የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6 አዋጆችንና 16 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመትን አፀደቀ

Jul 27 2016

ከዕረፍት ላይ በአስቸኳይ የተጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6 አዋጆችንና 16 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመትን አፅድቆ ተበተነ፡፡

ምክር ቤቱ ሰኔ 30 ቀን 2008 .. የሥራ ዘመኑን ጨርሶ የተበተነ ቢሆንም አፈጉባዔ አባዱላ ገመዳ ከሳምንት በፊት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ባስነገሩት ማስታወቂያ የምክር ቤቱ አባላት ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2008 .. በአስቸኳይ እንዲሰበሰብ ጥሪ አድርገው ነበር፡፡

በዚሁ መሠረት የተሰበሰበው ምክር ቤቱ የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅን፣ የታክስ አስተዳደር አዋጅን፣ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ረቂቅ አዋጅን፣ የጂኦተርማል ሀብት ልማት ረቂቅ አዋጅን፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅን ያፀደቀ ሲሆን፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት 16 ዳኞች ሹመትንም አፅድቋል፡፡

የገቢ ግብር አዋጁ ከሐምሌ 1 ቀን 2008 .. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን የተወሰነ በመሆኑ፣ የተቀጣሪዎች የሐምሌ ወር ደመወዝ ላይ ማሻሻያው መታየት ይኖርበታል፡፡ የንግድ ምዝገባ አዋጁ የፍራንቻይዝ ንግድን የሚፈቅድ ሲሆን ብቸኛ አስመጪነትን ይከለክላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲሾሙ ያቀረቧቸው ዳኞች ሹመት ፀድቋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡትና በምክር ቤቱ ሹመታቸው ከፀደቀላቸው 16 ዳኞች መካከል ሰባቱ ሴቶች ናቸው፡፡

Read 49793 times Last modified on Jul 27 2016
Abyssinia Law | Making Law Accessible!

Abyssinia Law is  a legal resource portal providing open access to primary and secondary legal materials for Ethiopia, such as laws, court decisions, articles, contact guidance and Lawyers Directory - with texts supplemented by online videos, a discussion forum and user blog. The service gives free access to Federal and State consolidated laws of Ethiopia (with status information whether the law is amended, repealed or effective)