Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

-ለመርማሪዎች የይምሰል ጋብቻ ከመፈጸም እስከ ወንጀል ድርጊት መሳተፍ ይፈቅድላቸዋል -የውጭ ሥራ ስምሪት አዋጅም ለፓርላማው ቀርቧል ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ልዩ የምርመራ ቴክኒኮችን የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ለፓርላማ ቀረበ፡፡ ረቂቅ አዋጁ ‹‹ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡…
በደርግ መንግሥት ከ13 ዓመታት በላይ ታስረው ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠር በ1983 ዓ.ም. ከእስር የተፈቱት አምባሳደር ታደለች ኃይለ ሚካኤልና ቤተሰቦቻቸው፣ ለ40 ዓመታት በመንግሥት እጅ የነበረን ንብረታቸውን በፍርድ ቤት ክርክር በመርታታቸው እንዲመለስላቸው ፍርድ ተሰጠ፡፡ በአዋጅ 47/67 ተወርሶ ንብረትነቱ ለመንግሥት እንደተዘዋወረ በመግለጽ፣ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በእነአምባሳደር ታደለች የቀረበበትን ክስ ያስተባበለ ቢሆንም፣ ያቀረባቸው…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ፡፡ ዶ/ር አዲሱ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀ መንበር በመሆን ያለፉትን ሁለት አጠቃላይ ምርጫዎች ያገለገሉ ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲና አጋሮቹ 547ቱንም የፓርላማ መቀመጫ ያሸነፉበትን የ2007 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ በመምራት በሕግ የተፈቀደላቸውን…
በርካታ የግል ድርጅቶችና የሲቪክ ማኅበራት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረቡ፡፡ የምክር ቤቱ የማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ማሻሻያውን አስመልክቶ ባዘጋጀው የሕዝብ አስተያየት መስጫ መድረክ ላይ የተጋበዙ ከ300 በላይ የሚሆኑ የግል ድርጅቶችና ሲቪክ ማኅበራት፣ ማሻሻያውን ያረቀቀው የግል ድርጅት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ…
በሽብር ወንጀል ተከሰው በክርክር ሒደት ላይ ከሚገኙት ጦማሪያን መካከል አንዱ የሆነው ጦማሪ አቤል ዋቤላ ፍርድ ቤት በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ በመባል በአራት ወራት እስራት እንዲቀጣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ወሰነ፡፡ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ አቤል ዋቤላ በተከሰሰበት ወንጀል ክርክር ሂደት መልካም ጸባይ እንዳሳየ በመግለጽ የአራት ወራት እስራቱን በሁለት ዓመታት…
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባዮ ሴፍቲ ረቂቅ አዋጅን ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. አጸደቀ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ኃብትና የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት በማድረግና የማሻሻያ ሃሳቦችን በማቅረብ ሕጉ እንዲጸድቅ አድርጓል፡፡ 
የ16 ዓመቷን ታዳጊ ሐና ላላንጎን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽመውባት ለሕይወተ ህልፈት ዳርገዋታል በሚል የተከሰሱ 5 ግለሰቦች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈባቸው፡፡ የፌደራል ዓቃቤ ሕግ አምስቱን ግለሰቦች የአስገድዶ መድፈርና ከባድ የሰው ግድያ ወንጀሎች በሚሉ ሁለት ክሶች ክስ መሥርቶባቸው ጥፋተኛ ማስባሉ ይታወሳል፡፡ በተመሠረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ናቸው ብሎ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ…
-ሦስት የፓርቲው አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቆመ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በተመለከተ ሕዝቡ ሐዘኑን ለመግለጽና የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለማውገዝ፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በተደረገው ሠልፍ ላይ፣ ብጥብጥ እንዲፈጠር አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው በታሰሩ ሰባት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና በሁለት ግለሰቦች ላይ ግንቦት 4 እና 3 ቀን 2007…
-በፍርድ ቤቶችና በባለሥልጣኑ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ጻፈ - ‹‹የተጣለበት ኃላፊነት ለመወጣት እንዲችል የተፈለጉት ሰነዶች መቅረብ አለባቸው›› የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተጠረጠረበትን ‹‹ደረሰኝ ሳይቆርጡ ሽያጭ ማከናወን›› ወንጀል በሚመለከት፣ ምርመራ ለማካሄድ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የብርበራ ትዕዛዝ ከፍርድ ቤት ያወጣ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ከሰጠው…
‹‹ፌዴራል መንግሥት ለክልሎች የደመወዝ ጭማሪ የማድረግ ሥልጣን የለውም›› ባለሙያዎች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ያዘጋጀውና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ ይሁንታ ያገኘውን የስምንት ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ፓርላማው ሚያዝያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. አፀደቀ፡፡ ይሁን እንጂ ፓርላማው ባፀደቀው ተጨማሪ በጀት ላይ የሕግ ክርክሮች እየተነሱ ነው፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የተጨማሪ በጀት…
ቁርጥራጭ ብረቶችን ወርቅ በማስመሰል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ከ95.5 ሚሊዮን ብር በላይ አጭበርብሮ ተሰውሯል ተብሎ በሌለበት 25 ዓመታት ጽኑ እስራትና 180 ሺሕ ብር የተፈረደበት አቶ አስማረ አያሌው፣ የቅጣት ውሳኔው ተሰርዞ ክሱ እንደ አዲስ እንዲጀምር ተወሰነ፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዝያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ውሳኔውን ያሳለፈው፣ ግለሰቡ ‹‹በሌለሁበትና…
-ሰማያዊ ፓርቲ መንግሥት ከስም ማጥፋት ዘመቻ ይታቀብ አለ በኢትዮጵያውያን ላይ የአይኤስ አሸባሪ ቡድን የፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በተደረገው ሠልፍ ላይ፣ ሆን ብለው ብጥብጥ ያስነሱትና ሁከት እንዲፈጠር ያደረጉት፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት መሆናቸውን ማረጋገጡን የፌዴራል ፖሊስ ገልጾ፣ ክስ እንዲመሠረት ለዓቃቤ ሕግ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡ በክሱም የሰማያዊ ፓርቲ…
የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋኩልቲ የሥነ አዕምሮ ዲፓርትመንትና ከአማኑኤል ሆስፒታል ጋር በመተባበር የአዕምሮ ጤንነት ችሎት ማቋቋሙ ታወቀ፡፡ ሚያዝያ 9 እና 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በቸርችል ሆቴል ባለድርሻ አካላት ከሆኑት የፖሊስ አባላት፣ ዳኞች፣ ዓቃቢያነ ሕግ፣ የምርመራ ክፍል ሹሞች፣ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች፣ የአማኑኤል ሆስፒታል ሐኪሞች፣ የሰላም አምባሳደሮችና ሌሎችም…
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ማክሰኞ በዋለው መደበኛ ጉባዔው፣ የሁለት የፌዴራል ዳኞችን ሹመት አነሳ፡፡ ውሳኔውን ያስተላለፈው ሁለቱ ዳኞች በሙስና ወንጀል ተከሰው ጥፋተኛ መሆናቸውን ካረጋገጠ በኋላ መሆኑ ታውቋል፡፡ የፌዴራል ዳኞችን ሹመት የሚያፀድቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን፣ ከሹመት የሚያነሳውም ራሱ ፓርላማው እንደሆነ በሕግ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሠረት የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ታኅሳስ…