Latest blog posts

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያና በሱዳን መንግሥታት መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የተፈረመውን ስምምነት ሰኔ 23 ቀን 2008 .. በዋለው መደበኛ ጉባዔ አፀደቀው፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ወደ ውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመራው የማፅደቂያ ረቂቅ አዋጅ በሁለቱ አገሮች በኩል ሰላምና መረጋጋት ለማስፈንና በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ሊቃጣ የሚችልን ወንጀል ለመከላከል ይረዳል ተብሏል፡፡ ለዝርዝር ዕይታ የተመራለት የውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ ተስፋዬ ዳባ፣ ስምምነቱ ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይና አገራዊ ደኅንነት ፖሊሲዋ ትኩረት ከሰጠችባቸው ጉዳዮች መካከል ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ፣ ከጎረቤት አገሮች ጋር ተባብሮ ለመሥራትም ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ምክር ቤቱ ስምምነቱ እንዲያፀድቀው የኮሚቴው አባላት በሙሉ ድምፅ መስማማታቸውን ጨምረው አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአገሮችና ለሕዝቦች ደኅንነት ሥጋት እየሆኑ ከመጡ ጉዳዮች ውስጥ የተደራጀ ወንጀል ድርጊቶች፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገወጥ ንግድ፣ ሽብርተኝነት የመሳሰሉት ተጠቃሽ መሆናቸውን  በመጥቀስ የእነዚህን ወንጀሎች ፈጻሚዎች ከተጠያቂነት እንዳያመልጡ ያደርጋል ሲሉም አብራርተዋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ አገሮች በብሔራዊ ሕጎቻቸው ከአንድ ዓመት ጀምሮ ሊያስቀጣ በሚችል ወንጀል ክስ የቀረበበት ወይም የተቀጣ ግለሰብን ለጠያቂው አገር አሳልፎ ለመስጠት ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ ከላይ የተገለጸው እንዳለ ሆኖ የታክስ፣ የጉምሩክና የውጭ ምንዛሪን በተመለከቱ የወንጀል ድርጊቶች የተጠረጠረ ግለሰብ ተላልፎ እንዲሰጥ በሚጠየቅበት ጊዜ ጥያቄው በቀረበበት ወገን ሕግ መሠረት መሰል የግብር ወይም የቀረጥ ግዴታ አለመኖሩ የቀረበውን አሳልፎ የመሰጠት ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ እንደማይቻል በስምምነቱ ተገልጿል፡፡

የኮሚቴውን የውሳኔ ሐሳብ ያደመጠው ምክር ቤትም ያለ ተጨማሪ ጥያቄና ማብራሪያ በቀጥታ በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አፅድቆታል፡፡

በተያያዘ ዜናም ቋሚ ኮሚቴው እንዲሁ ተመርቶለት የነበረውን በኢትዮጵያና በቱርክ በወታደራዊ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተፈረመውን ስምምነት አቅርቦ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሊቀመንበር በቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ በሁለቱ አገሮች የመከላከያ ሚኒስትሮች 1998 .. የተፈረመው ስምምነት አገሮቹ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓላማዎችና መርሆዎች ማዕቀፍ ውስጥ በመሆን ዓለም አቀፍ ግዴታቸውን ለመወጣት እንደሚያስችላቸው አቶ ተስፋዬ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡

እንዲሁም አገሮቹ በወታደራዊ ሥልጠናና ትምህርት፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪ፣ ለአየር ኃይል፣ በምድር ጦርና በሎጂስቲክ ዙሪያ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ካስረዱ በኋላ ‹‹ቱርክ በምድር፣ በአየርና በባህር የተደራጀ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል ካላቸው አገሮች ውስጥ የምትመደብ በመሆኗ፣ የትብብር ስምምነቱ ለአገራችን የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ጠቀሜታው የጎላ ነው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

ምክር ቤቱም የውሳኔ ሐሳቡን ካደመጠ በኋላ ስምምነቱን በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል፡፡


Editors Pick

International Law Blog
  1.    ስለዓለም አቀፍ ሕግ በአጭሩ ዓለም አቀፍ ሕግ በሉዓላዊ አገሮች መካከል ያለን ግንኙነት ወይም በአገሮችና እንደተባበሩት መንግሥታት ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል ያለን ግንኙነት የሚገዛ የሁሉ አቀፍ ደንቦች እና መርሆዎች ሥርዓት ነው። በሌላ አነጋገር «International law is the univer...
15447 hits
Others
  መምህሩ ወጣቱን ተማሪ ጠየቀው፤ “በየዓመቱ ይህን ፎቶ ታሳየኛለህ፣ ሁሌም አስተያየቴ አንድ ነው፣ አይረባም። ይህን ያህል ፎቶውን ለምን ወደድከው?” ወጣቱ መለሰ፤ “ምክንያቱማ፤ ይህን የተፈጥሮ ገጽታ ለመፎተት በጣም ትልቅ ተራራ በእንፉቅቅ መውጣት ስለነበረብኝ ነው”።  የመታደል ውጤት/ተጽእኖ የተለያዩ ጥናቶችና ግን...
11302 hits
About the Law Blog
  መግቢያ ለዚህ ጽሑፍ ምክንያት የሆነኝ ከታች እንደተገለጸው አንድ ተከራካሪ ወገን በፍ/ቤት ክርክር በሚያቀርብበት ወቅት ሊያጋጥሙት ከሚችሉ ጉዳዮች አንዱ ከችሎት ይነሳልኝ (ችሎት ይቀየርልኝ) በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ሲሆን ዳኞች ከችሎት የሚነሱባቸውን ምክንያቶችና ባለጉዳዮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው በአዋጅ ቁጥር 2...
6805 hits
About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
4221 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...