የአቶ ሀብታሙ አያሌው ከሀገር የመውጣት ጥያቄ በፍ/ቤት ተቀባይነት አላገኘም

Addisadmass Jul 03 2016

አምነስቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች እግዱ እንዲነሳ መንግስትን ጠይቀዋል

በጠበቃቸው አማካይነት ትናንት ለጠቅላይ /ቤት ያመለከቱት የቀድሞው የአንድነት አመራር አባል አቶ ሀብታሙ አያሌው፤በቂ ምክንያት አላቀረቡምበሚል /ቤቱ ጥያቄያቸውን አልተቀበለም፡፡ 
/ቤቱ ትናንት ከሰዓት በኋላ የቀረበለትን ጥያቄ ከተመለከተ በኋላዛሬውኑ እግዱን ለማንሳት የቀረበው ምክንያት በቂ አይደለም፤ ታማሚው ህክምናቸውን ሀገር ውስጥ እንደማያገኙና ህይወታቸው አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ከሆስፒታሎች ማስረጃ ከቀረበ ወዲያውኑ እግዱ እንዲነሳ ይደረጋልየሚል ምላሽ እንደሰጣቸው የአቶ ሀብታሙ ጠበቃ አቶ አመሃ መኮንን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ 
በሽብር ክስ ይግባኝ የተጠየቀባቸው ጉዳይ በመጪው ማክሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2008 . በቀጠሮ መሰረት የሚታይ ሲሆን /ቤት የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥና ምናልባት የአቶ ሀብታሙ ጉዳይ እልባት ሊያገኝ እንደሚችል ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

የሃብታሙን የህክምና ጉዳይ የሚከታተሉት የቅርብ ወዳጃቸው አቶ ዳንኤል ሺበሺ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፤ አቶ ሀብታሙ ስር በሰደደ ከፍተኛ የኪንታሮት ህመም እየተሰቃዩ ሲሆን በሀገር ውስጥ እስካሁን 4 ሆስፒታሎች ለመታከም ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራ ባለመሳካቱ የተሻለ ህክምና ማግኘት አለባቸው በሚል የቤተሰብ ውሳኔ ወደ ውጭ ሄደው እንዲታከሙ መፈለጉን አስረድተዋል፡፡ 
ያጋጠማቸው ህመም የመጨረሻው ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑን ከህክምና ባለሙያዎች መረዳታቸውን የጠቀሱት አቶ ዳንኤል፤ ቀዶ ጥገናውን በሀገር ውስጥ ለማከናወን አስቸጋሪ መሆኑ እንደተገለፀላቸውና ውጭ ሀገር ሄደው ጥንቃቄ የተሞላበት ዘመናዊ ህክምና ማግኘት ቢችሉ የተሻለ ነው እንደተባሉ ገልፀዋል፡፡ 

አቶ ሀብታሙ ቀደም ሲል በዘውዲቱ ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ እንደነበርና ለውጥ ባለማሳየታቸውም ወደ ዋሽንግተን ሆስፒታል መሄዳቸውን፣ እዚያም ህክምና ስላላገኙ ወደ ቤተዛታ ሆስፒታል ማምራታቸውን የጠቆሙት አቶ ዳንኤል፤ ቤተዛታ ሆስፒታል በራሱ አምቡላንስ አሁን ወዳሉበት ካዲስኮ ሆስፒታል እንዳዘዋወራቸው አስረድተዋል፡፡ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ እስከ ትናንት ማምሻ ድረስ በካዲስኮ ሆስፒታል የህመም ማስታገሻዎችን ብቻ እየወሰዱ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል፡፡ 
አቶ ሀብታሙ አያሌው ህመሙ ተባብሶባቸው ሆስፒታል መግባታቸው ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በማህበራዊ ድረ ገፆች ወደ ውጭ ሀገር ሄደው እንዲታከሙ መንግስትን የሚጠይቁ መልዕክቶች እየተሰራጩ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ለመንግስት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው አለማቀፉ የመብት ተሟጋች ተቋምም የፍ/ቤት እግዱ ተነስቶ አቶ ሀብታሙ የፈለጉትን ህክምና እንዲያገኙ ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል፡፡ 

 

ጉዳዩን አስመልክቶ ሰማያዊ ፓርቲና የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በፃፉት ደብዳቤ፤ አቶ ሀብታሙ ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመጠቆም በታማሚው ላይ ከሀገር እንዳይወጡ የተጣለው እግድ እንዲነሳ ጠይቀዋል፡፡ እግዱ ባይነሳና አቶ ሀብታሙ የፈለጉትን ህክምና ሳያገኙ ለሚደርሰው አደጋ ሁሉ መንግስት ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ፓርቲዎቹ አሳስበዋል፡፡ 

Read 44881 times Last modified on Jul 04 2016