የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ድርጅት (Law Firm)

Aug 19 2014

በ1992 ዓ.ም ወጥቶ በሥራ ላይ ያለው የፌዴራል ፍርድ ቤት ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 199/1992 ማንኛውም ሰው የጥብቅና ፈቃድ ሳይኖረው የጥብቅና አገልግሎት መስጥ እንደማይችል በመደንገግ ፈቃድ እንዴት እንደሚገኝ፣ ፈቃድ ለማግኘት መሟላት ስላለባቸው መስፈርቶች፣ የፈቃድ ዓይነቶች፣ ፈቃድ ስለሚሰጥበት አኳኋን፣ ፈቃድ ስለማደስ፣ ስለመመለስ፣ ስለመሰረዝ እና ከዚሁ ጋር የተገናኙ ሌሎች ዝርዝር ነገሮችን አካትቶ ይዟል፡፡

በዚሁ አዋጅ የፌዴራል የጥብቅና አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ያገኙ ጠበቆች ሁለት ወይም ከሁለት በላይ በመሆን የንግድ ማኅበር ባልሆነና ኃላፊነቱ ባልተወሰነ ማኅበር የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ድርጅት ማቋቋም እንደሚችሉና ከፍትሕ ሚኒስቴር ፈቃድ እንደሚያገኙ በአንቀጽ 18 ሥር በመደንገግ ስለጥብቅና ሙያ አገልግሎት ድርጅት ፈቃድ አሰጣጥ እና ከዚሁ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች አዋጁን ተከትሎ በሚወጣ መመሪያ እንደሚወሰን አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ 4 ይገልፃል፡፡

ነገር ግን የዚህ አዋጅ ድንጋጌ እስካሁን ድረስ ተፈጻሚነት ያላገኘ ስለሆነ ወይም የጥብቅና አገልግሎት ድርጅትን የሚመለከት መመሪያ ስላልወጣ ጠበቆች ተደራጅተው አገልግሎቱን ሊሰጡ አልቻሉም፡፡ ከቁጥጥርና አስተዳደር አንፃርም ሲታይ የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ድርጅት ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ሥራን በአግባቡ ለማከናውንም አልተቻለም፡፡

በመሆኑም የአዋጁ አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ 4 ድንጋጌ እስካሁን ሥራ ላይ ያልዋለ በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተለይ ፍትሕ ሚኒስቴርና የጠበቆች ማኅበር በመተጋገዝ የጥብቅና አገልግሎት ድርጅትን የሚመለከት ሕግ እንዲወጣ ቢደረግ የጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥን ካለበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ እንዲሁም የጠበቆች ተደራጅቶ የመሥራት ፍላጎ ለማሟላት የሚረዳ ይሆናል፡፡ 

Read 12947 times Last modified on May 22 2015
Abyssinia Law | Making Law Accessible!

Abyssinia Law is  a legal resource portal providing open access to primary and secondary legal materials for Ethiopia, such as laws, court decisions, articles, contact guidance and Lawyers Directory - with texts supplemented by online videos, a discussion forum and user blog. The service gives free access to Federal and State consolidated laws of Ethiopia (with status information whether the law is amended, repealed or effective)