Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

‹‹የጦር መሣሪያ በእጃቸው ስላገኘን ተጨማሪ አላቸው ብለን እንጠረጥራለን›› መርማሪ ፖሊስ ‹‹ተጨማሪ ጊዜ የተጠየቀበት ጉዳይ አሳማኝ አይደለም›› የተጠርጣሪዎች ጠበቃ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ላለፉት 28 ቀናት በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) በእስር ላይ የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሦስት አባላት፣ መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ…
In an important step towards resolving a long-running dispute over the Grand Renaissance Dam, the leaders of Egypt, Ethiopia and Sudan have signed in Khartoum a declaration of principles as follows: Introduction Valuing the increasing need of the Arab Republic of Egypt, the Federal Democratic Republic of Ethiopia and the…
የጫት ንግድና አጠቃቀምን ስርአት ለማስያዝ የሚያስችል ረቂቅ ህግ እየተጠናቀቀ መሆኑን የምግብ፣መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ። በህገ-ወጥ የምግብ፣መድሃኒትና ጤና አገልግሎት ቁጥጥር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰሞኑን በሎግያ ከተማ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ እንደተናገሩት፥ ወጣቱ ትውልድ ስትራቴጂካዊ ሀይል በመሆኑ ከጫት፣ሲጋራና አልኮል ሱስ ነፃ…
ከ5 ወራት በፊት በሃዋሳ ከተማ የአንድ ጠበቃን ህይወት ያጠፋው አና ረዳቱን ያቆሰለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ የሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ። አቶ ታምራት ሙሉ የተባለው ግለሰብ መስከረም 28 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ጠበቃው ቢሮ በማምራት ነበር ወንጀሉን የፈጸመው። ተከሳሹ ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ ለጊዜው የተሰወረ ቢሆንም፥ ከ11 ቀናት ክትትል በኋላ…
ከፖሊስ ባልደረባ ኮንስታብል ሞባይል የወሰደው ግለሰብ በአንድ ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ 1ኛ የወንጀል ችሎት ነው ቅጣቱን ያስተላለፈው። ተከሳሹ ኢዮሲያስ ገበረሚካዔል አራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 05/06 ነዋሪ ሲሆን፥ በገል ስራ አንደሚተዳደር በክስ መዝገቡ ተጠቅሷል። ተከሳሹ በተደጋጋሚ በተለያዩ ቀናቶች በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 05 በሚገኘው…
በአሰቃቂ ሁኔታ ወላጅ እናቱና ሁለት የቤተሰብ አባሎቹን የገደለውና በአባቱ ላይ ከባድ የመግደል ሙከራ የፈጸመው ግለሰብ ዛሬ የሞት ቅጣት ተላለፈበት፡፡ ተከሳሹ ዳንኤል ከበደ ይባላል፤ የ30 አመት ወጣት ሲሆን የታክሲ ተራ አስከባሪ ነበር፡፡ እንደ ፌዴራል አቃቤ ህግ ወንጅሉን የፈጸመው ሰኔ 17 2002 አመተ ምህረት ሌሊት ላይ ነው፡፡ ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ አዲስ አበባ…
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 20ኛው ወንጀል ችሎት ረዳት አውሮፕላን አብራሪው ሃይለመድን አበራ ከተመሰረቱበት ሁለት ክሶች በአንዱ ጥፋተኛ ሲለው ሁለተኛውን ውድቅ አደረገ። ተከሳሹ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከግንቦት 2000 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በረዳት አውሮፕላን አብራሪነት ተቀጥሮ ይሰራ እንደነበር የክሱ መዝገቡ ያስረዳል። ለካቲት 10 / 2006 አጥቢያ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ከ30 ሲሆን የበረራ…
የማማለያ ቃላትን በመጠቀም ልጅሽን ወደ ውጭ እልካታለው በማለት ከ12 ሺህ ብር ተቀብሎ ልጅቷን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ቤሩት በመላክ ህይወቷ እንዲጠፋ ያደረገው ግለሰብ በ8 ዓመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ ተወሰነ። ተከሳሽ ቢኒያም ወርቁ ይሰኛል። ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ወደ ውጪ አገራተ የመላክ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው ዜጎችን ወደውጪ አገራት በመላክ ወንጀል ነው አቃቤህግ…
በኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን በመመልመል መንግሥትንና ተቋማቱን እንዲሰልሉ፣ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን) ወይም ዴሞክራሲያዊ ምንቅስቃስ ሕዝቢ ትግራይ (ዴምሕት) ብሎ በሚጠራው ቡድን የተመለመሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡ የወንጀል ድርጊት በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የአይዲዎሎጂ ዓላማን ለማራመድ፣ ሕዝብን ለማስፈራራትና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብለው…
-በድጋሚ ፍርድ ቤት ደፍራችኋል በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶ ለቅጣት ተቀጠሩ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ ጠምቶታልና እግዚአብሔር ፍትሕ ይስጠው››አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበሩ ‹‹ተራ ስድብ ተሳድባችኋልና ማዕከላዊ እንድትመረመሩ እናዛለን›› ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በሙግት ላይ የሚገኙት የአንድነት፣ የዓረናና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ አቶ አብርሃ ደስታና…
መጋቢት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ረቂቅ አዋጅ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ቢኖረውም፣ ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚቃረኑ አንቀጾችን የያዘ በመሆኑ እንዲስተካከል የፓርላማ አባላት ጠየቁ፡፡ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ አገሪቱ የቀረፀቻቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መሠረት በማድረግ ከ40 እስከ 50 ዓመታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ በኢንዱስትሪ የዳበረችና ዜጎቿም ከፍተኛ…
ተቀማጭነቱ በሆንግ ኮንግ የሆነው ፔትሮትራንስ የተሰኘው የቻይና የነዳጅ ኩባንያና የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በካሉብ ጋዝ ፕሮጀክት ጉዳይ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ በሚገኘው ዓለም አቀፍ ንግድ ምክር ቤት የግልግል ፍርድ ቤት ክርክር ሊጀምሩ ነው፡፡ በኦጋዴን ክልል የሚገኙትን የካሉብና የሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቶች እንዲያለማ የማዕድን ሚኒስቴር ለፔትሮትራንስ የሰጠውን የፔትሮሊየም ልማት ፈቃድ፣ ሚኒስቴሩ አላግባብ ሰርዞብኛል ያለው ፔትሮትራንስ…
‹‹በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 21 በተደነገገው መሠረት እየተስተናገዱ ነው›› የሴት ታራሚዎች ጥበቃና ደኅንነት ዘርፍ አስተዳዳሪ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙት ጦማሪያንና ጋዜጠኞች መካከል ጣማሪና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪ ማኅሌት ፋንታሁን፣ በእስር ላይ በሚገኙበት ማረሚያ ቤት የአያያዝ ችግር እንዳለባቸው በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤት ላቀረቡት አቤቱታ፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የካቲት 25 ቀን 2007…
-ተዘረፍን በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደረገ በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸውና በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት፣ የሰማያዊና የዓረና አመራሮች ችሎት በማወክ፣ በማንጓጠጥ፣ የችሎቱን ስም በማጥፋትና የችሎት ሒደትን በማስተጓጎል የቅጣት ውሳኔ ሊሰጥባቸው ነው፡፡ የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የዓረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋ ላይ የቅጣት…