የኬንያ ፓርላማ አንድ ወንድ የሚስቱን ፍቃድ ሳይጠይቅ ተጨማሪ ሚስቶችን ማግባት ይችላል የሚል ህግ አጸደቀ
የህጉን መጽደቅ የተቃወሙ ሴት የፓርላማ አባላት የጉባዔውን አዳራሽ ለቅቀው ወጥተዋል፡፡ ህጉ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሀገሪቱን የትዳር ህግ ለማሻሻል ታስቦ የተዘጋጀና በባህላዊ መንገድ በስፋት በኬንያ የሚካሄዱ ባህላዊ ልማዶችን በህግ ማዕቀፉ ውስጥ ለማካተት የተደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ረቂቅ ህጉ “ባል ተጨማሪ ሴት ለማግባት የሚስት ፈቃድ ሊኖር ይገባል” ይል እንደነበረና የፓርላማው አባላት ባደረጉት ክርክር ‘የሚስት ፈቃድ መኖር አለበት’ የሚለው ሐረግ እንዲነሳ መደረጉን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
ህጉ የሀገሪቱ ህግ ሆኖ ይጸድቅ ዘንድ በፕሬዝዳንቱ መጽደቅ እንዳለበት ታውቋል፡፡