Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም ባካሔደው ስብሰባ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙትን ክቡር አቶ ጌታቸው አምባዬን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አድርጎ ሾመ፡፡ ምክር ቤቱ ሹመቱን አዲስ ለተዋቀረው ለፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት ያፀደቀው ጠቅላይ ሚንስትሩ ለምክር ቤቱ ሹመቱ እንዲፀድቅ ባቀረቡት መሠረት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ …
በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የተፈጸመው የህክምና ስህተት አነጋጋሪ ሆኗል ችግሩ የተፈጠረው እንቅርቷን በቀዶ ጥገና ለማስወጣት የሁለት አመት ቀጠሮ በተሰጣት ሰላም ደሞዜ እና የሃሞት ጠጠሯን በቀዶ ጥገና ለማስወገድ የህክምና ቀጠሮ በያዘችው ሰላም ሃጎስ ላይ ነው፡፡ ጉሮሮዋ ላይ ከእንቅርት ጋር የተያያዘ የጤና ችግር ያጋጠማት ሰላም ደሞዜ በዘውዲቱ ሆስፒታል ተከታታይ ህክምና ስታደርግ ቆይታ ከሁለት…
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዕድሜያቸው እስከ ሦስት ዓመት የሆኑ የሠራተኞቻቸውን ልጆች ማቆያ ማዕከላት እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ሰማን፡፡ የፐብሊክ ስርቪስና የሰው ኃብት ልማት ሚኒስቴር የመንግሥት ሠራተኞች ዕድሜያቸው እስከ ሦሰት ዓመት ያሉ ህፃናት የሚቆዩበት ማዕከላት በተቋማት ማቋቋምን ጨምሮ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደረጉ ሃሳቦች በሚሻሻለው የመንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አካቷል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ መንግሥት…
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ16ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ለይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ ለዝርዝር እይታ ለሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ መወሰኑ ይታወሳል። ቋሚ ኮሚቴው በረቂቅ አዋጁ ላይ ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና የህብረተሰብ ክፍሎች ዝርዝር ውይይት በማካሄድ ሪፖርትና የመነሻ…
የኮምፒዩተር ወንጀል ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡ በወታደራዊ ወይም ለዓለም አቀፍ ግንኙነት ሲባል በተሰየመ የኮምፒዩተር ዳታ ላይ የወንጀል ጥፋት የተሰነዘረ እንደሆነ፣ ድርጊቱ ከ15 እስከ 25 ዓመታት ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ይገልጻል፡፡ ይህ ቅጣት የሚጣለው ለወታደራዊና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሲባል ጥብቅ ሚስጥር በተባለ የኮምፒዩተር መረጃን (ዳታ) ያለፈቃድ ያገኘ፣ በሕገወጥ መንገድ የጠለፈ፣ እንዲሁም በኮምፒዩተር…
የቀድሞው የአክሰስ ሪል ስቴት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የ500 ሺህ ብር ዋስትና ተፈቀደላቸው። መርማሪ ፖሊስ ከተጠርጣሪና ከምስክሮች ቃል መቀበልን ጨምሮ የሰነድ ማስረጃዎችን መሰብሰብ፣ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ማስረጃዎችን እንዲልኩ ማድረግ የሚሉትና መሰል ስራዎችን ሰርቺያለሁ በማለት ለቀሪ ስራዎች የ14 ቀን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። የአቶ ኤርሚያስ አመልጋ ጠበቆችም ፖሊስ የተሰጠው ጊዜ…
- የአቶ ኤርሚያስ ጠበቆች የምርመራውን ሒደት ተቃወሙ የአክሰስ ሪል ስቴት ኩባንያ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ ለነበሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ በአካውንታቸው በቂ ስንቅ (ገንዘብ) ሳይኖራቸው ደረቅ ቼክ በመጻፋቸው የተጀመረባቸው ምርመራ ወይም ክስ ካለ እንዲቋረጥ ፍትሕ ሚኒስቴር ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ስላስተላለፈው (ስለበተነው) የዋስትና ደብዳቤ እንደማያውቅ፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን የካቲት 14 ቀን…
