Latest blog posts

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ማክሰኞ በዋለው መደበኛ ጉባዔው፣ የሁለት የፌዴራል ዳኞችን ሹመት አነሳ፡፡ ውሳኔውን ያስተላለፈው ሁለቱ ዳኞች በሙስና ወንጀል ተከሰው ጥፋተኛ መሆናቸውን ካረጋገጠ በኋላ መሆኑ ታውቋል፡፡ 

የፌዴራል ዳኞችን ሹመት የሚያፀድቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን፣ ከሹመት የሚያነሳውም ራሱ ፓርላማው እንደሆነ በሕግ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሠረት የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ታኅሳስ 7 ቀን 2007 .. ለምክር ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ፣ ሁለቱ ዳኞች እንዲነሱለት መጠየቁን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ፓርላማው ጉዳዩን ለራሱ የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመምራት ጥያቄውንና ምክንያቱን እንዲመረምር ልኮታል፡፡ ኮሚቴው ከዳኝነት እንዲነሱ የተባሉትን አንደኛ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ብርሃኑ መሸሻ ላቀው፣ ሁለተኛው ደግሞ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ዘሪሁን አስፋው ቅጣው ላይ የተጠቀሰውን የዲሲፕሊን ችግር መመርመሩን፣ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ያስረዳል፡፡

አቶ ብርሃኑ መሸሻ ላቀው ከሐምሌ 2001 .. ጀምሮ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኝነት ሲሠሩ የቆዩ መሆኑን፣ ነገር ግን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በጉቦ መቀበል ወንጀል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን በነፃ እንዳሰናበተ፣ ኮሚሽኑ በመቀጠል በይግባኝ ክሱን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ በመዝገብ ቁጥር 90525 መስከረም 30 ቀን 2006 .. ተከሳሹን ጥፋተኛ እንዳላቸው አረጋግጧል፡፡

በጥቅምት ወር 2006 .. በሰጠው የቅጣት ውሳኔም ተከሳሹ የስምንት ዓመት ጽኑ እስራትና 5,000 ብር እንዲቀጡ ወስኗል፡፡ ይሁን እንጂ ግለሰቡ ቅጣቱ ተግባራዊ እንዳይሆንባቸው አገር ለቀው መሄዳቸውንም አረጋግጧል፡፡

አቶ ዘሪሁን አሰፋ ቅጣው የተባሉት ዳኛም እንደዚሁ በጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል በሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ክስ ተመሥርቶባቸው፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የአራት ዓመት ጽኑ እስራትና 7,000 ብር ቅጣት እንደተጣለባቸው፣ የይግባኝ መብታቸውን ተጠቅመው እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ሕጋዊ መብታቸውን መጠቀማቸውን፣ ነገር ግን በሁሉም ፍርድ ቤቶች ጥፋተኝነታቸው መፅናቱን ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡

 

በመሆኑም የፌዴራል ዳኞች አስተዳዳር ጉባዔ የዳኞቹ ሹመት እንዲነሳ የጠየቀው በሕግ አግባብ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው በሙሉ ድምፅ በመስማማት፣ ፓርላማው ሁለቱን ግለሰቦች ከዳኝነት እንዲያሰናብት ጠይቋል፡፡ ምክር ቤቱም የውሳኔ ሐሳቡን በሙሉ ድምፅ ተቀብሎታል፡፡


Editors Pick

International Law Blog
  World Trade Organization (WTO) was established with the main objective of liberalizing multilateral trade, based on the belief that the liberalization of trade brings multiple of benefits to the wor...
16116 hits
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
  Synopsis Labor is the most important activates of a human being crate both material productivity and social values. Now a day it is not a point of disagreement that the development of any given coun...
9453 hits
Intellectual Property and Copy Right Blog
-    ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ስራዎች የቅጂ መብት በአዋጁ እንዴት ይታያል? -    ያለ ባለቤቱ ፍቃድ ማሳተም አለመከልከሉ የቅጂ መብትን ሌላ ሰው እንዲጠቀም መፍቀድ ማለት ነው፤ -    በመፅሔት፣ በጋዜጣ እና በመፅሐፍ የወጡ ስራዎች የሚኖራቸው የቅጂ መብት ጥበቃ ይለያያል? -    በአለቃ አያሌው ታምሩ ወራሾችና...
10621 hits
Intellectual Property and Copy Right Blog
The idea of enacting a copyright law was first developed to encourage creativity and further grew on that sole purpose and protecting companies’ and individuals’ right to ownership.  Such protections ...
11734 hits

Top Blog Posts

About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...
Succession Law Blog
መግቢያ ማንኛውም ሰው አንድ የፍርድ ውሰኔ ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ያለው እንደሆነ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሊያቀርብ ሚችልበት የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቶ ይገኛል፡፡ ይህን መሰል የጊዜ ገደብ በሕግ አጠራር ይርጋ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜውም በሕግ በተቀመጠው የጊዜ ገደ...
Succession Law Blog
መግቢያ የውርስ ህግ ክፍል በሆነው የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 826 ላይ እንደተመላከተው አንድ ሰው የሞተ አንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው በሆነበት ስፍራ የዚህ የሟች የውርስ ሀብት ይከፈታል፡፡ የሟች ውርስ ሟች በሞተበት ቅጽበት የሚከፈት ቢሆንም የሟች የውርስ ሀብት እስከሚጣራ ድረስ የሟች ንብረት እንደ አንድ የ...