Latest blog posts

Not published yet

ቁርጥራጭ ብረቶችን ወርቅ በማስመሰል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ከ95.5 ሚሊዮን ብር በላይ አጭበርብሮ ተሰውሯል ተብሎ በሌለበት 25 ዓመታት ጽኑ እስራትና 180 ሺሕ ብር የተፈረደበት አቶ አስማረ አያሌው፣ የቅጣት ውሳኔው ተሰርዞ ክሱ እንደ አዲስ እንዲጀምር ተወሰነ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዝያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ውሳኔውን ያሳለፈው፣ ግለሰቡ ‹‹በሌለሁበትና ባልተከራከርኩበት ይኼንን ያህል የእስራት ቅጣት ሊወስንብኝ አይችልም፤›› ብሎ በመከራከሩ ነው፡፡

ፍርድ ቤቱም ግለሰቡ ያቀረበው የመከራከሪያ ሐሳብ ትክክል መሆኑን በማመን፣ እንደገና በማረሚያ ቤት ሆኖ እንዲከራከር አዟል፡፡

አቶ አስማረ አያሌው ከታህሳስ 1998 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 1999 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ከንግድና ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሐሰተኛ የሆነ የላኪና የአስመጪ ፈቃድ በማዘጋጀት፣ ከማዕድንና ከኢነርጂ ሚኒስቴር ሐሰተኛ የሆነ የወርቅ ጥራት ማረጋገጫ በመያዝ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውስጣቸው ቁርጥራጭ ብረታ ብረት የያዙ 29 የታሸጉ ሳጥኖች በማቅረብ፣ ብሔራዊ ባንክን ከ95.5 ሚሊዮን ብር በላይ በማጭበርበሩ ተከሶ ነበር፡፡ 

አቶ አስማረ ድርጊቱን መፈጸሙ ሲታወቅባት በኬንያ በኩል ከአገር እንደወጣና ለሰባት ዓመታትም መኖሪያውን በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አድርጎ እንደቆየ ታውቋል፡፡ አቶ አስማረ ፈጽሞታል በተባለው በማጭበርበር ድርጊት ክስ ተመሥርቶበት ባለመቅረቡ እርሱ በሌለበት ክሱ እንደተሰማና ፍርድ ቤቱም ጥፋተኛ ብሎት የ25 ዓመት ጽኑ እስራት እና የ180 ሺሕ ብር ቅጣት አስተላልፎበት እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ግለሰቡ እ.ኤ.አ. መስከረም 30 ቀን 2014 በቁጥጥር ሥር ውሎ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ፖሊስ ኮሚሽን በብሔራዊ ኢንተርፖል ተቋማቶቻቸው አማካይነት በተደረገ ትብብር ተላልፎ መስጠቱን የሚታወስ ነው፡፡


Editors Pick

Family Law Blog
  መግቢያ የሰው ልጆች በዚህ ምድር ላይ መኖር የጀመሩትና ማህበራዊ መስተጋብር እንድ ህብረተሰብ ክፍል ብሎም እንደ ሀገር መኖር የጀመሩበት ጊዜ እና ቦታ ላይ የታሪክ ሊቃውንት በእርግጥ ይሄ ጊዜና ቦታ ባይሉንም ረጅም ዘመናትን እንዳስቆጠሩ ይገልፃሉ፡፡ የአንድ ሀገር ወይም ማህበረሰብ መሠረት የሆነው ቤተሰብ እንደሆነ ...
52140 hits
Arbitration Blog
1. Introduction   Arbitration has been a prevalent method of dispute settlement, in various countries of the world of today and yesterday. Arbitration is defined in the Black’s Law Dictionary as “a me...
8536 hits
Constitutional Law Blog
{autotoc}     በሀገራችን ህዝባዊ አመጽን ተከትሎ በሰኔ 2010 ዓ.ም ብትረ መንግሥቱን የሚዘውረው የብልጽግና ፓርቲ ለአመጹ ምክንያት የሆኑትን የዲሞክራሲ ጥያቄዎች ለመመለስ የተቋም ግንባታ እና የህግ ለውጦችን እያደረገ ነው፡፡ በተጨማሪም ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ከኦሮሚያ እና አማራ ብሔር ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር...
2928 hits
Constitutional Law Blog
  በዓለማችን እና በሀገራችን የተከሰተውን የኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ በሀገራችን የፌደራል መንግሥትና የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች መታወጃቸው ተከትሎ የሀገራዊ ምርጫን መራዘምና ክልላዊ ምርጫ በትግራይ መከናወኑን ከሕገ-መንግሥቱ ድንጋጌዎች አኳያ እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ፡፡ በቅ...
3515 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...