Latest blog posts

የገጠማቸውን ሕመም ለማወቅ ባደረጉት ምርመራ በግራ ኩላሊታቸው ላይ ጠጠር መኖሩ የተነገራቸው 37 ዓመት ሴት፣ ጠጠሩን በቀዶ ሕክምና ለማስወገድ በቤተል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የተኙ ቢሆንም፣ ሕክምናው ተደርጎላቸው በሰላም ከተጠናቀቀ ከአራት ዓመታት በኋላ ባደረጉት የአልትራ ሳውንድ ምርመራ የግራ ኩላሊታቸው ሙሉ በሙሉ ተነጥሎ መውጣቱን በማወቃቸው የፍትሐ ብሔር ክስ መሠረቱ፡፡

ያለፈቃዳቸውና ያለዕውቀታቸው የግራ ኩላሊታቸው መውጣቱን ካረጋገጡ በኋላ ክስ የመሠረቱት 37 ዓመቷ ወጣት /ሪት ወርቅነሽ ደበላ የሚባሉ ግለሰብ ሲሆኑ፣ ክሱን የመሠረቱት በቤተል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታልና ቀዶ ጥገናውን አድርገዋል በተባሉት እንግሊዛዊው ሐኪም ፕሮፌሰር ጎርደን ዊሊያም ላይ መሆኑን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጥተኛ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ያቀረቡት የክስ ቻርጅ ይገልጻል፡፡ ተጎጂዋ በጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ጓንጉል አማካይነት ያቀረቡት የፍትሐ ብሔር ክስ እንደሚያብራራው፣ በሐምሌ ወር 2004 .. በሚሠሩበት ተቋም ክሊኒክ ተመርምረው፣ በሪፈራል ወደ ቤተል ቲቺንግ ጠቅላላ ሆስፒታል ተልከዋል፡፡ በሆስፒታሉ የላብራቶሪና የአልትራሳውንድ ምርመራ ታዞላቸው ውጤቱ በሌላ አካላቸው ላይ ውኃ መኖሩንና በግራ ኩላሊታቸው ላይ ጠጠር እንደሚታይ ተገልጾላቸዋል፡፡ ጠጠሩን በቀዶ ሕክምና ካስወጡ በኦቫሪ ላይ የታየው ውኃ እንደሚጠፋ ተነግሯቸው ወደ ፕሮፌሰሩ መላካቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ ፕሮፌሰሩ ድጋሚ ምርመራ አድርገው ጠጠር መኖሩን ካረጋገጡ በኋላ፣ ግለሰቧ አልጋ እንዲይዙ አድርገው ጠጠሩን ለማስወገድ ሌሎች አማራጮች እንዳሉ ሳይገለጹላቸው፣ የኩላሊት ጠጠሩን በቀዶ ሕክምና አውጥተው ለከሳሿም እንዳሳዩዋቸው ክሱ ይገልጻል፡፡

የስድስት ሳምንታት እረፍትና የተኝቶ ታካሚዎች የምስክር ወረቀት ፈርመው ሰጥዋቸው፣ ታካሚዋ ሐምሌ 24 ቀን 2004 .. ከሆስፒታሉ እንደወጡም ያክላል፡፡ የሕክምና ተቋሙ ከመሥሪያ ቤታቸው ጋር ባለው የሕክምና ስምምነት መሠረት ከሳሿ በሆስፒታሉ ለተለያዩ ሕክምናዎች ክትትል ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ ለሌሎች ሕመሞች የሚታዘዙላቸው መድኃኒቶች አልስማማ እንዳላቸው ክሱ ይገልጻል፡፡ በሌላ አካል ላይ ታይቷል የተባለው ውኃ መጥፋት አለመጥፋቱን ለማረጋገጥ ከሦስት ዓመታት ቆይታ በኋላ በጥቅምት ወር 2008 .. አልትራሳውንድ ሲነሱ፣ የግራ ኩላሊታቸው እንደማይታይ ባለሙያዎች እንደነገሯቸው ክሱ ይጠቁማል፡፡ ግለሰቧ በባለሙያ የተነገራቸውን ባለማመንና በመደናገጥ ክትትል ወደ ሚያደርጉላቸው የቤተል ሆስፒታል ሠራተኛ ዶክተር ሄደው የተነገራቸውን ሲያስረዷቸው፣ ቀደም ብለው የቀዶ ሕክምና ባደረጉበት ወቅት የነበራቸውን የሕክምና ማስረጃ እንዲያገኙ ነግረዋቸው፣ በብዙ ውጣ ውረድ ማስረጃቸውን ማግኘታቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ ኩላሊታቸው መኖር አለመኖሩን በድጋሚ በቤተዛታ ሆስፒታል ባደረጉት ምርመራ፣ የግራ ኩላሊታቸው እንደማይታይ ማረጋገጣቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ ነገር ግን ቀደም ብለው በቤተል ቲቺንግ ጠቅላላ ሆስፒታል ባደረጉት ምርመራ፣ ሁለቱም ኩላሊታቸው እንደነበር በሰነድ መረጋገጡን ክሱ ጠቁሞ፣ በሆስፒታል ቀዶ ሕክምና ካደረጉ በኋላ ኩላሊታቸው እንዴት ላይታይ እንዳልቻለ ተጎጂ ማብራርያ ጠይቀው፣ ፕሮፌሰሩ ማብራርያ መስጠታቸውንም ክሱ አካቷል፡፡ ፕሮፌሰሩ በሰጡት ማብራርያ ግለሰቧ የቀኝ ኩላሊታቸው ጤነኛ እንደነበርና የግራ ኩላሊታቸው ግን ጠጠር እንደነበረበት መናገራቸው በክሱ ተገልጿል፡፡ እንዲሁም የግራ ኩላሊታቸው መኮማተሩንና ሌሎችም ምርመራ አክለው ከቀዶ ሕክምና በፊት የታካሚዋ ኩላሊት መወገድ እንዳለበት በመወሰን ማስወገዳቸውን፣ በጽሑፍ ማብራርያ መስጠታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡

ፕሮፌሰሩ የራሳቸውን ውሳኔ ለታካሚዋ የማሳወቅና የማስፈረም ግዴታ ቢኖርባቸውም አለማድረጋቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ ፕሮፌሰሩ ለታካሚዋ በሰጡት የሕክምና ሰርተፊኬት ላይ የጠቀሱት የኩላሊት ጠጠር ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን እንጂ፣ ስለኩላሊቱ መወገድ የጠቀሱት ነገር እንደሌለም ያብራራል፡፡ ፕሮፌሰሩ ማብራርያ ሲሰጡ ከግራ ኩላሊታቸው ላይ ጠጠር እንዳወጡ የገለጹ ቢሆንም፣ ተኝተው ታክመው ሲወጡ በሰጡት ሰርተፍኬት ላይ ግን ከቀኝ ኩላሊታቸው ላይ ጠጠሩ እንደወጣ መግለጻቸውንና ይህም የተለያየ መረጃ መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡ ግለሰቧ በመጀመርያ ሕክምና ሲያደርጉ ምንም ዓይነት የኩላሊት ሕምም እንደሌለባቸውና ጤነኛ መሆናቸውን የሚያስረዳው ክሱ፣ ቀዶ ሕክምና ተደርጎላቸው ከሦስት ዓመታት በላይ ሌላ ሕክምና ሲከታተሉ ምንም የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረና ፕሮፌሰሩ በራሳቸው ውሳኔ አካላቸውን ከሚያሳጧቸው ሊያማክሯቸው፣ ሊስማሙና ሊፈርሙ ይገባ እንደነበር ያክላል፡፡ በአንድ ኩላሊት ሲኖሩ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸው እንደበርም ሊገለጽላቸውና ሙያዊ ምክር ሊደረግላቸው ይገባ እንደነበርም ግለሰቧ በክሱ ገልጸዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ በእንግሊዝ በመምህርነትና በሆስፒታል አስተዳዳሪነት መሥራታቸውን፣ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ፕሮግራሞችን በተለያዩየ የአፍሪካ፣ አውሮፓና ሌሎች አገሮች የጀመሩት እሳቸው መሆናቸው በክሱ ተዘርዝሯል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የእንግሊዝ መንግሥት በሚያስተዳድረው ብሪትሽ ካውንስል አማካይነት መሆኑን ጠቁመው፣ ከፍ ያለ የሥራ ልምድና ዕውቀት ያላቸው ከመሆኑ አንፃር የተጎጂን ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባቸው ይጠፋቸዋል የሚል ግምት እንደሌላቸው በክሱ ገልጸዋል፡፡ የግራ ኩላሊታቸውን ያወጡትም ሆን ብለው ነው የሚል ግምት እንዳላቸውም አክለዋል፡፡ በመሆኑም ፕሮፌሰሩ የተጎጂን የግራ ኩላሊት ያለፈቃዳቸው በማውጣታቸው ላደረሱት ጉዳት ኃላፊነት እንዳለባቸው በክሱ ገልጸዋል፡፡ ተጎጂዋ የኩላሊታቸው መውጣትን ካወቁ ጀምሮ ከፍተኛ የሥነ ልቦና ችግር እንዳጋጠማቸውም በክሱ አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ቀጥተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት 4,590,000 ብር ተከሳሾች የጉዳት ካሳ እንዲከፍሏቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ግለሰቡ የዳኝነት መክፈል እንደማይችሉ ለፍርድ ቤቱ በማመልከት በደሃ ደንብ እንዲታይላቸው ጠይቀዋል፡፡ ክሱ መታየት ያለበት በደሃ ደንብ ነው ወይስ አይደለም በሚለው ላይ ለመወሰን ቤተል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል መልሱን በጽሑፍ እንዲያቀርብ ለሐምሌ 13 ቀን 2008 .. ፍርድ ቤቱ መጥሪያ ልኮለታል፡፡


Editors Pick

Criminal Law Blog
በልደታ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሺሻ በማስጨስ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ግለሰቦች እና የማስጨሻ ቤቶች መኖራቸውን የተረዳው የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በሥሩ የሚገኙ የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች የሺሻ ማስጨሻ ዕቃዎችን እና ሺሻ ሲያስጨሱ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡ ሺሻን ሲያስጨሱ የነበሩ ግ...
10003 hits
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
  ጥያቄው? በዚህ ጽሁፍ መመለስ የምፈልገው ጥያቄ ቀላል ይመስላል፤ እንዴት ያለባለቤቱ ሙሉና ነጻ ፈቃድ የተላለፈን ንብረት ማስመለስ፤ የተቋቋመን የመብት ገደብ ማስነሳት ይቻላል የሚለውን ነው፡፡ ቀጥታ ጥያቄውን ወደ መመለሱ ከመሄዴ በፊት፤ ጥያቄው የሚመለከታቸው ሁኔታዎች ምን አይነቶቹን እንደሆነ ግልጽ ላድርግ፡፡ ያለ...
19515 hits
About the Law Blog
የማስረጃ ሕግ የማስረጃን አግባብነት፣ የማስረጃን ተቀባይነት እንዲሁም የማስረጃን ክብደትና ብቃት የሚገዙ ደንቦችና መርሆዎች ጥርቅም ነው፡፡ ማስረጃ ተሟጋቾች በአቤቱታቸው አማካኝነት ፍርድ ቤት የያዘውን ጭብጥ የሚያረጋግጡበት ዘዴ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ማስረጃ ማለት ፍርድ ቤት የያዘውን አከራካሪ ጉዳይ ወይም ጭብጥ በ...
14655 hits
Criminal Law Blog
  ካሳ አልባ የፍትሕ ሥርዓቱ ተጎጂዎች እንዲያው አያድርገውና በወንጀል ተጠርጥረው ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆብዎ አስቸጋሪውን የወንጀል ምርመራ ተቋቁመው ካለፉ በኋላ በዓቃቤ ሕግ ተከሰው የዋስትና መብትዎን ተከልክለው ክራሞትዎ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆነ እንበል፤ በሕግ ጥላ ሥር፡፡ የፍርድ ቤት ቀጠሮዎት በደረሰ ጊዜ እጅዎ በካቴ...
11318 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...