የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከዚህ በታች በተመለከተው ርዕስ ላይ የግማሽ ቀን የልምድ ልውውጥ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም የማኅበሩ አባላት፣ ተባባሪ አባላት እና የሕግ ባለሙያዎች በመድረኩ ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል፡፡
ርዕስ፡- “የሕግ ነክ ጽሑፎች መጣጥፍ፣ መጽሐፍ፣ ጡመራ ልምድ ልውውጥ መድረክ”
ጽሑፍ አቅራቢዎች፡-
1. አቶ አበበ አሳመረ /የማኅበሩ ም/ፕሬዚዳንት፣ የሕግ አማካሪና ጠበቃ/
2. አቶ ፋሲል ታደሰ /የሕግ አማካሪና ጠበቃ እንዲሁም በአ.አ.ዩ. የሕግና ሥነ-መንግሥት ኮሌጅ የከፊል ጊዜ መምህር/
3. ወ/ሮ ማርታ በለጠ /በአ.አ.ዩ. የሕግና የሀገር አስተዳደር ኮሌጅ ተባባሪ ፕሮፌሰር/
4. አቶ ሚካኤል ተሾመ /የሕግ አማካሪ፣ ጠበቃና የአቢሲኒያ ሎው ጦማሪ/
አወያይ፡- አቶ ታምራት ኪዳነማርያም /የማኅበሩ ፕሬዚዳንት፣ የሕግ አማካሪና ጠበቃ/
የስብሰባ ቀን፡- ኅዳር 29 ቀን 2008 ዓ.ም.
የስብሰባ ሰዓት፡- ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30
የስብሰባ ቦታ፡- ዋቢ ሸበሌ ሆቴል
በስብሰባው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ አባላት፣ ተባባሪ አባላት እና የሕግ ባለሙያዎች በስልክ ቁጥር 0115-53-01-22 ወይም በኢሜል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ተመዝገቡ፡፡
የማኅበሩ ጽ/ቤት