Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

ሀሰተኛ የአባላት ዝርዝር በማዘጋጀት ያቋቋመው የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር እውቅና እንዲያገኝ አስደርጐ መሬት ወስዷል የተባለው ግለሰብ በ8 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ፣ የወሰደው መሬትም ለመንግሥት ገቢ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 18ኛ ችሎት ባሳለፈው የፍርድ ውሳኔ በህገ-ወጡ የመኖሪያ ህብረት ስራ ማህበሩ ስም ለቦታው የተሰጡ 4 ካርታዎችም እንዲመክኑ ተወስኗል፡፡…
አድራሻቸው በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ የሆኑ ሦስት የፖሊስ መኮንኖች፣ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣት አንድ ሰው አፍነው ወደ ጅግጅጋ በመሄድ ላይ እያሉ ተይዘው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡  በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎቹ ዋና ኢንስፔክተር ጐይቶም አረጋዊ ኪዳነ ማርያም፣ ረዳት ኢንስፔክተር አንተነህ አስናቀ ተፈራና ኮንስታብል ዘሪሁን ሲሳይ…
ከኤርትራ መንግሥት የመረጃ ሠራተኞች ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት በመፍጠር፣ ከጥቅምት ወር 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት ወር 2006 ዓ.ም. ድረስ፣ በኢትዮጵያ ድንበር ላይ ስለሚገኘው፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወቅታዊ ሁኔታ በመሰለልና መረጃ በመስጠት የተጠረጠሩ ዘጠኝ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ ዓቃቤ ሕግ፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሠረተባቸው ኢትዮጵያውያን ከሀሠ…
ለሥነ ጽሑፍ፣ ለኪነ ጥበብና፣ ለፎቶግራፍ ሥራዎች ጥበቃ በሚያደርገው የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ቁጥር 410/96 ላይ የተደረገውን ማሻሻያ ፓርላማው አፀደቀው፡፡  ማሻሻያው ለንግድ ዓላማ የታተመ የድምፅ ሪከርዲንግ እንደ ካፍቴሪያዎች፣ መዝናኛ ቦታዎች ባሉ ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ከቀረበ ወይም እንደ ምሽት ክበቦች ባሉ ቦታዎች በይፋ ከተከወነ ወይም ደግሞ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በተለያዩ ድረ ገጾችና በመሳሰሉት…
- ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ የጠየቀው ጊዜ ተፈቀደለት ከትምህርት ቤት ወደ ቤቷ ለመሄድ በተሳፈረችበት ሚኒባስ ታክሲ ተገዳ ከተወሰደች በኋላ፣ በደረሰባት በቡድን የመደፈር ጥቃት ምክንያት ሕይወቷ ያለፈው ተማሪ ሃና ላላንጐ ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡ ድርጊቱን ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ተጠርጣሪዎች፣ ድርጊቱን እንዳልፈጸሙ በመካድ ኅዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው…
የአንድነት፣ የአረናና የሰማያዊ ፓርቲዎች አመራሮች ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ስለሺ፣ የሺዋስ አሰፋና አብርሃ ደስታን ጨምሮ በሽብርተኝነት የተከሰሱ አሥር ተጠርጣሪዎች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የመሠረተውን የሽብርተኝነት ክስ እየመረመረው የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ ኅዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት…
በግለሰብ ነጋዴዎች ላይ የሚጣል ግብርና ታክስ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ አስነሳ- ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ልኮታልየአዲስ አበባ ከተማ ግለሰብ ነጋዴዎች የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94ን ተላልፈዋል በሚል፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሚመሠርትባቸው ክስ የሕገ መንግሥት ጥያቄ አስነሳ፡፡ባለሥልጣኑ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 መሠረት በአዲስ አበባ ግለሰብ ነጋዴዎች…