ሀሰተኛ ሰነድ በማቅረብ የሌላቸውን የተቋራጭነት ደረጃ ያገኙና ለፕሮጀክቶች መጓተት መንስኤ የሆኑ ከ500 በላይ የስራ ተቋራጮች ታገዱ። የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው፥ እነዚህ ተቋራጮች ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 4 ወስደው ሲሰሩ የነበሩ ናቸው። በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማትና ሬጉላቶሪ ቢሮ በዚህ ዓመት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ እና በተለይም ከደረጃ 1 እስከ…
በ2001 የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት በመሆን ተሹመው ለሰባት ዓመታት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትነት ሲያገለግሉ የቆየቱት አቶ ተገኔ ጌታነህ ሥራቸውን በፈቃዳቸው ከሥራቸው የለቀቁ መሆኑን ፎርቹን ጋዜጣ ገለጸ፡፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንቱ ከሳምንት በፊት መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡ መሆኑ የታወቀ ሲሆን የመልቀቂያቸው ምክንያት ከጤና ጋር የተያያዘ መሆኑን በደብዳቤያቸው እንዳሰፈሩ ተገልጻል። ይህ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ…
በሽብር ወንጀል ከተመሰረተባቸው ክስ በነጻ መሰናበታቸውን ተከትሎ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የአንድነት፣ ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ እና የአረና ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሽበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ አብርሃም ሰሎሞን እና የሺዋስ አሰፋ ላይ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠየቀባቸው ይግባኝ ክርክር ላይ ቆይተው የካቲት 3 2008 ዓ.ም ችሎቱ አምስቱም ተከሳሾች ጉዳያቸውን ከማረሚያ…
የንግድ ሚኒስቴር የአባላት ቅርንጫፍን በማብዛት የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን እንደሚያስገኝ እየገለፀ ሲሰራ የነበረው ቲያንስ የተባለው ድርጅት ንግድ ፈቃድ ማገዱ ተሰማ፡፡ ድርጅቱ ከአሁን በፊት የወሰደው ፈቃድ እና እያከናወነ ያለው ተግባር የማይጣጣም በመሆኑ እንዲያስተካክል ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ከስህተቱ ሊታረም አለመቻሉን ሚኒስቴሩ ገልጾ ሕገ ወጥ ተግባር ሲያከናውን ስለነበረ ድርጅቱ መታገዱን ነው አስታውቋል፡፡ ቲያንስ ኢትዮጵያ ቢዝነስ በአውሮፓውያኑ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ሳምንት በፊት ያረቀቀውና በውጭ ምንዛሪ ንግድ ላይ ግልጽነት እንዲሰፍን የሚያደርግ ነው የተባለለት መመርያ፣ ከየካቲት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታወቀ፡፡ የፀደቀው መመርያ በረቂቁ ላይ ያልተካተቱ ማሻሻያዎች የያዘ ሲሆን፣ በዋነኝነት በገቢ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ለአንድ ወደ አገር ውስጥ ለሚገባ የገቢ ዕቃ ከአንድ ባንክ በላይ…
በሌላ ሰው የተፃፈን መፅሀፍ የራሱ ለማድረግ ሲል ገዳዮችን በመቅጠር ያሰማራው ግለሰብና በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ የፈፀሙት አምስት ተከሳሾች በሞት እና እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ። ተከሳሾች አበባየሁ ሳሙኤል፣ አስፋው አጌቦ፣ መካሻ ብርሃኑ፣ ኤፍሬም ዋደላ፣ ወጣት ሜሮን አየለና አብርሃም አቶታ ናቸው። 1ኛ ተከሳሽ አበባየሁ ሳሙኤል የመጀመሪያ ዲግሪ ያለውና የልብ ወለድ…
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የቀረቡትን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶችን ሹመት አፀደቀ። በዚህ መሠረት አቶ በላቸው አኑቺሳ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሁም አቶ መሀመድ አህመድ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል። አቶ በላቸው ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ዲፕሎማ፣ ከሲቨል…