Latest blog posts

-ሦስት የፓርቲው አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቆመ

በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በተመለከተ ሕዝቡ ሐዘኑን ለመግለጽና የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለማውገዝ፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በተደረገው ሠልፍ ላይ፣ ብጥብጥ

እንዲፈጠር አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው በታሰሩ ሰባት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና በሁለት ግለሰቦች ላይ ግንቦት 4 እና 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡ 

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የተከሰሱት ‹‹ስብሰባን ወይም ጉባዔን ማወክ ወንጀል›› በሚል ሲሆን፣ ክሱ የተመሠረተው በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ቂርቆስና መናገሻ ምድብ ችሎቶች ነው፡፡ 

በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት ግንቦት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ የተመሠረተባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬና ማስተዋል ፈቃደ ሲሆኑ፣ ቤተልሔም አካለወርቅ የምትባል ግለሰብ በክሱ ተካታለች፡፡ 

በመናገሻ ምድብ ችሎት ግንቦት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ የተመሠረተባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ደግሞ መሳይ ደጉሰው፣ ብሌን መስፍንና ተዋቸው ዳምጤ ናቸው፡፡ ማትያስ መኩሪያ የሚባል ግለሰብም አብሯቸው ተከሷል፡፡ 

በቂርቆስ ምድብ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው ግለሰቦች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ)ን ማለትም በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን፣ እንዲሁም አንቀጽ 490(3)ን ማለትም፣ በቡድን ሆኖ ስብሰባን ወይም ጉባዔን ማወክ የሚለውን ድንጋጌ መተላለፋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ 

በመናገሻ ምድብ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው ግለሰቦችም፣ ከላይ ከተጠቀሱት የወንጀል ሕግጋት በተጨማሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 487(1ሀ)ን ማለትም፣ ‹‹የማነሳሳት ጠባይ ያላቸው የሐሳብ መግለጫዎችን፣ በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታ ወይም ስብሰባ ላይ ሕገወጥ ለሆነ ድርጊት የሚያነሳሳ ወይም የዛቻ ጠባይ ያለው የንግግር መግለጫ ወይም ምስል ያዘጋጀ፣ ያስፋፋና ያሠራጨ ወይም ያሰማ›› የሚለውን መተላለፋቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ 

አንደኛ ተከሳሽ ወይንሸት ሞላ በሕዝብ የተመረጠን መንግሥትን ክብርና ሰብዕናን፣ እንዲሁም ከሕዝብ የተሰጠውን የአመራርነት አደራ የሚያንቋሽሽና የሚያጎድፉ ቃላት እያወጣች በመጮህና በማስተጋባት፣ ሠልፍ ለወጣው ኅብረተሰብ መግለጿን ክሱ ያስረዳል፡፡ 

ተከሳሽ ዳንኤል ተስፋዬ አንደኛ ተከሳሽ የተናገረችውን እየደገመ ‹‹ናና ናና መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ናና›› ማለቱንና ተከሳሽ ኤርሚያስ ፀጋዬ ‹‹ወያኔ አሳረደን ወያኔ አሳረደን›› በማለት እየተቀባበሉና ሕዝቡ እንዲቀበል ሲያደርጉ እንደነበር በክሱ ተጠቁሟል፡፡ በሠልፉ ላይ ጋዜጠኞች ካሜራ ይዘው ሲንቀሳቀሱና ወደ እነሱ ሲቀርቡ ‹‹ሌባ ሌባ›› በማለት ድንጋይ በመወርወርና እነሱ የሚሉትን ሕዝቡ እንዲያስተጋባ ሲያነሳሱ እንደነበርም በክሱ ተብራርቷል፡፡ 

ቤተልሔም አካለወርቅ የተባለች ተጠርጣሪ እጆቿን እያጣመረች ‹‹ታስረናል፣ የታሰሩ ይፈቱ፣ ፍትሕ የለም›› እያለች ስትጮህ፣ ሁሉም ተጠርጣሪዎች እሷን በመቀበልና በእጃቸው ምልክቱን በማሳየት ሕዝቡ እንዲያስተጋባ በማድረግ ሠልፉን ያወኩ መሆኑን ክሱ ይገልጻል፡፡ ሁሉም ተከሳሾች ተመሳሳይ ድርጊቶችን በመፈጸም ‹‹ስብሰባን ወይም ጉባዔን ማወክ ወንጀል›› ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡ 

