Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

ማረሚያ ቤት ምላሽ እንዲሰጥ ፍ/ቤት አዝዟል “የግንቦት 7 አባል በመሆን በሽብር ድርጊቶች ተሳትፈዋል” በሚል ክስ የተመሰረተባቸው የአንድነት፣ የሰማያዊ እና የአረና ፓርቲ አመራሮች፤ ሌሊት በማረሚያ ቤት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶች እንደተወሰደባቸው ባለፈው ረቡዕ ለፍ/ቤት አመልክተዋል፡፡ በእነ ዘላለም ወርቅ አገኘው መዝገብ የተከሰሱት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀብታሙ አያሌው፣…
መቀመጫውን ኤርትራ ውስጥ ያደረገውና ራሱን የትግራይ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ በማለት የሚጠራው የሽብር ድርጅት አባል በመሆን በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የዝርፊያ፣ የእገታና የግድያ ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ሰባት ተከሳሾች ክስ ተመሰረተባቸው። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶታል። ተከሳሾቹ 1ኛ ግርማ ልዑል አረጋይ፣ 2ኛ ሙቀት ንጉስ፣ 3ኛ ሀይለ በላይ…
-ሁለት ጠበቆች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ትዕዛዝ ተላለፈባቸው በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በሚኒስትር ማዕረግ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ፣ ጥብቅና የቆሙላቸውን ጠበቆች እንዲሰናበቱና የሚያርፍባቸውን ውሳኔ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲሰሙ፣ ክሱን እየመረመረው የሚገኘውን ፍርድ ቤት ትናንትና ጠየቁ፡፡ አቶ መላኩ ፈንታ ጥያቄውን ያቀረቡት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት…
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት የአገር ውስጥ ኃላፊ የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በምርመራ ወቅት ተፈራርመው የተረካከቡበትን ሰነድ (ቨርቫል) ሊሰጣቸው ባለመቻሉ፣ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን ለፍርድ ቤት ታኅሳስ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. አመለከቱ፡፡ አቶ ወልደ ሥላሴ ክሱን እየመረመረው ላለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት…
-የተጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ተሰረዘ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አሥረኛውን ጠቅላላ ጉባዔ ታግዶ እንዲቆይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ለማሳገድ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ሆነ፡፡ ታኅሳስ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ለማካሄድ የታቀደው ጠቅላላ ጉባዔ መሰረዙን ንግድ ምክር ቤቱ አስታወቀ፡፡ ንግድ ምክር ቤቱ ከኅብረት ኢንሹራንስ…
ትላንት ሐሙስ በኬንያ ፓርላማ የቀረበው አዲሱ የጸረ ሽብር ረቂቅ ታላቅ ተቃውሞ ማስነሳቱ ተዘገበ፡፡ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ በሆኑነት ጀስቲን ሙቱሪ ላይ መጽሐፎች፣ ሰነዶችና የተለያዩ ዕቃዎች በተቋዋሚዎች ሲወረወርባቸው ፖሊስ በበኩሉ በመንገድ ላይ ተቋውሞ ሲያደርጉ የነበሩ ሰልፈኞችን በመበተን ስምንት የሚያህሉ ሰልፈኞችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ ይህንን ውዝግብ የሚያሳይ ቪዲዮ ከዚህ በታች ይመልከቱ
ሃና ላላንጎ የተባለች የ16 ዓመት ታዳጊ ተማሪ በቡድን በመፈራረቅ አስገድደው በመድፈር ለሞት ዳርገዋታል በሚል በተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች ላይ፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ታኅሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ መሠረተ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሳምሶን ስለሺ፣ በዛብህ ገብረ ማርያም፣ በቃሉ ገብረ መድኅን፣ ኤፍሬም አየለና ተመስገን ፀጋዬ የተባሉ የታክሲ ሾፌሮችና ረዳቶች ሲሆኑ፣ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ…