ከአልሸባብና ደቡብ አፍሪካ ከሚገኝ የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት ነበራቸው ተብሏል መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል በጅሃድ ጦርነት እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም በጅማ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች፤ ሰሞኑን ፍ/ቤት ቀርበው ክሣቸው ከተሰማ በኋላ የክስ መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡  በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ባለፈው ረቡዕ ክሣቸው በንባብ የተሰማው 7 ተጠርጣሪዎች፡-…
ከ575 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ ሲያዘዋውር የተገኘው የ29 አመቱ ወጣት ዛሬ በስምንት አመት ከአምስት ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ። ተከሳሹ አብዱልፈታህ ሙስጠፋ የሚባል ሲሆን፥ በፌደራል ፖሊስ ነው በህገወጥ መንገድ ዶላር ሲያዘዋውር የተያዘው። ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ከተለያዩ ግለሰቦች 29 ሺህ 551 የአሜሪካን ዶላር ይዞ በፖሊሶች የታየው…
አቶ ዮናስ ካሳሁን የተባለ ግለሰብ የወ/ሮ አኪኮ ስዩምን ኢ-ሜይል አድራሻ የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ያለ ግለሰቧ ፈቃድ ባልታወቀ መንገድ በመጠቀም ግለሰቧ ከተለያዩ ሰዎችና ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን የመረጃ ልውውጥ ወደራሱ አድራሻ በመላክ፣ በማጥፋትና ለ3ኛ ወገን አሳልፎ በመስጠት ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ፡፡ ግለሰቡ በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኝ ሲሆን የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ፍ/ቤቱ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር በሱዳን ካርቱም ባለፈው ዓመት ታኅሳስ ወር ላይ የተፈራረሙት የወንጀል ጉዳዮች የጋራ ትብብር ስምምነት፣ ባለፈው ሐሙስ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡  ስምምነቱ 26 አንቀጾችን የያዘ ሲሆን፣ ወንጀል የፈጸመ የአንድ አገር ዜጋ ወይም ሕጋዊ ሰውነት ያለው አካል በሌላኛው አገር እንደሚኖር ከተጠረጠረ፣…
‹‹የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅን ይቃረናል›› የፓርላማ አባላት ለሥነ ጹሑፍ፣ ለኪነ ጥበብና ለሳይንሳዊ የፈጠራ ሥራዎች ጥበቃ የሚያደርገውን አዋጅ ቁጥር 410/96 የሚያሻሽል ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ሐሙስ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡ ረቂቅ አዋጁ ባለ አምስት ገጽ ማሻሻያ አንቀጾችን የያዘ ነው፡፡ በሥራ ላይ የሚገኘው አዋጅ ጥበቃ የሚያደርግለትን የታተመ ሥራ አንድ ኮፒ ለግል…
-መኖሪያ ቤቱ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ዕግድ ተጣለበት ድምፃዊ ንዋይ ደበበ መልካም ግንኙነትና ወዳጅነት እንደነበራቸው ከሚናገሩት አቶ ኤፍሬም ኤርሚያስ ከሚባሉ ግለሰብ 20,000 ዶላር ተበድሮ ‹‹አልከፍልም›› ብሏል ተብሎ ፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተበት፡፡ ድምፃዊውና አበዳሪ መሆናቸውን የሚናገሩት ግለሰብ በነበራቸው መልካም ግንኙንት አማካይነት ከስድስት ዓመታት በፊት ገንዘቡን እንዳበደሩት በክሱ ላይ ሰፍሯል፡፡ ‹‹በአሜሪካ ያሉብኝን አንዳንድ ዕዳዎች…
ፍትህ ጋዜጣን እያሳተመ ሲያሰራጭ የነበረው ማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ስራ ድርጅት በ10 ሺህ ብር ተቀጥቷል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 9ኛ የወንጀል ችሎት ተመስገን ጥፋተኛ ነህ የተባለባቸውን ሶስት ክሶች በአንድ ሀሳብ ቅጣቱ ተፈፃሚ ይሁን ብሎ መፍረዱን ተከትሎ ነው በሶስት አመት ፅኑ እስራት የተቀጣው። አቃቤ ህግ ከዚህ ቀደም የወንጀል ህግ 257 ጠቅሶ በመገፋፋትና ግዙፍ…