Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

በፈረንሣይ ፓሪስ በሚገኘው የዓለም አቀፍ ንግድ ምክር ቤት የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት፣ ፔትሮትራንስ ኩባንያ ሊሚትድ የተሰኘ የቻይና ኩባንያ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የመሠረተው የ1.4 ቢሊዮን ዶላር ክስ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተደመደመ፡፡ የፍርድ ቤት ክርክሩ በጄኔቫ ስዊዘርላንድ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲካሄድ ቆይቶ፣ ፍርድ ቤቱ ሰኞ ጥር 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ውሳኔ መስጠቱን ከታመኑ…
አዋጁ ቀደም ሲል በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ይፀድቃል ተብሎ ቢጠበቅም በውስጡ ውስብስብና አከራካሪ ጉዳዮችን በመያዙ ሊዘገይ እንደቻለ ተገልጻል። በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ በሕዝባዊ ውይይቶች፣ ከተለያዩ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም በሥራው ከሚሳተፉ አካላት ጋር በተካሄዱ መድረኮች ጠቃሚ ሀሳቦችና ረቂቁን የሚያዳብሩ ሀሳቦች ተገኝተዋል። ከዚህ በመነሳትም 28 የሚደርሱ አንቀጾች መሻሻላቸው ተገልጻል። አዲሱ የውጭ ሀገራት…
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከዚህ በታች በተመለከተው ርዕስ ላይ የግማሽ ቀን የልምድ ልውውጥ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም የማኅበሩ አባላት፣ ተባባሪ አባላት እና የሕግ ባለሙያዎች በመድረኩ ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል፡፡ ርዕስ፡- “የሕግ ነክ ጽሑፎች መጣጥፍ፣ መጽሐፍ፣ ጡመራ ልምድ ልውውጥ መድረክ” ጽሑፍ አቅራቢዎች፡- 1. አቶ አበበ አሳመረ /የማኅበሩ ም/ፕሬዚዳንት፣ የሕግ አማካሪና ጠበቃ/ 2. አቶ…
ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዕጩ ዳኝነት ከተወዳደሩት ውስጥ ለቀጣዩ የቃል ፈተና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ይፋ ሆነ፡፡ የቃል ፈተናው ሕዳር 18 እና 19 ቀን 2008 ዓ.ም እንደሚሰጥም ታውቋል፡፡ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽሕፈት ቤት እንደገለፀው ቀደም ሲል በተሰጠው የጽሑፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ያመጡ ተወዳዳሪዎች ለቃል ፈተና እንዲቀርቡ…
መጥሪያ በመኖሪያ ቤቷ ላይ ቢለጠፍላትም አለመቅረቧ ተገልጿል የቤጂንግ ኦሎምፒክ ድርብ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የእሷ መሆኑ የተገለጸው የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪ፣ በተሳፋሪዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት በማድረሱ ምክንያት በተመሠረተባት የፍትሐ ብሔር ክስ ቀርባ ባትከራከርም፣ በኦሮሚያ ክልል የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጉዳት ካሳ እንድትከፍል ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡ ክሱ የተመሠረተው በአትሌት…
-የአዕምሯዊ ጽሕፈት ቤት ውሳኔ ተሽሯል ታዋቂው ነጋዴ አቶ ይርጋ ኃይሌ የመሠረቱት ካንጋሮ ፕላስቲክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ በሞጆ ከተማ በገነባው የቢራ ኢንዱስትሪ ፋብሪካ ለሚያመርተው የዋልያ ምሥል ያለው “IBEX” በማለት ያስመዘገበውን የንግድ ምልክት፣ ለሌላ አካል መሰጠቱን በመቃወም ባቀረበው አቤቱታ አሸናፊ ሆነ፡፡ ካንጋሮ ፕላስቲክ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው ይግባኝ አሸናፊ የሆነው…
ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረ ገፅ ተጠቅመው የተለያዩ ጽሑፎችን በማውጣት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል በሚል የተከሰሱ አራት የዞን9 ጦማርያን ከክሱ ነፃ በማድረግ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ወሳኔ የተላለፈው በጦማርያን ሶልያና ሽመልስ፣ አቤል ዋበላ ሱጌቦ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሃይሉ እና አጥናፉ ብርሃኔ ላይ…