አራጣ በማበደር ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸውና እስከ 500 ሺሕ ብር በሚደርስ ዋስ ተፈትተው ክሳቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች፣ በዓቃቤ ሕግ ምስክር ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ እያደረሱባቸው መሆኑን ክሱን እየመረመረው ለሚገኘው ፍርድ ቤት አመለከቱ፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በአራጣ አበዳሪነት ወንጀል ተጠርጥረው ክስ በመሠረተባቸው በእነ ዳንኤል ግዛቸው በላይ የክስ መዝገብ ከተካተቱት ተጠርጣሪዎች ውስጥ፣ ቄስ…
-የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማስተጓጐል ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተጠቁሟል በታምሩ ጽጌ በኤርትራ መንግሥት ድጋፍ ኤርትራ ውስጥ የተለያዩ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሥልጠናዎችን በመውሰድ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም በማቀድና በመዘጋጀት፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ለመገንጠል የሽብርተኝነት ድርጊት ፈጽመዋል በሚል በተጠረጠሩ አሥር የክልሉ ነዋሪዎች ላይ ታኅሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡ በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ…
በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በተመሠረተባቸው ክስ ጥፋተኛ የተባሉት፣ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) አመራሮች፣ አቶ አንዱዓለም አራጌና አቶ ናትናኤል መኰንን፣ እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ) አመራር፣ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደርጐ፣ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀናባቸው፡፡  ሰበር ሰሚ…
በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረውና ክስ ተመሥርቶባቸው በክርክር ላይ ከሚገኙት የቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ከምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ገብረዋሀድ ወልደጊዮርጊስ ጋር በመመሳጠር የሙስናውን ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት ነጋዴ በነፃ ተሰናበቱ፡፡ በነፃ የተሰናበቱት ነጋዴ አቶ ማሞ ኪሮስ ይባላሉ፡፡ አቶ መላኩ ፈንታና አቶ ገብረዋሀድ በተጠረጠሩበት ወንጀል…
የሲቪል ማኅበራትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ኤጀንሲ የሚቆጣጠራቸው ድርጅቶች፣ በአስተዳደራዊ ወጪዎች ሥር የነበሩ የተወሰኑ አገልግሎቶች የተወሰኑ በፕሮግራም በጀት እንዲካተቱ በማድረግ የ30/70 መመርያን አሻሻለ፡፡ ኤጀንሲው ይህንን ያደረገው የ30/70 መመርያ የተወሰነውን ክፍል በማሻሻል ሲሆን፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በኤጀንሲው መመርያ ማሻሻያ ሙሉ ለሙሉ ባይረኩም፣ በጎ ጅማሬ ብለውታል፡፡ ቀደም ሲል ኤጀንሲው በ30/70 መመርያ ግብረ ሰናይ…
የኢትዮጵያና የሱዳን መንግሥታት እ.ኤ.አ. በ2013 ወንጀልን በጋራ ለመመርመር የፈረሙትን ስምምነት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት አፀደቀው፡፡  ስምምነቱን የመረመረው የምክር ቤቱ የሕግ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለፓርላማው ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ስምምነቱ ላይ ያካሄደው ማስተካከያ አንድ ብቻ ሲሆን፣ ይህም ስምምነቱ የተፈረመበት ቀን ተሳስቶ የተጻፈ በመሆኑ ይስተካከል የሚል ነው፡፡  ባቀረበውም የውሳኔ…
በቅርቡ በቡድን ተደፍራ ህይወቷ ያለፈው የሃና ላላንጎ የምርመራ መዝገብ ባለመጠናቀቁ ፖሊስ ምርመራውን በ14 ቀን ውስጥ እንዲያጠናቅቅ የቂርቆስ የመጀምሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ የወንጀል ችሎት ትእዛዝ አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ ትእዛዙን ያስተላለፈው ዛሬ በዋለው ችሎት ፖሊስ ምርመራውን ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ በመጠየቁ ነው። የዛሬው ቀጠሮም በዝግ ችሎት ነው የታየው። የቂርቆስ ምድብ ችሎት የመጀምሪያ ፍርድ ቤት ለፋና…