በቂርቆስ ምድብ ወንጀል ችሎት ግንቦት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ የቀረበባቸው ዋስትና ተከልክለው ለግንቦት 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ተቀጥረው ወደ ማረሚያ ቤት ወርደዋል፡፡ በመናገሻ ምድብ ወንጀል ችሎትም ግንቦት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ የተመሠረተባቸውም ዋስትና ተከልክለው ለግንቦት 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ተቀጥረው ማረሚያ ቤት ወርደዋል፡፡

በሌላ በኩል ሦስት የፓርቲው አባላት መሆናቸው የተጠቆመው ናትናኤል ያለምዘውድ፣ ሜሮን አለማየሁና ደብሬ አሸናፊ ግንቦት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ፣ በፖሊስ ታስረው መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ወጣቶቹ ለምንና በምን ምክንያት በፖሊስ ሊወሰዱ እንደቻሉ ከፖሊስ ለማጣራት በተደረገው ጥረት፣ ፖሊስ ምንም የሚያውቀው እንደሌለ አስታውቋል፡፡

 

Editors Pick

About the Law Blog
  ኢትዮጵያ ውስጥ የዳኝነት ሥልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ብቻ አይደሉም፡፡ ይህን ሥልጣን የተጎናፀፉ ብዙ አካላት አሉ፡፡ ለአብነት ያህል ለመጥቀስ፡- በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ውስጥ የሚገኘው የአስተዳደር ፍርድ ቤት ከሥራ መሰናበት፣ ደመወዝ መቁረጥና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች አስመልክቶ በመንግሥት ሠራተኛውና  በፌ...
6627 hits
Criminal Law Blog
  መግቢያ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የተለያዩ የከፉ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች (Genocide)፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (Crimes against Humanity)፣ የጦር ወንጀሎች (War Crimes) እና የወረራ ወንጀሎች (Crime of aggression)፣ በሰላም ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች (Crime a...
549 hits
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
  ዶ/ር ትዝታ በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩዋን ለመከታተል በችሎት ታድማለች፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በቤቷ ላይ ያለአግባብ ፍርድ ተሰጥቷል ብላ ስላመነች የተማረ ጠበቃ የይግባኝ አቤቱታ ጽፎላት ጉዳይዋን በራሷ ትከታተላለች፡፡ እንደ እርሷ አስተሳሰብ ጉዳይዋን ከእርሷ ይልቅ የሚረዳው የለም በሚል ...
12569 hits
About the Law Blog
  ጸሐፊው በሚከታተለው አንድ የንግድ ችሎት ጉዳይ ጠበቃው የችሎቱን ዳኛ ያማርራል፡፡ የዳኛውን የችሎት አካሄድ እየተቸ በዕለቱ በሰጠው ፍርድ ጠበቃው ለጉዳዩ ጠቃሚ የሆነውን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ የሕግ ትርጉም የችሎቱ ዳኛ በፍርዱ አለማካተቱ፣ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው መሆኑንና ይዘቱንም በፍርዱ ለማን...
7400 hits

Top Blog Posts

Labor and Employment Blog
  ዓለማችን ላይ የፈረንጆቹ 2020 የተወሳሰቡ ችግሮችን ይዞባት መጥቷል፡፡ ከቻይና ውሃን በትንሹ ተነስቶ በወራት ውስጥ ዓለምን ካዳረሰው የኮሮና ቫይረስ የሚስተካከል ችግር ግን ይመጣል ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡ ይህ ቫይረስ በቀጥታ በሰው ልጆች ጤና እና ህይዎት ላይ እያሰከተለ ከሚገኘው ኪሳራ እና ውድመት በሚስተካከ...
Taxation Blog
  በዚህ ጽሑፍ ስለ ግብር ስወራ ምንነት፣ በተለያዩ የግብር ዓይነቶች ሥር የግብር ስወራ ስለሚያቋቋሙ ድርጊቶች፣ ለግብር ስወራ መነሻ ሊሆኑ ስለሚችሉ ምክንያቶች እንዲሁም የመከላከያ መንገዶቹ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ መነሻ የሆነኝ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጉምሩክና ታክስ ወንጀል ችሎት...
About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...