር እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት። የ24 አመቱ ቃቂ ተስፋዬ አቃቤ ህግ በአዋጅ ቁጥር 410/1996 የወጣውን የቅጅና ተዛማጅ መብቶችን ጥሷል በማለት ነው የከሰሰው። ወንጀሉን የፈፀመው ደግሞ ከ2004 አ.ም ጀምሮ ነው። በአርቲስት አስቴር…
መንግስትን 1 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ አጭበርብረዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው የውጭ ዜጎችና አንድ ኢትዮጵያዊ ዛሬ የተመሰረተባቸውን ክስ ተከትሎ ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ አቃቤህግ ምላሽ እንዲሰጥ ታዘዘ። ክስ የተመሰረተባቸው 17 የውጭ ሃገር ዜጎች እና ድርጅቶች እንዲሁም አንድ ኢትዮዽያዊ በህገ ወጥ ንግድ እና ከታክስ ስወራ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ነው የተከሰሱት። አስረስ አወል አብዱ…