Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

‹‹መጠየቅ ካለብኝ በክልል እንጂ በፌዴራል አይደለም›› አቶ ወንድሙ ቢራቱ ለመንግሥት መግባት የነበረበትን ተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች የመንግሥት የግብር ገቢዎች በማጭበርበር በግላቸውና በዘመዶቻቸው ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በማካበት በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት፣ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ወንድሙ ቢራቱ ሰው በመግደል ወንጀል መጠርጠራቸው ለፍርድ ቤት ተገለጸ፡፡ ነሐሴ 3…
ስካይ ባስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ከሦስት ዓመት በፊት በመንገደኞች ላይ ላደረሰው ጉዳት ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት፡፡ ስካይ ባስ ጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር 48 ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ እያለ ዓባይ ድልድይ መዳረሻ ላይ ተገልብጦ ላደረሰው የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ውሳኔ የሰጠው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ…
የኢትዮጵያ አዕምሮዊ ንብረት ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ከአንድ ዓመት በፊት ሚያዝያ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. በክራውን ሆቴል (Crown Hotel) እና በክራውን ፕላዛ (CROWNE PLAZA) ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐምሌ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. የፀና ቢሆንም፣ ክራውን ሆቴል ጉዳዩን ወደ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመውሰዱ ታገደ፡፡…
The 2016 United Nations Regional Course in International Law for Africa is organized by the Codification Division of the United Nations Office of Legal Affairs in cooperation with Ethiopia, the United Nations Economic Commission for Africa (ECA) and the African Union. The Regional Course will be held at the facilities…
ቢጂአይ ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ የሚሸጥላቸውን የድራፍት መጠን አሳንሶ መግለጹንና መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ግብር ደንበኞቹ እየሰወሩ መሆኑን በመጠቆማቸው፣ በሕግ አግባብ የሚገባቸውን ክፍያ ለማግኘት ጠቋሚዎች ባደረጉት ክርክር የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን አሸነፉ፡፡ ባለሥልጣኑና በጠበቃ ተሻገር ደሳለኝ የተወከሉት ሦስት ጠቋሚዎች ክርክር፣ አምስት ዳኞች በሚሰየሙበት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተጠናቀቀው፣ የፌዴራል ከፍተኛ…
-በመቶ ሚሊዮን ብሮች ተጠርጥረዋል በከባድ ሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ላለፉት ሁለት ወራት ሲፈለጉ የቆዩት የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ቢራቱ፣ ነሐሴ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ አቶ ወንድሙ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በፌዴራልና በኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ጥምረት ነው፡፡ በሁለቱ ፀረ ሙስና…
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ሰሚት ምድብ በእነ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተጠቀሱ 18 ተከሳሾችን ዛሬ ከ7 አመት እስከ 22 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ቀጥቷቸዋል። 22 አመት የተቀጡት ፍርድ ቤቱ በሽብር ወንጀሉ ከፍተኛ ሚና ነበራቸው ያላቸው አቡበክር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ እና ከሚል ሸምሱ ናቸው። ችሎቱ በመዝገቡ…
ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም የተጠየቀበት የእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ ይነሳልን አቤቱታ ከሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም አያስፈልገውም ተባለ። ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዲሱን የጉሙሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀጽ 182ን በመጥቀስ ክስ ይነሳልን ወይም ይቋረጥልን በማለት አቤቱታ ያቀረቡት አቶ መላኩ ፈንታ እና አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ 8 ግለሰቦችና 5…
በአዲስ አበባ በተለያዩ አከባቢዎች በመንገድ ግንባታው ዘርፍ የተሰማራው የእስራኤሉ ትድሃር ኩባንያ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ሚናሼ ሌሺ ጉቦ በመስጠት እና በታክስ ስወራ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ። የፌደራል ስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤህግ ግለሰቡን ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያስደረገው በኢትዮዽያ ገቢዎች እና ጉሙሩክ ባለስልጣን ለሚሰሩ 3 ኦዲተሮች 1…
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ የወንጀል ችሎት አቶ መላኩ ፈንታና አቶ ገብረዋሀድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ 8 ግለሰቦችና 6 ኩባንያዎች በክስ ይነሳልንና ይቋረጥልን አቤቱታ ላይ የምክር ቤትን ምላሽ ለመጠበቅ የተያዘውን ቀጠሮ በአንድ ሳምንት አሸጋገረ። ችሎቱ አዲሱ የገቢዎችና ጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንድ አንቀጽ ከህገ መንግስት አንቀጽ 22 ንዑስ ቁጥር 2 ጋር ስለሚቃረን ፤…
በተለያዩ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በመተወን የምትታወቀው ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን እና ግብረ አበሯ በእስራት ተቀጡ። በአዲስ አበባ ከተማ በኮልፌ ቀራንዮ ነዋሪ የሆኑት ተከሳሾቹ በእስራት የተቀጡት ከታዘዘላቸው ውጭ ተጨማሪ ገንዘብ ከባንክ ቤት በማውጣት ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ነው። የ22 አመቷ ተዋናይት ከግብረ አበሯ ጋር በመሆን በተሰጣቸው የ4 ሺህ ብር ቼክ ላይ ከፊት…
በሽብር ወንጀል ተፈርዶባት በይግባኝ በአምስት ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥታ በማረሚያ የነበረችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ትናንት የአመክሮ ጊዜዋ ተጠናቆ ከእስር ተለቀቀች። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የወንጀል ችሎት ግለሰቧ በእነ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በሶስት የሽብር ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብላ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥታ ነበር። በይግባኝ ባደረገችው ክርክር የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት…
ድረ ገፅ ተጠቅመው የተለያዩ ፅሁፎችን በማውጣት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ከተከሰሱት አስር ግለሰቦች መካከል አምስቱ ክሳቸው ተነስቶ ዛሬ ማምሻውን ከእስር ተፈቱ። ክሱ ሊነሳ የቻለው የፍትህ ሚኒስቴር በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን ትናንት ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደብዳቤ መፃፉን ተከትሎ ነው። በዚህም መሰረት ክሳቸው…
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በእነ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የዓቃቤ ሕግን እና የመከላከያ ምስክሮችን ቃል በንባብ አሰምቶ ማጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ በ18 ተከሳሾች ላይ ፍርድ ሰጥቷል። በዚህም መሰረት አቡበከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ፣ ካሚል ሸምሱ፣ በድሩ ሁሴን፣ ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሀመድ አባተ፣ አህመድ ሙስጠፋ፣…