የሠራተኛ የደመወዝ ገቢ ግብር ተሻሻለ በሚል የተለቀቀው መረጃ እውነትነት የሌለው መሆኑን የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን አስታወቀ። የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው በተቋሙ ደረጃ ገና እየታየ ያለ ረቂቅ ነው። በማማሻያው ላይ ከክልሎች የገቢ ቢሮዎች ጋር ውይይት ተደርጎ እንደተተቸ እና ከዚህ በኋላም ማሻሻያ ተደርጎ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር እንደሚቀርብ ባለስልጣኑ አስታውቋል። ቀጥሎም…
በጋምቤላ ክልል በተለይም በአማራ ተወላጆችን (ደገኞች) ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ በማፈናቀልና በመግደል ወንጀል የተጠረጠሩ 46 የቀድሞ የክልሉ ሹማምንት ክስ ሰሞኑን በአዲስአበባ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ቀረበ። ከቀበሌ እስከ ዞን በአመራርነት ርከን ነበሩ የተባሉት ተከሳሾች ባቀጣጠሉት ግጭት 126 ሰዎች በግፍ የተገደሉ ሲሆን ከ7 ሺህ የሚልቁ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። የፌደራል…
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ አዋጅ ሊሻሻል መሆኑን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ። በአዲስ መልክ የሚሻሻለው አዋጅ ላለፉት 8 ዓመታት ተግባራዊ ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ያለ ነው። የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክተርአቶ ጥላሁን ንጉሴ እንደተናገሩት፥ በስራ ላይ ያለውን አዋጅ ክፍተት በጥናት በመለየት ነው ማሻሻያ የሚደረግበት። በድሮውና በአዲሱ መንጃ ፈቃድ እየደረሰ ያለውን…
አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ለቡ አካባቢ በሚገኝ መዝናኛ ቤት ውስጥ ሰኞ ምሽት አንዲት ወጣት መግደሉ ተሰማ፡፡ ግለሰቡ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ተርፎ በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡ ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ከጓደኛዋ ጋር በመሆን በለቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ በሚገኝ የጓደኛቸው መዝናኛ ውስጥ በመዝናናት ላይ እያሉ ነው ከተጠርጣሪው ገዳይ ጋር የተገናኙት፡፡ ለጊዜው…
የፌዴራል የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ለፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዳኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት በ25/11/2007 የተፈተኑ ተወዳዳሪዎች ከ100% ያመጡትን ውጤት አስታውቋል፡፡ አቢሲኒያ ሎው የተፈታኞችን ውጤት በቀላሉ ለመከታተል ያመች ዘንድ የፌዴራል የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የለጠፈውን የፈተና ውጤት ከዚህ በታች አቅርቧል፡፡ የፌዴራል የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ለቃል ፈተና የሚፈለጉትን ወደፊት በሚያወጣው ማስታወቂያ መሠረት…
መኪና ለመዝረፍ በማሰብ አሽከርካሪና ረዳቱን ገድለው ገፈርሳ ወንዝ ውስጥ የከተቱ ሁለት ተጠርጣሪዎች ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው ወንጀሉን መፈጸማቸውን አመኑ። ወቅቱ ነሐሴ 14፣ 2007 ምሽት 2 ሰዓት ነው፤ ሟች ኤፍሬም ተሾመ እና ሰለሞን አድነው የተሰኙ የ22 እና የ13 ዓመት ረዳት ሚኒባስ ታክሲ ኮንትራት…
አዲሱ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 የመሸጋገሪያ ድንጋጌ አንቀጽ 182 ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 22(2) ጋር እንደሚጋጭ በመግለጽ፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል በማለት ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ተልኮ ጉባዔው “አይጋጭም” ብሎ ውሳኔ መስጠቱን በመቃወም፣ እነ አቶ መላኩ ፈንታ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ ጉዳዩን እየመረመረ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ…