Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

-ዓቃቤ ሕግ አቤቱታውን ተቃውሞ ምላሽ ሰጥቷል -ፍርድ ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት በክርክር ላይ የሚገኙትና በክስ መዝገብ 141352 ላይ ከተካተቱት ውስጥ፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ሌሎች ተከሳሾች፣ የቀረበባቸው ክስ ተሰርዞ በነፃ እንዲሰናበቱ ለፍርድ ቤት አቤቱታ…
የአዲስ አበባ ከተማ ነጋዴዎች የብቃት መመዘኛ መመርያና የሊዝ አዋጁ እንዲሻሻል ጠየቁ፡፡ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ባህል አዳራሽ በተካሄደው ውይይት፣ ሁለቱ ሕጎች ለንግድና ኢንቨስትመንት ሥራዎች ማነቆ እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ይህንን ስብሰባ የመሩት የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማና የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ፣ ሁለቱ ሕጎች ያሉባቸው ችግሮች ታይቶ…
ራሱን የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ (ጋሕነን) እያለ በሚጠራው ቡድን ውስጥ አመራር፣ ታጣቂና አባል በመሆን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉና በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ የተመሠረተባቸው 11 ግለሰቦች፣ በ12 እና በ13 ዓመታት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተፈረደባቸው፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ.ም.…
በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደርና ኅብረተሰቡን ለማስፈራራት፣ እንዲሁም ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በትጥቅ ትግልና በኃይል ለማፈራረስ የሽብር ቡድን ከሆነው የአርበኞች ግንባር ጋር በመቀላቀል ሲያሴሩ በቁጥጥር ሥር ውለዋል በተባሉ ስድስት ተጠርጣሪ ወጣቶች ላይ፣ የሽብርተኝነት ክስ መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመሠረተ፡፡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ…
-የፓርቲው ሊቀመንበር ፓስፖርታቸው ተመለሰላቸው በአማራ ክልል በአምስት የምርጫ ወረዳዎች እንዳይወዳደሩ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰጥቶባቸው የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪዎች፣ ውሳኔው ተሽሮ እንዲወዳደሩ መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ትዕዛዝ መሰጠቱ ታወቀ፡፡ ትዕዛዙን የሰጠው አምስት ዳኞች የሚሰየሙበት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሲሆን፣ ከአምስቱ ዳኞች አንደኛው በትዕዛዙና ውሳኔው…
የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በመላ አገሪቱ ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ የመኖሪያ ቤቶች አስተዳደር አዋጅ ለማዘጋጀት ጥናት ማካሄድ ጀመረ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሚኒስቴሩ ከሚያዘጋጀው አዋጅ በመነሳት፣ ሲንጋፖርን ከመሳሰሉ አገሮች ልምድ በመቅሰም ደንብና መመርያ ለማዘጋጀት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መስፍን መንግሥቱ…
የንግድ ሕጉን ለማሻሻል የፖሊሲ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው በክርክር ሒደት ላይ እያሉ የሚቋረጡ የክስ መዝገቦች መበራከት ምክንያቱ ተከሳሾችንና ምስክሮችን ማቅረብ ባለመቻሉ መሆኑን፣ የፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው አምባዬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጹ፡፡ ሚኒስትሩ የ2007 ዓ.ም. የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለምክር ቤቱ ባለፈው ማክሰኞ ባቀረቡበት ወቅት፣ በክርክር ሒደት የሚቋረጡ የክርክር መዛግብትን ለመቀነስ…
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያና ቱርክ በመከላከያ ዘርፍ ሊተባበሩ የፈረሙትን ስምምነት በሙሉ ድምፅ አፀደቀው፡፡ በተመሳሳይም የምሥራቅ አፍሪካ የተጠንቀቅ ኃይልን ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ መጋቢት 24 ቀን 2007 ዓ.ም. አፅድቋል፡፡ ኢትዮጵያና ቱርክ ከሁለት ዓመት በፊት የተፈራረሙት የመከላከያ ኢንዱስትሪ ስምምነት፣ የኢትዮጵያን የመከላከያ አቅምን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከመገንባት ባሻገር ሁለቱ አገሮች የጦር መሣሪያዎችን በጋራ…
ባዜን እርሻና ኢንዱስትሪ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ለተበደረው ብድር በመያዣነት ያስያዘውን 10,000 ሔክታር መሬት ከሕግ አግባብ ውጪ በሆነ መንገድ ሸጦብኛል በማለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ክስ መሠረተ፡፡ ማኅበሩ ለፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት ያቀረበው የፍትሐ ብሔር ክስ እንደሚያስረዳው፣ ባዜን የእርሻና የኢንዱስትሪ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር…
በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጥራ ስትፈለግ የቆየችው አስካለ ደዴሶ ዴዴቦ በቅፅል ስሟ ቤቲ እና ተጠርጣሪ የወንጀል አጋሯ ሰሚራ ሀሰን ዓሊ በቁጥጥር ስር ዋሉ። ተጠርጣሪዎቹ በፌደራል ፖሊስ እና በአለምአቀፉ የፖሊስ ሃይል/ ኢንተርፖል የጋራ ጥረት ተይዘው አዲስ አበባ ገብተዋል። ግለሰቧ በቅርቡ በታንዛኒያ በአንድ ኮንቴይነር ውስጥ ታጭቀው ህይወታቸው ያለፈው 47 ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በ30…
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር (ኢሕባሴማ) ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት በቀረበው ሪፖርት በ2014 እ.ኤ.አ ሰባት ሺህ ለሚደርሱ ሴቶች ነፃ የሕግ ምክር አገልግሎት አበረከተ፡፡ ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል በተካሄደው ጉባኤ የማኅበሩ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ወይዘሮ ዜናዬ ታደሠ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመለከቱት ማኅበሩ ባለፈው አንድ ዓመት 6,997 ለሚሆኑ…
-የወረዳ አስተዳዳሪና የፖሊስ አዛዥ በክሱ ተካተዋል አንዱ ወገን በሌላኛው ወገን ላይ የጦር መሣሪያ እንዲያነሳ በመስማማትና በሚያስከትለው የወንጀል ድርጊት ላይ ሙሉ በሙሉ ተካፋይ በመሆን፣ ከ55 በላይ የሌላ ብሔር ተወላጆችንና የፌዴራል ፖሊሶችን በመግደል ወንጀል የተጠረጠሩ፣ የደቡብ ክልል ቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ 18 ነዋሪዎች ላይ መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡…
የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የሽብርተኝነት ክስ በመሠረተባቸው ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ላይ ምስክሮቹን ከመጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ማሰማት ጀመረ፡፡ ዓቃቤ ሕግ መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ባስያዘው ጭብጥ፣ በዕለቱ ያቀረባቸው ምስክሮች የደረጃ ወይም ታዛቢ ምስክሮች መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ፣ የሚመሰክሩትም ፖሊስ በተከሳሾቹ ቤት፣ በቢሮአቸውና በማዕከላዊ ምርመራ ቢሮ፣ ከተከሳሾቹ ላይ የተገኙ ማስረጃዎች…
-ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ማረሚያ ቤት መውረዳቸው ተጠቁሟል የጣሊያን ዜግነት አላቸው የተባሉት ራንቺፍ ፎክቲዎሊ የተባሉ ግለሰብ፣ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ዙርያ በሚገኝ ወላጅ አልባ ለሆኑና ለአካባቢው ልጆች የትምህርትና ዕርዳታ በሚሰጥ ድርጅት ውስጥ፣ በታዳጊ ወንድ ሕፃናት ላይ የግብረሰዶም በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸውን የሪፖርተር ምንጮች አረጋገጡ፡፡ ተጠርጣሪው መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር…