Latest blog posts

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋኩልቲ የሥነ አዕምሮ ዲፓርትመንትና ከአማኑኤል ሆስፒታል ጋር በመተባበር የአዕምሮ ጤንነት ችሎት ማቋቋሙ ታወቀ፡፡ 

ሚያዝያ 9 እና 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በቸርችል ሆቴል ባለድርሻ አካላት ከሆኑት የፖሊስ አባላት፣ ዳኞች፣ ዓቃቢያነ ሕግ፣ የምርመራ ክፍል ሹሞች፣ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች፣ የአማኑኤል ሆስፒታል ሐኪሞች፣ የሰላም አምባሳደሮችና ሌሎችም ተሳታፊዎች በተገኙበት ለሁለት ቀናት በተደረገ ውይይት፣ ስምምነት ላይ በመደረሱ ችሎቱ ሊቋቋም ችሏል፡፡

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሥነ አዕምሮ ባለሙያ በሆኑት ዶ/ር አስናቀ ልመንህ፣ በተጀመረው የሁለት ቀናት ውይይት ላይ ለሆስፒታሉ ዕርዳታ የሚለግሱና በአገራቸው ተመሳሳይ ችሎት ከተቋቋመ 15 ዓመታትን ማስቆጠሩን የገለጹ፣ ሁለት የካናዳ መንግሥት ተወካዮች፣ አንድ የሕክምና ባለሙያና አንድ ዳኛ መገኘታቸው ተገልጿል፡፡ 

ለሁለት ቀናት በቆየው የውይይት መድረክ ላይ ከተሳተፉ ባለድርሻ አካላት፣ ስለአዕምሮ ጤንነት ችሎት መቋቋም ዓላማና ተግዳሮቱ ተነስቶ ውይይት ተደርጓል፡፡ 

የአዕምሮ ሕሙማን ጥፋት የሚያጠፉት ሆን ብለው ሳይሆን፣ በሕመም ምክንያት በመሆኑ እንዴት መረጋገጥና መለየት እንደሚቻል፣ በጤንነታቸው ምክንያት ረዘም ያለ ጊዜ በእስር ከመቆየታቸው በፊት በፍጥነት ተለይቶ መታወቅ ስለሚቻልበት ሁኔታ፣ ሕመሙ ሳይታወቅለት በተጠረጠረበት ወንጀል ቅጣት ተጥሎበትና ቅጣቱን ጨርሶ ሲወጣ ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይደግም ለመቆጣጠር አስፈላጊና ጥሩ ጅምር መሆኑን፣ ሁሉም ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት እንደተስማሙበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተለይ የፖሊስ አባላት ሕሙማኑን ቃል ሲበቀሏቸው እነሱ እንደፈለጉ ሳይሆን፣ ሕሙማኑ የሚነግሯቸውን ብቻ እንዲቀበሉ ችሎቱ መቋቋሙ ጥሩ መሆኑን የገለጹት ተሳታፊዎቹ፣ ይኼ ሲሆን ደግሞ ከፖሊስ ምርመራ የሚገኘው የቃል ውጤት ለሐኪሞች ምርመራ መነሻ ስለሚጠቅም፣ የሕሙማኑን ጤንነት በቀላሉ ማወቅ እንደሚቻልና መፍትሔም ለማግኘት ቀላል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የችሎቱ ስያሜ ሕሙማኑ የሚገለሉበት እንዳይሆኑ፣ የሕግ ማዕቀፍን በሚመለከት የወንጀል ሕጉ ችግር ባይኖርበትም፣ የወንጀል መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ ግን ፖሊስ ሕሙማኑን እንዴት መያዝ እንዳለበት፣ ሕሙማኑ እንዴት ተለይተው እንደሚያዙ በዝርዝር አለመቀመጡና የበጀት፣ የሆስፒታሎችና የባለሙያዎች እጥረት ለችሎቱ ተቀዳሚ ተግዳሮቶች እንደሚሆኑ በውይይቱ ተነስተዋል፡፡ የሚመደበው ዳኛ በችሎቱ የሚያየውና ችሎቱም የሚያስተናግደው የአዕምሮ ሕመምተኞችን ብቻ ነው? ወይስ ሌሎችንም ጉዳዮች ያያል? ተጠርጣሪውን ዕለት በዕለት የሚከታተልና ሕሙማኑ የሚቆዩበት ማቆያ ቦታና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት፣ ተወያይተው ችሎቱ እንዲቋቋም ውሳኔ ማሳለፋቸው ተገልጿል፡፡

ስለችሎቱ መቋቋም ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው፣ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ለችሎቱ መቋቋምም ከፍተኛ ጥረትና ጥናት በማድረግ ‹‹እውን አድርገውታል›› የተባሉት አቶ ደሳለኝ በርሔ የችሎቱን መቋቋም አረጋግጠው፣ ‹‹የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአዕምሮ ጤንነት 14ኛ ችሎት›› መባሉን ገልጸዋል፡፡

አንድ ሰው ወንጀል ሲፈጽም ‹‹አዕምሮው ጤነኛ ነው? ወይስ አይደለም?›› የሚለውን ለመለየት (ለማወቅ) ረጅም ጊዜ ይፈጅ እንደነበር የገለጹት አቶ ደሳለኝ፣ ‹‹አንድ ሰው ያለው የጤንነት ሁኔታ በፍርድ ቤት ቆሞ ለመከራከር ያስችለዋል ወይስ አያስችለውም? ተከሶ የቀረበበት ጉዳይ ሲነገረው ይገባዋል ወይስ አይገባውም? ቆሞ መከራከር ይችላል ወይስ አይችልም?›› የሚሉትንና ሌሎች መሥፈርቶችንም ችሎቱ በቀላሉ ለመለየት እንደሚረዳ አስረድተዋል፡፡ 

አንድ የአዕምሮ ሕመም እንዳለበት የተረጋገጠ ተጠርጣሪ ዋስትና የማይከለክል ቢሆንም፣ የባህሪው ሁኔታ ‹‹ዋስትና ያስከለክለዋል ወይስ ይፈቅድለታል? አንድ ጊዜ የፈጸመውን የወንጀል ድርጊት በድጋሚ ይፈጽመዋል ወይስ አይፈጽምም?›› የሚለውን ለማወቅ፣ ቀደም ባሉት ጊዜያት ከሆስፒታሎች ጋር በመጻጻፍ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ይኼ ችሎት ከተቋቋመ በኋላ ግን እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡

መጻጻፉ የሚቆመው ለአዕምሮ ጤንነት ችሎቱ የሚያስፈልጉ የሥነ አዕምሮ ባለሙያዎች፣ ሐኪሞች፣ መርማሪዎችና ሌሎች አካላት በፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ ቢሮ ተሰጥቷው ከዳኞች ጋር በቅርበት እየተነጋገሩና በችሎትም እየታደሙ ሥራውን አብረው በመሥራታቸው መሆኑን አቶ ደሳለኝ አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የአዕምሮ ሕሙማኑን የሚለቀው ቤተሰብ ወይም የሚጠብቀው አካል ጉዳት እንደሚያደርስና በአግባቡ እንደሚጠብቀው ግዴታ ውስጥ ገብቶ እንደሚሆንም አክለዋል፡፡

ሐኪሞቹ፣ ባለሙያዎቹና ዳኛው በቀላሉ ከመግባባታቸውም በተጨማሪ (አብረው ሲሠሩ) ትልቁን ኃላፊነት በመውሰድ የመንግሥትንና የኅብረተሰቡን ኃላፊነት የተሸከሙትን የአዕምሮ ሕሙማን ቤተሰቦች ስለሕሙማኑ ሲያስረዷቸው ሳይሰለቹ በቀላሉ እንዲረዷቸው በማድረግ፣ ችሎቱ ትልቅ ጥቅም እንዳለው አቶ ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡

የአዕምሮ ጤንነት ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው የሚታዩ ተማርማሪዎች ቅጣት የሚወሰንባቸው በመደበኛና እንደ ማንኛውም ችሎት መሆኑን የገለጹት አቶ ደሳለኝ፣ ዋናው ጥቅሙ በምርመራና በመጻጻፍ ከሁለት ዓመታት በላይ ይፈጅ የነበረውን ጊዜ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅና በተለይ ከቤተሰቦቻቸውና ከዳኞች ጋር ያለውን ሁኔታ የተመቻቸ ማድረግ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን አስረድተዋል፡፡


Editors Pick

Arbitration Blog
{autotoc}         Abstract Today, the adjudicatory system of arbitration is replacing the court, since it is considered to be more private, economic, rapid, certain, conducive to business relationship...
4191 hits
Arbitration Blog
In 1996 the case between Arab Republic of Egypt v Chromalloy Aero services brought a new debate to the international arbitration world. Chromalloy Aero services (“Chromalloy”), an American corporation...
11959 hits
About the Law Blog
  መንግሥት ገቢ ከሚሰበሰብባቸው ምንጮች መካከል የቴምብር ቀረጥ አንዱ ነው፡፡ የቴምብር ቀረጥ ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ ሲሆን፣ የሚሰበሰበውም በተወሰኑ ሰነዶች ላይ እንዲለጠፍ ወይም እንዲከፈል በማድረግ ነው፡፡ በአገራችን የቴምብር ቀረጥ የተጣለው ስለ ቴምብር ቀረጥ አከፋፈል በወጣው አዋጅ ቁጥር 110/90 መሠረት ነው፡...
16166 hits
Legislative Drafting Blog
 “No law, regulation, directive or practice shall, in so far as it is inconsistent with this Proclamation, have force or effect with respect to matters provided for by this Proclamation”. 1.      Intr...
13917 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...