የቀድሞው የአክሰስ ሪል ስቴት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የ500 ሺህ ብር ዋስትና ተፈቀደላቸው።
መርማሪ ፖሊስ ከተጠርጣሪና ከምስክሮች ቃል መቀበልን ጨምሮ የሰነድ ማስረጃዎችን መሰብሰብ፣ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ማስረጃዎችን እንዲልኩ ማድረግ የሚሉትና መሰል ስራዎችን ሰርቺያለሁ በማለት ለቀሪ ስራዎች የ14 ቀን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።
የአቶ ኤርሚያስ አመልጋ ጠበቆችም ፖሊስ የተሰጠው ጊዜ በቂ በመሆኑ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሊሰጠው አይገባም ሲል ሞግቷል።
ይህ ቢሆን እንኳን የዋስትና መብት ይጠበቅልን ሲሉ አመልክተዋል።
መርማሪ ፖሊስ ግን አቶ አቶ ኤርሚያስ የተጠረጠሩበት ወንጀል ውስብስብና ሌሎች ተጠርጣሪዎችም በመኖራቸው ዋስትና ሊሰጥ አይገባም ብሏል።
የግራ ቀኙን ክርክር ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ባለፈው የመጨረሻ የሚል ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ተከትሎም መርማሪ ፖሊስ የተሰጠው ጊዜ በቂ ነው በማለት ለተጠርጣሪው የ500 ሺህ ብር ዋስትና ፈቅዷል።
ውሳኔውን ተከትሎም ፖሊስ ይግባኝ ሊጠይቅ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።