Latest Blog posts
Editors Pick
Latest documents
Education and Training Policy of Ethiopia - Amharic version - 2023 7249 Downloads - policies and strategies | 7.6 MB | |
The Normative Basis for Decision on the Merits in Commercial Arbitration - the Extent of Party Autonomy 197 Downloads - Arbitration Law | 635.59 KB | |
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ማውጫ ቅጽ 01-25 8781 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 10.72 MB | |
ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ እይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ FEATURED 397 Downloads - Criminal Law | 317.19 KB | |
Federal Supreme Court Cassation Decisions - Table of content Volume 1-25 10412 Downloads - Federal Supreme Court Cassation Bench Decisions | 6.57 MB |
- Details
- Category: Legal News - የሕግ ዜናዎች
ፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ በሕገወጥ መንገድ ተወስዶብኛል ያለው ሰነድ ሳይመለስለት ሌላ ሰነድ መጠየቁን ተቃወመ
-በፍርድ ቤቶችና በባለሥልጣኑ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ጻፈ
- ‹‹የተጣለበት ኃላፊነት ለመወጣት እንዲችል የተፈለጉት ሰነዶች መቅረብ አለባቸው›› የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን
ፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተጠረጠረበትን ‹‹ደረሰኝ ሳይቆርጡ ሽያጭ ማከናወን›› ወንጀል በሚመለከት፣ ምርመራ ለማካሄድ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የብርበራ ትዕዛዝ ከፍርድ ቤት ያወጣ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ከሰጠው ትዕዛዝ ውጭ ሕገወጥ በሆነ መንገድ የድርጅቱን በርካታ ሰነዶች ወስዶ እያለ በድጋሚ ለኦዲት አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች እንዲያቀርብ መጠየቁን ተቃወመ፡፡
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ኅዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ከፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ ማውጣቱን የገለጸው ድርጅቱ ፍርድ ቤቱ ከሰጠው ትዕዛዝ ውጭ የሕጉን ድንጋጌ በመጣስ ባደረገው ብርበራ፣ ከ40 በላይ በአቃፊ የተቀመጡ የሰነድ ማስቀመጫዎችን መውሰዱን ጠቁመዋል፡፡ ባለሥልጣኑ የፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሰነዶች መውሰዱን ያስታወሰው ድርጅቱ ለሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎችና ለባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ደብዳቤ ጽፎ መልስ በመጠባበቅ ላይ ባለበት ባሁኑ ጊዜ በአሥር ቀናት ውስጥ ሰነዶችን እንዲያቀርብ መጠየቁ ግራ እንዳጋባው ለባለሥልጣኑ የሕግ ዘርፍ የጻፈው ደብዳቤ ይገልጻል፡፡
ድርጅቱ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርቦ ባለሥልጣኑ የሠራው ሥራ አግባብ አለመሆኑ በመታወቁ ባለሥልጣኑ ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ተሰጥቶት እንደነበር ጠቁሟል፡፡ ነገር ግን ባለሥልጣኑ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ከማክበር ባለፈ የባለሥልጣኑ ኢንቬስቲጌሺን ኦዲት ቡድን አስተባባሪ ‹‹የሒሳብ ሰነዶችና መዛግብቶች ለኦዲት እንድታቀርቡ›› የሚል ደብዳቤ እንዳደረሰው በደብዳቤው ገልጿል፡፡ ድርጅቱ፣ በድጋሚ ለፍርድ ቤቱ ሲያሳውቅ ባለሥልጣኑ ቀርቦ ምላሽ መስጠቱን የገለጸው ድርጅቱ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በስምምነት እንዲፈቱት ማሳሰቢያ በመስጠቱ ውይይት አድርገው ስምምነት ላይ የደረሱ ቢሆንም ባለሥልጣኑ ግን የወሰዳቸውን ሰነዶች አለመመለሱን ገልጿል፡፡ ድርጅቱ በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመና በመሥራት ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቁሞ፣ ሕግ የጣለበትን ግዴታ ሳያጓድል የሚጠይቅና የሚጠቀም ድርጅት በመሆኑ መብቱን በሕግ እንደሚያስከብረው ሁሉ በሕጉና ሥርዓቱ ኦዲት የመደረግ ግዴታ እንዳለበት በደንብ እንደሚገነዘብ አሳውቋል፡፡
ማንኛውም ዓይነት የኦዲት ተግባር የሚመሠረተው በሒሳብ ሰነዶች ላይ መሆኑን የሚጠቁመው ድርጅቱ፣ በባለሥልጣኑ ሠራተኞች ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ በሆነ መንገድ የድርጅቱ ሰነዶች መወሰዳቸው አግባብ አለመሆኑ በፍርድ ቤት ጭምር ተረጋግጦ ለድርጅት ባልተመለሰበት ሁኔታና የተወሰኑ ሰነዶች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ሳይታወቅ በድርጅቱ የሌሉ ሰነዶችን ለኦዲት እንዲያቀርብ መጠየቁ ከሕግ አግባብነትና ሕጋዊነት አንፃር ባለሥልጣኑ እንዲመለከትለት አመልክቷል፡፡
ሌላው ድርጅቱ በማመልከቻው የጠየቀው ባለሥልጣኑ የግዥ ሰነዶች፣ ከፊል የሽያጭ ሰነዶች፣ የወጪና የሽያጭ ሰነዶች የተመዘገቡበት ሶፍት ኮፒና የሒሳብ ሌጀሮችን እንዲያስረክብ መጠየቁን ገልጾ፣ ምን ማለት እንደተፈለገ ስላልገባው ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ከአገሪቱ ሕጎችና ደንቦች እንዲሁም ከባለሥልጣኑ መቋቋሚያ አዋጅ በደንብና መመርያ አኳያ እንዲጣራላት ፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ በአቤቱታ ጠይቋል፡፡
ሌላው ድርጅቱ በባለሥልጣኑና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች እየደረሰበት ያለውን በደልና የፍትሕ መጓደል እንዲታረምለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአቤቱታ ደብዳቤ መጻፉን ገልጿል፡፡
በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመው ፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች አንዱ ለግንባታ ሥራዎች የሚያገለግሉ ከባድ ተሽከርካሪዎችና መሣሪያዎች ከውጭ ማስመጣት መሆኑን ጠቅሷል፡፡ የሚያስምጣቸውን ተሽከርካሪዎች ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች መሸጥና የተፋጠነ ኢኮኖሚ እንዲመጣ አስተዋጽኦ ማድረግ መሆኑን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በደብዳቤው ገልጿል፡፡ የአገሪቱን ሕግ፣ ደንብና መመርያ አክብሮ የሚሠራ እንደነበርና ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ጋርም ጥሩ ግንኙነት እንደነበረው ጠቁሟል፡፡ ነገር ግን የአቶ ፀጉ ብርሃነ ገብረ እግዚአብሔር ውክልና የሰጣቸው ግለሰብ የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ ሲጠየቁ ሊመልሱ ባለመቻላቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስድስተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ክስ ሲመሠርቱ፣ ግለሰቧ ደግሞ ከአቶ ፀጉ ብርሃነ ጋር የትዳር ግንኙነት እንዳላቸው በመግለጽ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ የቤተሰብ ችሎት ክስ በመመሥረታቸው ከባለሥልጣኑ ጋር ችግር መፈጠር መጀመሩንና ከድርጅቱ የማይገናኝ ችግር እንደገጠመው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፈው የአቤቱታ ማመልከቻ ላይ በዝርዝር አስፍሯል፡፡
ድርጅቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፈው ደብዳቤ የኢኮኖሚ ተቋም መሆኑንና በሥሩ በርካታ ሠራተኞች እንዳሉት ጠቁሞ፣ በባለሥልጣኑ አንዳንድ ሠራተኞችና ኃላፊዎች አስተዳደራዊ በደልና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አንዳንድ ዳኞች በደረሱበት የፍትሕ መጓደል ሕልውናውን ሊያጣ እየተቃረበ በመሆኑ የደረሰበት በደል በጥልቀት ተመርምሮ ችግር የሆኑበት ነገሮች እንዲወገዱለትና የማያዳግም መፍትሔ እንዲሰጡለት ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ ገቢዎና ጉምሩክ ባለሥልጣን ለፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ ለኦዲት አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን እንዲያቀርብ ጠይቋል፡፡ የባለሥልጣኑ የኢንቨስቲጌሽን ኦዲት ዳይሬክቶሬት ለድርጅቱ በጻፈው ደብዳቤ ድርጅቱን ኦዲት ለማድረግ ሐርድ ኮፒና ሶፍት ኮፒ መረጃዎችና ሰነዶችን እንዲያቀርብና የኦዲት መግቢያ ስብሰባ እንዲያደርግ መጠየቁን እንዲሁም የባለሥልጣኑ የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ማኅበሩ በሰጠው ምላሽ ላይ ውይይት መደረጉ ተጠቁሟል፡፡ በውይይቱ የተደረሰው ድምድሜ የገቢ ግብር አዋጁ በሚያዘው መሠረት ግብር ከፋይ ድርጅቱና የሥራ ኃላፊዎች ሊወጡ የሚገባቸውን ግዴታ ለመወጣት ፈቃደኝነት መጓደሉን መሆኑን ገልጿል፡፡ በመሆኑም ድርጅቱ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት እንዲችል ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ የግዥ ሙሉ ሰነዶች ከፊል የሽያጭ ሰነዶች የግዥ ሙሉ ሰነዶች፣ የግዥ፣ የወጭና የሽያጭ ሰነዶች የተመዘገቡበት ሶፍት ኮፒና የሒሳብ ሌጀሮችን አግባብ ያለው የድርጅቱ ኃላፊ እንዲያስረክብ አሳስቧል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ተጠያቂነቱ በድርጅቱ ላይ የሚወድቅ መሆኑንም አሳስቧል፡፡