የ16 ዓመቷን ታዳጊ ሐና ላላንጎን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽመውባት ለሕይወተ ህልፈት ዳርገዋታል በሚል የተከሰሱ 5 ግለሰቦች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈባቸው፡፡
የፌደራል ዓቃቤ ሕግ አምስቱን ግለሰቦች የአስገድዶ መድፈርና ከባድ የሰው ግድያ ወንጀሎች በሚሉ ሁለት ክሶች ክስ መሥርቶባቸው ጥፋተኛ ማስባሉ ይታወሳል፡፡
በተመሠረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ናቸው ብሎ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የወንጀል ችሎት የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ለዛሬ በቀጠሮ መታለፉም የሚታወስ ነበር፡፡
በዚህም መሠረት ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2007 ዓ.ም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሾቹ ላይ ከ17 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡
በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ተከሳሽ ሳምሶን ስለሺ እና በዛብህ ገብረማሪያም ፍርድ ቤቱ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ሲወስን በሦስተኛ፣ አራተኛ እና አምሰተኛ ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው በ17፣ 20 እና 18 አመት እሥራት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