Latest blog posts

አቢሲኒያ ሎው የሰበር ውሳኔዎችን ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ በመተርጎም (Case Summary) ውሳኔዎቹን ለተጠቃሚዎቹ ለማድረስ የመጨረሻ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 80 ሥር የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት የማየት ስልጣን እንደሚኖረው በግልጽ ይደነግጋል፡፡ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዳዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት የማየት ስልጣን ይኖረዋል የሚል ተመሳሳይ ድንጋጌ በዚህ አንቀጽ ሥር ይገኛል፡፡

አዋጅ ቁጥር 454/1997

  1. ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የሚሰጠው የሕግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ በሚገኝ የፌዴራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት ላይ አስገዳኝነት ይኖረዋል፤
  2. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የተሰጠባቸውን ውሳኔዎች በየደረጃው ላሉ ፍ/ቤቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካል አሳትሞ ያሰራጫል፡፡ 

የሚሉ ድንጋጌዎችን ይዟል፡፡

በእነዚህ ድንጋጌዎች መሠረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት የተለያየ አስገዳጅ ውሳኔዎችን ሲሰጥና ውሳኔዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል፡፡ ዋና ዓለማውም በፌዴራልና በክልል የሚገኙ ፍርድ ቤቶች በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያየ ውሳኔ እንዳይሰጡ እና ወጥ የሆነ የሕግ አተረጓጎም ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል እንደሆነ ከተለያዩ ጽሑፎች ለመረዳት ይቻላል፡፡

ይህንን ጽሑፍ እስከምንጽፍበት ጊዜ ድረስ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተለያዩ የሕግ ክፍሎች አስገዳጅ ውሳኔዎችን የያዙ 19 ቅጾችን በአማርኛ በማሳተም በድረገጽ እና በመጽሐፍ መልኩ ለተጠቃሚዎች አሰራጭቷል፡፡

በዚህ ረገድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ምስጋና ይገባዋል፡፡ እኛም ለዚህ ሥርዓት መጠናከር የሰበር ሰሚው የሰጣቸውን አስገዳጅ ውሳኔዎች ወደእንግሊዘኛ ቋንቋ በመተርጎም (Case Summary) ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ የመጨረሻ ዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡

ይህንን ማድረግ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት፡-

01የሰበር ውሳኔዎችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን እና ተማሪዎች በቀላሉ እንዲያገኟቸውና የመማር ማስተማር ሂደቱን ለመደገፍ፤

02በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ አማርኛ ቋንቋን ለመረዳት የሚቸገሩ የሕግ ባለሙያዎች የሰበር ውሳኔውን በቀላሉ እንዲረዱ ለማስቻል፤

03የኢትዮጵያ ሕጎችን ከሰበር ውሳኔዎች ጋር አቀናጅተው መረዳት ለሚፈልጉ የውጪ ሀገር ዜጎች ሕጉን ከውሳኔው ጋር በቀላሉ እንዲረዱ ለማስቻል፤ እና

04የተለያዩ ጥናቶች የሚያደርጉ አጥኚዎችና የሕግ ተመራማሪዎች የሰበር ውሳኔዎችን ለመተርጎምና ለማስተርጎም የሚያወጡትን ጊዜና ወጪ ለመቀነስ በማሰብ ነው፡፡

ይህ ሥራ የሰበር ውሳኔዎች ተደራሽነትን ከመጨመሩም በተጨማሪ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ የበኩሉን ድርሻ ይጫዋታል ብለን እናምናለን፡፡

በቅርብ ይጠብቁን! 

ስለዚህ ሥራ ያለዎትን አስተያየት ቢነግሩን እጅግ ደስ ይለናል!


Editors Pick

Criminal Law Blog
Seenaa adabbii yakka yoo ilaalle, adabbiin balleessaa adda addaa hordofuun kennamaa ture baay’ee suukaneessaa fi kaayyoo sirna haqaa yakka hammayyaa irraa kan fagaate ture. Adabbiin haala akkasiin ken...
33784 hits
Criminal Law Blog
የተከበራችሁ አንባቢዎች ለዛሬው ርዕሰ አንቀፅ መነሻ የሆነኝ የውንብድና ወንጀልን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች በአግባቡ ባለመረዳት ወይም በተለያዩ መልኩ በመተርጎም የሚፈፀሙ የክስ አመሰራረት ልዩነቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ያለውን አሰራር እና አንቀፁን እኔ በምረዳው መልኩ በማቅረብ ለአንባቢዎቼ እንደሚከተለው ለውይይት እና አ...
9767 hits
Arbitration Blog
  Introduction   Let alone in countries with less developed arbitration industries such as Ethiopia, pathological arbitration clauses are common in countries like the Switzerland, UK, Singapore, and F...
2198 hits
Commercial Law Blog
   {autotoc}     Abstract Ethiopia introduced a new Commercial Code in March 2021, replacing the Commercial Code of the Empire of Ethiopia Proclamation No. 166/1960 (the repealed Commercial Code) that...
6796 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...